ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።

 

• ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።
ዕለተ ሰነበት ማዕዶተ ርትህ ወሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።
ጥልፍ
„አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫
ጠብታ! ዘለላ-
የመንፈስ ወለላ
መዳፈ-ጥልፍ
ጠፈፍ!
አልቦሽ ጠረፍ
ብራና ላይ ሲንጠፈጠፍ
ዛላው ሲርገፈገፍ
ጊዜ አይሽረው አይነጥፍ
አይሆን ጠፍ
ጥልፍ!
ብዕረ ምጥ-የቁርጥ
የቀለም ሰርጥ
ንጥር የምናብ መረቅ
ነበልባላዊ መንፈስ አቅልጥ
ጥልፍ!
የቅመም ውቅጥ
የተግባር ነቁጥ
ወልጋዳን ቆንጥጥ፣
ተባደግን አፍርጥ-ደፍጥጥ
ጥልፍ!
ነው ጥልፍ
የኮፒ እንፋሎት፣
ፍ ላ ሎ ----------- ት
ሮ ኆ ቦ ------------ ት
ጥልፍ!
ዘይቢያዊ ንቅሳት
ነቀል - ተከል፣ የሌለበት
ቀድሞ የሚያልፍ፣
አይደለም ግርድፍ
ማገሩ አለው ውብ ዘርፍ
የሚያዘርፍ፤
ጥልፍ!
ገለባን የሚቀርፍ
ድቃቂን የሚያራግፍ፣
ባለ ጥርኙ ጥልፍ
ፍቅርን የሚያሳቅፍ
ጥልፍ!
የአብረንታት ጥልፍ
ደፋር …
የሚያመረቃ ጨረር …
የቅኝት ጥልፍ
የዜማ ጥልፍ
የእስትንፋስ - ጥልፍ
የሕሊና ደም ጥልፍ
የሚታገል ግፍ…
የሌለበት እድፍ
ጥልፍ
እዮር እፍ ያለበት እፍ
የብዕር ጥልፍ!
ቅዱሰ መንፈስን የሚጠልፍ
የሚያራግፍ፤ ግ --------- ፍ፡
ጥልፍ
ቆመ ለዕልፍ
ለሥነ-ተፈጥሮው ህግጋት … አለ እልፍ
እ ------------- ፍ
የርትህ እቅፍ
የማይል ዝንፍ፤
አንባገነንን ’ሚዘነጥፍ
መለመላ የሚያሰነጥፍ
ምሰባክ የእልፍ፤
ጥልፍ
ሰማያዊ ጽንፍ
ረቂቅ ንድፍ
ባለ ትርፍ፤
የማይደክም
ዓራት ዓይናማ - የማያርፍ
የሚዳኝ - ግርድፍ
ጥልፍ፤ ውጽፍተ-ምዕራፍ .....
ሥርጉተ©ሥላሳሴ
Sergute©Selassie
21.08.2021
ከግፈኞች ጋር ለሰከንድ አልቆምም!
ግፈኞችን አገሬ ኢትዮጵያ አብዝታ ትጠየፋቸዋለች!
ገዳዮችን መንፈሴ አያስጠጋቸውም! ፈጽሞ!
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።