ይበቃል ግጥም።

ይበቃል።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
15.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


ይበቃል
         ***
የምን ሽላሽሊውት? የምን መጓተት?
ጨዋታው ይበቃል አትዋትት።

ለአንተ ሲዘንብልህ፣ ለእኔ ያካፋል
የሁሉ ፈጣሪ እኩል ያድላል።

ያፈለቀልኝን የራሱን ሰላም
ያለ ጊዜ መጥተህ አስመነንክብኝ።

ጠምቶኝም አያውቅም ምንጩ ከሆ ነው፣
ከአንተ ጋር መራኳት ጊዜ መግደያ ነው።

ቲፍ ብሎ ሞልቶ አንገቴ ድረስ
ዕብለት ሃሞት ሆኖ ልቤን አስነከሰ።

የምመካው እኔ በአንድዬ ብቻ ነው፣
የአንተማ ክንብንብ፤
ሽፍንፍን-ድፍንፍን
 ውስጠ ወይራማ ነው!

   ሽበት ምን ያደርጋል? ...
... ከአናት ላይ መውጣቱ?
ከአልሰገደ በቀር ለወስጠ-ህብስቱ።

ክብር ነው ሞገስ፤ ደረ መገኘት
ቃል ሕይወትን ዘርቶ ጃኖ ሲሰራበት።
ቅልጥ ያለ ቤቱ በጣም የሚያምር
ውስጡ ግን አመዳም ለዛቢስ ፈረፈር።

እንብኝ አሻፈረኝ አልሻም ብያለሁ
የካራንን ህብረት፡ ....
... 80 ቀኔ ----ም፤ አለሁ።

ከዘለዓለም ቤቴ --- ስገባ፡
መድህኒቴ አገኘሁ
  የተስፋ ዘበኛ።

ይቅር ባዩ ጌታዬ ምህረቱን ይልካል
ወራዳን ሕሊናን እሱ ያጸዳዳል።
 
ሥርዬት እያለ እኔ መጨነቄ
በፍትሃት ይጸዳል መጨመላለቄ።

በቃሽም ይለኛል እሱ ያለ ለታ
ተሰፋዬ እያለ ዬኔሁን መከታ።
                                                      

  • ·       ተጣፈ ሚያዝያ 17/2001 ... ሄርሽን ሆቴል
  • ·       ተስፋ መጽሐፌ ላይ ገጽ 13 ለህትምት የበቃ።


ውዶቼ በዛን ጊዜ ስሜቴ ውስጥ የተፃፈ ነው። ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
   


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።