ቢራቢሮ ሥነ - ግጥም። የምወዳትም።
ቢራቢሮ ... *** „የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጠላል።“ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 15.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ቢራቢሮ። ነይ እሰኪ ዘንድሮ አለፈልግም ከርሞ የለኝም አርምሞ ሁለመናዬ አሮ በበቀል ተነክሮ ቀለም የለሽ ኑሮ፣ ቋሳ ተዘርሮ መብቴ ተዘሮ ሁኛለሁ ደንቆሮ። አንቺ ቢራቢሮ ሕይወት ቢራቢሮ ኑሮ ቢራቢሮ ነፍሴ ቢራቢሮ ተስፋ ቢራቢሮ አትሁኝ በረሮ አታፍቅሪ ጦሮ። ነጠብጣቤ አሮ ...