የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነትን በቀዝዝቃ ጦርነት እናስረክብ ነው፤ የኮሚሽኑ ልዩ ኮሚቴ ፍላጎት።
የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነትን በቀዝዝቃ ጦርነት እናስረክብ ነው፤ የኮሚሽኑ ልዩ ኮሚቴ ፍላጎት። "ከንቱ፤ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ጠቅላላ የኢትዮጵያ ተቋማት፤ አህጉራዊ ይሁን ሉላዊ የሥልጣን ቦታወች በገፍ ለማን እየታደለ እንዳለ ይታወቃል። ይህም ይሁን ተብሎ ኢትዮጵያዊነት መንበረ - እርካቡን፤ ማዕዱን አስረክቡን "አንገት የተሰራው አዙሮ ለማየት ነው" ብሂልን ይድጠዋል። በዚህ ስሌት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር በኦሮምያ አስተዳደር #ሥር ይወድቃል። ማናቸውም ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ዓለም ዓቀፋዊ ጉባኤወችም በኦሮምያ አስተዳደር ስር ይወድቃሉ። የተንጠራራ ፍላጎት ነው ያለው። መግራትም፤ መቆንጠጥም አልተቻለም። ብልፄው እራሱን ፈቅዶ #እየናደ ይገኛል። ውስጥን በዝምታ ማሸፈት ጠንቁ ለራሱ ነው ለብልፄው አገራዊ ነኝ እያለ ሲደሰኩር ባጅቶ ዞጋዊ መሆኑን እራሱ እየመሰከረ ነው። ዲስፕሊኑ ሲጣስ ጸጥ ረጭ ብሏል። አንድ የፖለቲካ ድርጅት ዲስፕሊኑን መቆጣጠር ከተሳነው አናርኪዝም ይነግሳል። አናርኪዝም #አንጃ ይፈጥራ። አንጃው ፍርሻ ነው። በኢሠፓ ውስጥ አንጃ ተፈጥሮ ሁለት ዓመት አልቆየም ኢሠፓ መራራ ስንብት ያደረገው። ወፋ ጥሩ አይደለም። ኦሮምያ አስተዳደር መንፈሱ ኦነግ #ወረስ ነው። ኦነግ ደግሞ ህልሙም ፍላጎቱም ከኢትዮጵያ #መነጠል ነው። ይህን ለማስፈጸም ነው "አገራዊ" በሚል የተቋቋመው ኮሚሽን እያስፈጸመ የሚገኘው። " #ዋስትና " ከበሪንግ ነው። ወይንም ቅርፊት። አገር ተሰጥቶህ፤ ኖቤል ተሸልመህበት፤ ብሪክስ ላይ ቤተኛ ሆነህ ዋስትና ትጠይቃለህን??? ዋስትና በአንድ ሉዓላዊ መንግሥት ...