ልጥፎች

ከጁን 19, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሰቆቃው ጴጥሮስ ይህችን ሰዓትም።

ምስል

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ እና የሚኒስትሪ ቀጣይ ዕጣን በሚመለከት የት/ሚር የወሰደው ደፋር እርምጃ ጥሩ ነው።

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።  የት/ሚር ደፋር እርምጃ ጥሩ ነው። „ወርቅና ብዙ ቀይ አንቚ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።   መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭“ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እፍታ በመሆን ውስጥ ያለ መኖር ሥነ - መኖሩ ዕውቅና ያለው ነው። በመኖር ውስጥ ያለ አለመኖር ደግሞ ሥነ - መኖሩ ስሩዝ ነው። በመሆን ውስጥ ያለ መኖርም ሥነ - ሰውነቱ ህልው ነው። በመሆን ውስጥ የሌለ መኖር ደግሞ ሥነ - ህይወቱ ተደፍሯል። በ መደፈር እና በማስ ደፈር ያለው ድልድይ ደግሞ እንደዬሰብዕናው ኩሰት ወይንም ጥንዙልነት ፤ ወይንም ቀጥነት ፤ ወይንም ዝልቅነት ይወሰናል። ድልድዮ ደግሞ እውነት ከሆነ ከቀጥነት ከዝልቅነት ጋር ሲዋደድ፤ ዕብለት ከሆነ ግን ጥንዙልነት እና ኩሰት ይገጥማዋል። በዚህ ማህል አዲስ ትውልድ፤ ተተኪ ትውልድ፤ መጪ ትውልድ ደግሞ አለ። ይህ የትውልድ ሂደት ባለማቋረጥ ሲከታታል ቁጬታው በቁጭታ መዳህነት ከተባዛ ወይንም ከተደማመረ ትውልድ ተከታይም፤ ተተኪም፤ መጪም ትውልድ የብክነት አንፓዬር ሥጦታ ይቀርብለታል። በዚህ ስምጠት ባናወዘው የብከነት ኢንፓዬር ውስጥ ማግሥትን ማሰብ ይከብዳል። መሰረታዊ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው በቀጣይ ትውልድ ላይ ልብ ያለው ተግባር ለመከወን ከብክነት የሚታዳግ፤ ጭምት ፤ ምራቁን የዋጠ እስተውሎት ይሻል። የወግ ገበታ። የሰሞኑ የት/ሚር ከግልቦ ንድፍ ወጥቶ እንደ ቀደመው የ8ኛ እና የ6ኛ የሚኒስትሪ ፈተናን አሰጣጥን፤ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የደረጃ ልክን ጨምሮ፤ የማትሪክ ፈተና አሰጣጥን ለማሻሻል ወይንም በምልሰት ራሱን ወቅሶና፤ ራሱን ነቅ