ልጥፎች

ስለዕንባ ጸጋዬ ራዲዮ 18 03 2021

ምስል

Meine Füllfeder.

ምስል
  Willkommen bei Kebebush Media. „Der HERR schaut vom Himmel auf die Menschenkinder, dass er sehe, ob jemand so verständig sei und nach Gott frage ,“ (PSALM 14/2)   ·       Meine Füllfeder   Die Abendglocke Mein Abendlicht Schönest ist sie … Immer noch blitz sie Im Tiefesten denke ich Sie ist schön … Sie hat Geduld mit mir Möge Gott die Welt und dich beschützen. Amen. Herzliche.   Sergute©Selassie Schweiz (Winterthur.) 18.03.2021

የመጋቢት 18. 2021 የጸጋዬ ራዲዮ በሲዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። ዕለተ ሃሙስ ማዕዶተ አሰጋሪው ሃሙስ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 16) ·        ማ ዕዶተ አሰጋሪው ሃሙስ ዕለተ ጸጋዬ ነው። ዛሬ 18.03.2021 ዙሪክ ከተማ በ97.5 መካከለኛ ሞገድ በራዲዮ ሎራ ከ15.00 – 16.00 በአማርኛ ቋንቋ የጸጋዬ ራዲዮ ይቀርባል። በመሰናዶዬ ማሰረፊያ የሚሆኑ መዝናኛወች በቁጠባ ስለሚቀርቡ ከ50 ደቂቃ በኋላ ያን ለሚፈልጉ ቅኖች የ10 ደቂቃ ጊዜ ሰጥቼ እሰራለሁኝ።  በተረፈ 10 ደቂቃ ሲቀርም ቀደም ብዬ ሼር አደርገዋለሁኝ። እናንተም ቀድማችሁ ቁጥር አንድ ሊንኩን ብትከፍቱት ታገኙታላችሁ ላይፍ ላይ ያለውን ከእኔ የቀደመውን ዝግጅት። ማለፊያ የመደማመጥ ጊዜ እመኛለሁኝ። ዙሪክ ክፍለ አገር ለምትኖሩት ደግሞ ራዲዮ ላይ ታገኙታላችሁ። ዕድሜ ለ እጬጌው ግሎባላይዜሽን። የልብ አድርስ ነው።     ላይፍ ላይ መከታተል ለማትችሉ ዘግዬት ብዬ ዩቱብ ቻናሌ ላይ እለጥፈዋለሁኝ። በተጨማሪም ጸጋዬ ራዲዮ አርኬብ እልፍኝ ላይም ይኖራል። ዘመኑ የልብ አድርስ ነው። ·        ቁ ጥር አንድ ሊንክ። ዘግይታችሁም አርኬቡ ላይ ማዳመጥ ትችላላችሁ።   https://www.lora.ch/sendungen/alle-sendungen?list=Tsegaye ·        ቁ ጥር ሁለት ሊንክ። ዘግይታችሁ ማድመጥ ለምትሹ። ከፕሮዳክሽን በኋላ ስለሚለጠፍ። https://www.youtube.com/channel/UCJEQXw86u_NG4A1FVC1j2qg እግዚአብሄር ይስጥልኝ።    ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18

የመኖር (የሕይወት) ፍልስፍናዬ በጥቂቱ። 17.03.2021

ምስል
ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ   ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ሮቡ ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በቢሆነኝ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ እንዳልጠግብ፣ እንዳልከዳህም “ ( ምሳሌ 30 ቁጥር 8) • ዕ ፍታ። ዕለተ ማዕዶተ ተናኜ ፈንገጥ ያሉ ዕይታዎቼ የሚቀርቡበት ነው። የሃሳብ ቀን። • የመኖሬ ፍልስፍና። ፍኖተ ካርታ ልንለው እንችላለን። ህይወቴን እምመራበት በርካታ መርሆዎች አሉኝ። ዝርግነት አልወድም። ዝርግ ሰውም ክፍሌ አይደለም። ልሙጥነትም ተጠግቶኝ አያውቅም። ጠፍጣፋነትንም እጠዬፋለሁኝ። ውራጅ ሰብዕና የለኝም። ራሴን ተውሼም አልኖርኩም። ልብ እንዲገጠምልኝ አልፈቅድም፤ ምን እንዳለኝ፤ ምን እንደምችል፤ ምን እንደሚፈቀደልኝ፤ ምን ደግሞ እንደማይፈቀደልኝ ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። በሚገባ። እራሴ ተቋም ነኝ። ዝንቅ ያልሆነ ወጥ አሻረም አለኝ። (1) መ ኖር ነፃነት ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። (2) ለ ነፃነቱ ደግሞ መታመን። (3) ለ መታመኑ ተፈጥሯዊነት። (4) ለ ተፈጥሯዊነቱ ጥሩ አስተዳዳሪነት። (5)     ለ ጥሩ አስተዳዳሪነቱ ጥሩ አድማጭነት። (6)    ለ ጥሩ አድማጭነት ጥሩ ዕውቅና። (7)    ለ ዕውቅናው ውስጥን ሳይሰስቱ ወይንም ሳይነፍጉ መስጠትን። (8)    መ ስጠትን በተሰጠው ልክ ሚዛኑን አስጠብቆ እራሰን ሳይሸሹ ወይንም ከራስ ጋር ድብብቆሽ ሳይጫወቱ።   1)        በቅድሚያ ስለ ነፃነት።          ነፃነት