#አድሎ እና #አግላይነት ይቁም! "ከልጅልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ።" ኮሚሽኑ የክት እና የእዳሪ ልጅ አለው። #የቀዝቃዛው ጦርነት ሂደት ቀጥሏል።

 

#አድሎ እና #አግላይነት ይቁም! "ከልጅልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ።" ኮሚሽኑ የክት እና የእዳሪ ልጅ አለው።
#የቀዝቃዛው ጦርነት ሂደት ቀጥሏል።
 
"ከክፋ ሸሽ፤ መልካሙን አድርግ፤
ለዘላዕለም ትኖራለህ።"
(መዝሙር ፴፮ ቁጥር ፳፯)
 
 May be an image of text
 
ለምክክር ኮሚሽኑ የቤት ልጅ አቆላማጭ፤ አባባይ ልዩ ኮሚቴ አቋቋመመ።
 
የማይገባኝ የማህበረ ኦነግ ቤተኞች ኢትዮጵያዊነትን የሚያገሉበት፣ እነሱን ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ አውጥተው የመንፈስ ውጊያ በየዘመኑ የሚያደርጉበት፣ እኛን ገፍተው ዶክትሬናቸው እኔ - እኔ - እኔ - የእኔ - የእኔ - የሚሉበት ጉዳይ ነው። እኛ እኮ በውስጣቸው ፈጽመን የለንም። ኧረ እኛ አማራነት አለ በዘር ሐረጋችን ሌሎችን ወገኖቻችን ቢያንስ የእኛ የማይሉበት ምክንያት አይገባኝም።
 
#የሆነ ሆኖ ………
 
"በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ኮሚሽኑን የሚያግዝ አዲስ ኮሚቴ ተዋቀረ " ሪፖርተር።"
ይህ ጉዳይ በቅጡ ምላሽ ካላገኜ ከፋኝ ላሉት ታጣቂወች ንጥረ አመክንዮ ይሆናል። አቅማቸውን ይጨምራል። ተስፋቸውን #ያደረጃል። የተበተነ መንፈስንም ይሰበስባል። በተለይ ሳይለንት ማጆሪቲውን የማቅረብ ሁነት ይፈጥራል። 
 
አሰላ የአርሲ ፎለቄ ዋና ከተማ፤ በደምብ ነው የማውቃት።
ጅማ ተወዳጁ የከፋ ክ/ አገር ዋና ከተማ፤
መቱ የደጋጎቹ የኢሊባቡር ዋና ከተማ፤
ነቀመት ተናፋቂው የወለጋ ዋና ከተማ፤
ድሬ እናታዊ የሁለመና ደማቅ ከተማ፤
ደብረዘይት ውዷ እታጌዋ ከተማ፤
ሻሸመኔ የህብራዊነት አብነት ከተማ፤
 
ናዝሬት ብቋዋ የደህንነታችን ዋስትና ከተማን አንድም ሳቢነት፤ አጓጊነት ሳያክል ጠቅልሎ የያዘው የአቶ አባዱላው #ኦህዴድ
በጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ የኦሮሞ ብልጽግና የሽዋን ዋና ርዕሰ መዲና፤ የኢትዮጵያን #አናት፤ የፓን አፍሪካኒዝም
#ትንፋሽ፤ የዓለም የዲፕሎማሲ #ትርታን ካልጠቀለልኩ ብሎ ብሄራዊ የተባለው ምክክር ኮሚሽን ቀርቅሮ የአንድ ክልል
መብት አስጠባቂ፤ የአንድ ክልል ፍላጎት አስጠባቂ፤ የአንድ ክልል ተጠሪ እራሱን አድርጎ ሂደትን #እየነዳደለው ይገኛል።
#ይበለው! አሜን።
 
ለምክክር ኮሚሽኑ ሲያንሰው ነው። አዲስ አበባን ወደ #ዞን ደረጃ ቁልቁል ለማውረድ የተጋው ምክክሩ ኮሚሽን ……
 
1) አዲስ አበባ ክልል ትሁን፤
2) አዲስ አበባ እራስ ገዝ ትሁን የሚሉትን በኽረ ጉዳዮች ጥሎ አዲስ አበባ "የፌድራሉ እና የኦሮምያ ትሁን" በሚል
#ልስን ተስፋ ገዳይ፤ አማራጭ አሳጪ ጉዞ ጉዳይ #ሲያስታምም ቆይቶ አሁን ደግቦ ለቤት ልጁ "ልዩ ኮሚቴ" እንዳቋቋመ
ሪፓርተር ዘግቦታል። 
 
ያለፋበትን፤ ያልደከመበትን እንዴት ይመኛል? የደከመበት የለፋበት ከ6ሚሊዮን ህዝብ በላይ ማንነቴ አዲስ አበባ ናት የሚል
ህዝብ እያለ ተጨፍለቅ እየተባለ ነው ያለው። እንደምን ህዝቡን እንደ ሌለ ይቆጠራል። በአርሲ፤ በወለጋ፤ በሐረር፤ በባሌ፤
በሻሸመኔ ያ ሁሉ ስቃይ እኮ "መጤ"በሚል ሰቅጣጭ ጉድ ነው ህዝቡ የተንገላታው። በኦርቶተዋህዶ ኦሮሞወችም
#ሰማዕትነት ተቀብለዋል።
 
"አገራዊ" ለማለት ይከብደኛል። አዲስ አበባን ለአንድ ዞግ ለማውረስ ከሆነ የኦሮምያ ክልል ከመሆን ውጪ
ሌላ ከፍ ያለ ተልዕኮ መያዙን የሚያሳጣ ስለመሆኑ ከተጀመረ ጀምሮ እያስተዋልን ነው ኮሚሽኑን።
በአደረጃጀቱም ብዙ ግድፈት ነበረበት። ፍፃሜው ቀብሩን አጭቶ እንደሚሆን እራሱን ክዶ እያሳየን ነው።
ከብሄራዊነት ወርዶ የአንድ ክልል ጉዳይ አስፈፃሚነት። ለዚህ ለዚህማ የብልፄው መንግሥት በአንድ ዓዋጅ
ካለምንም ወጪ ሊፈጽመው ይችል ነበር። 
 
የ130 ሚሊዮንን አንጡራ ሃብት በጠራራ ጸሐይ ለአንድ ክልል "የበላይ" አካል ምንትሶ ቅብጥርሶ እየተባለ
እዚህ ተደረሰ። አዲስ አበባ ከሁለት ተከፍላ ሸገር ሲቲም ለኦሮምያ ተካሎ እንጠቅልል ነው ፍልሚያው።
አገር #አራጠህ እየገዛህ በዚህ ልክ እራስን ነጥሎ መገኜት የጤና አይደለም።
 
ሂደቱ የእኛን እብደት ይሁን #ወፈፌነት ያጋለጠ ክስተት ነው። "የኢትዮጵያ ሱሴ በሽተኞች" ያመጣነው መከራ ነው
ይህ የማይገፋ ውሃ ያዘለ ተራራ። ነገ አንባይን እስከ ምንጩ ላለመጠቅለሉ ምን ዋስትና አለ???
 
የደብረ ዘይት የአየር ማረፊያ፤ የኢተያ የንፋስ ኃይል ማመንጫ የዴንማርክ ብራንድ፤ የአባይ ግድብ፤ ላቅ ሲልም
የወደብ፤ የባህር በር ጥያቄ በራሱ ጊዜ መንፈሱን #እያጫጫው ይገኛል ሂደቱ። ኮሪደር በለው የጫካ ፕሮጀክት
ለገዳ ዶክትሬን የሥጦታ ትልም ይሆናል ማለት ነው በዚህ አያያዝ። አዲስ አበባም በቢዛ ቀጣዩ ውሃ ያዘለ ተራራ።
 
50+ የሆነው ጭምቱ፤ ርጉው፤ ሥልጡኑ የአማራ ህዝብ ያላቀረበውን ጥያቄ፤ ታታሪው፤ ትጉሁ የጉራጌ ህዝብ ያላነሳውን፤ ደህነነቷን ሲንከባከብ የነበረው የሱማሌ ትንታግ ህዝብ፤ ታታሪወች የትግራይ ህዝብ ያላቀረቡትን የይገባኛል "የእኔ" ጥያቄ አባ ጠቅልል ኦቦ ገዳ እንደ ተፈጥሮዬ ልጠቅልል እያለ ሂደቱን ቁም ስቅሉን እያሳዬው ይገኛል። እራሳቸው ዶር አብይ ናቸው መደመር ከገዳ ስለመሆኑ የነገሩን። 
 
6 ሚሊዮን ህዝብ በሞጋሳ ልጅነት …… በዚህ ውስጥ የህዝብ ቁጥር እንደምን እንደሚንር እዩት። ፖለቲካዊ ውክልና፤ ዜጋዊ መብት የሌለው የግዴታ አገልይነት ብቻ። 
 
የሚገርመኝ የኮሚሽኑ ፍጹም #አድሏዊነት ነው። ኮሚሽኑ የኢትዮጵያን ህዝብ መንፈስ ተጭኖ አንዱን ልጅ ሌላውን እንጀራ
ልጅ፤ አንዱን የክት ሌላውን የእዳሪ፤ አንዱን ጫኝ ሌላውን ተጫኝ፤ አንዱን የቅርብ ሌላውን የሩቅ፤ አንዱን የውስጥ ሌላውን
የውጭ በማድረግ እንዲህ የአገር ሃብት፤ የእያንዳንዳችን መዋዕለ መንፈስ እያዋከበ፤ እያመሰ፤ እያከሰረም ይገኛል።
በቀላል ቋንቋ ኮሚሽኑ ቤቢሲተር ነው የሆነው። 
 
መወሰን ያልቻለ ነፍስ፤ መኖር አልጀመረም የሚባለውም ለዚህ ነው። ይህን የመሰለ ዕድል እንዲህ ጢስ * ጠቀስ፤ መታመስ -ገብ
ያደረገው እራሱ ኮሚሽኑ ነው። መነጋገር፤ መወያዬት፤ መተያዬት መልካም ነገር ነው። ክፋ ሃሳብን የማሸነፍ አቅም አለውና። ግን መነጋገሩ፤ መወያዬቱ ጫና፤ መጠራቅቅ፤ ስጋት ከኖረው። ነፃነት ቀሚ ይሆናል። ነፃነት አልባ ንግግር #ዱድማ ይሆናል።
 
ሌላው ብልጽግና "ወጥ ፓርቲ ነው "እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የነበሩት ሁሉ አሁን ከየት ይግቡ። ወጥነት አገራዊነት፤ ወጥነት ብሄራዊነት፤ ወጥነት ህብራዊነት ማለት ነበር። ለካስ ብልጽግና የዞግ መንፈስን የሚያራምድ የማህበረ ኦነግ መንፈስ ጥላ ሥር ያለ ነበር። በአመሰራረቱም ለብለብ ብቻ ሳይሆን ኢህዴግን ያስቀጠለ ትውስታዊ ስለነበር በዚህ ልክ ዞግ ላይ #ተቸክሏል የሚል ሃሳብ አልነበረም ለብዙወች። 
 
አብን ጠንከር ያለ ቅሬታ አቅርቧል። ከአማራ የተወከሉትም ዘለፋውን፤ መቃላሉን፤ ግልምጫውን፤ መገፋቱን ችለው ደጎስ ያለ ቅሬታ
አቅርበዋል። ለኮሚሽኑ ግን የልቡን አድራሽ ኦህዴድ ሠራሽ ብልጽግና ነው እና "ልዩ ኮሜቴ አቋቋመ። " "ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም
አይቆዩ።" ጥያቄው ሽዋን ልጠቅልል፤ ኢትዮጵያን ልውረስ ነው።
 
ከንቲባ አዳነች አበቤ እኮ የኦህዴድ ብልጽግና ናቸው እኮ። ከአንድ ጊዜ በስተቀር የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ከኦህዴድ ውጪ
ሌላ ብሄረሰብ ከንቲባ ሆኖ አያውቅም። ይህ በራሱ ትክክል ያልሆነ መንገድ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዕድሉን ሊያገኝ ይገባል።
በተለይ የአማራ ህዝብ እና ጉራጌ በዚህ የከንቲባነት ቀመር ሊሳተፋ ሲገባ ተሳዳጅ ሆኑ።
 
ያ አንካሳ ሂደት #ወጌሻ ስላላገኜ ከዚህ ተደረሰ። ነገ - ደብረብርሃን፤ ነገ - ቤንሻንጉል ጉምዝ፤ ነገ ወሎ አይቀሬ ይሆናል። ስለተባለ
ሳይሆን የገዳ ባህሬ ተፈጥሮው ይህን ያስገድዳል። አዲስ አበባን በሞጋሳ ልጅነት ለመስጠት ወይንም ለመሸለም የተጋው
ኮሚሽኑ ከቱርኮች፤ ከፖርቹጊዞች፤ ከጣሊያኖች ቀደም ኢትዮጵያን ካለሟት፤ ከተመኟት ምን ተለዬ??? ምንም።
 
ጥያቄው እኮ ኢትዮጵያዊነትን አግላይ ነው። በተለይ ሳይለንት ማጆሪቲውን የረሳ ነው። ዝምታ በዝምታ ምን ይወልዳል ብሎ
ማሰብ ይገባል። ዝም ብሎ የኖረ ዶር አብይ ሲመጡ ታይቷል። ጫና ሲበዛ ሲከር መበጠሱ ሲሞላ መፍሰሱ አይቀሬ ነው።
ህዝቡ ድህነቱን ችሎ ሰላሙ ቢሰጠው፤ አገሩን ባይቀማ?
 
ውዶቹ ክብሮቹ እንዴት ናችሁ። ይመራል ብዙ ነገር። ተስፋን ይፈትናል። ምን አገባችሁ የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህ ያላገባን
ምን ያግባን? አገር እኮ ህይወት ነው። አገር አለኝ ከማለት በላይ ምን የነፍስ ስጦታ አለ??? መራራ ስንብቱን እየጠብቅን
ነው። የወለጋ አማሮች ዕጣ ፈንታ፤ የሻሸመኔ፤ የሃረር፤ የአርሲ የተዋህዶ ልጆቼ መከራ???
 
አዲስ አበባ ራስገዝነት ማበጥ ያመጣል፤ አዲስ አበባ የፌድራል ተጫኝ አለባት፤ አዲስ አበባ ክልል ግን አንፃራዊ
ነፃነት ይኖራታል። ምርጫዬ ይህ ነበር። በአናሳ ድምጽ በኮሚሽኑ ሴራዊ መንገድ አማራጭ አልባ ሁነት ተፈጠረ።
ያሳዝናል። በሱባኤ ላይ አገር የሚያሳጣ ሙግት። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
21/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። 
 
" የአዲስ አበባ ጉዳይ አላግባባ ያሉ ጉዳዮችን ለማየት በተቋቋመው የክልል ምክር ቤት ጉባዔ ውይይት ሲደረግበት ውሏል
አከራካሪ የሆነው የአዲስ አበባን ጉዳይ በተመለከተ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለውሳኔ ሰጪው አካል ለሚያዘጋጀው የተጠቃለለ ምክረ ሐሳብ እገዛ የሚያደርግ አዲስ ኮሚቴ መዋቀሩ ታወቀ።
 
ኮሚሽኑ ይህን ኮሚቴ ያዋቀረው 120 አባላት ያሉት የአጀንዳ አጠናቃሪዎች ቡድን፣ ትላንት ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለስምንቱ የ500 የሥራ ቡድን ያቀረበው የተጠቃለለ ምክረ ሐሳብ ከተነበበ በኋላ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ከኦሮሚያ ክልል ተወካዮች በቀረበ ቅሬታ መሠረት ነው። 
 
ኮሚሽኑ ኮሚቴውን ያዋቀረው፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባዎች በተገኙበትና ከ330 በላይ አባላት ባሉት አላግባባ ያሉ ጉዳዮችን እንዲያይ የተቋቋመው የክልል ምክር ቤት ጉባዔ ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት ከተካሄደ በኋላ በተደረሰ ውሳኔ ነው።
 
የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች በ500 የሥራ ቡድን ከመግባባት የተደረሰባቸውን ምክረ ሐሳቦች በሚያጣጥመው 120 አባላት ባሉት ቡድን፣ የአዲስ አበባ ሕጋዊነት ጉዳይን በተመለከተ በቀረበው ምክረ ሐሳቦች ላይ ቅሬታ ማቅረባቸውን የክልል ምክር ቤት ጉባዔ ውይይት ተሳታፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል።
 
ቅሬታው አዲስ አበባ የፌዴራል አካልና የኢትዮጵያ ዋና መቀመጫ ትሁን የሚለው ምክረ ሐሳብ እንዳለ ሆኖ፣ የኦሮሚያ ክልል ዋና መቀመጫ መሆኗ በሕገ መንግሥቱ ይደንገግ የሚለው ምክረ ሐሳብ መካተት አለበት የሚል ነው።... 
 
🔗 ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/159336/
----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ↠ bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር ↠ bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም ↠ bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ bit.ly/3Ruxsyv
ትሬድስ ↠ bit.ly/466VBCG
🧾 የስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
📢 የጨረታ ማስታወቂያዎች ↠ ReporterTenders.com
📩 ለዜና ጥቆማ እና መረጃ፡ news.tips@ethiopianreporter.com
✍️ ነጻ ፕሬስ፣ ነጻ ሐሳብ፣ ነጻ መንፈስ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።