ሰሞናቱ ለረ/አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን እንዲሆን በጸሎት እንትጋ!
እንኳን ደህና መጡልኝ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዛብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ አማኑኤል ዛሬ እና ሰሞናቱን አንድ የተባረከ ነገር እንዲያደርግልን እማጸነዋለሁኝ። ይርዳን አንድዬ! ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.01.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። የተባረከ አሜን ለተባረከ ትውልድ! ዛሬ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲዊዘርላንድ እንደሚመጡ ዜና አዳምጫለሁኝ። እመኛው እሻው የነበረ ቀን ነው። እዚህ አንድ ውድ የሆነ የኢትዮጵያ ጀግና አለን። ይህ ጀግና ጀግንነቱ በተግባሩ ብቻ ሳይሆን በሰብዕናውም ጭምር ነው ። ስለ አገሩ አብዝቶ ያስባል፤ ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ በበዛ ሁኔታ እስኪገርመኝ ድረስ ይጨነቃል። በፈጣሪው እጅግ ያምናል አብዝቶ ይጸልያል። በባህሪው ጨዋ ወልዶ ጨዋ ያሰደገው ከመልካም ቤተሰብ የተፈጠረ፤ አሳዳጊውን ይባርከው የሚያሰኝ ነው። በመልካም ቤተሰብ በጥንቃቄ ያደገ ወጣት በመሆኑ በሁለመናው እጅግ ቁጥብ ነው። ብዙ የማይናገር፤ ብዙ የማይል፤ ብስጭት የሌለበት በፍጹም ሁኔታ የተረገጋ ወጣት ነው። ስላደረገው ብሄራዊ አር ያነት አብነት ያለው ብጡል ብሄራዊ የጥቁር አንበሳ ገድል እና ወጣትነቱን ሳይሳሳ የማገደበት፤ ህይወቱን የሰዋበት መንገዱን በፍጹም ሁኔታ ይህን በማድረጉ እና ነፍሱን ችግር ውስጥ ማስገባቱ የማይ...