ልጥፎች

ከፌብሩወሪ, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የለወጥ ሃሳብ እና ዘመነ ኦሮሙማ ...

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ማክሰኞ ዕለተ ተናኜ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   የለውጥ ሃሳብ።           የለውጥ ሃሳብ ሂደትን                 ማዕቀብ በመጣል ማስቆም                ወይንም የታቆረ ማድረግ                 አይቻልም። በፍጹም።                 ተፈጥሯዊ ነውና!   „በታካች ሰው እርሻ፤ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን   ቦታ አለፍሁ። እነሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፤ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል። የድጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“    (መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴፩) ·        በር።   ለእኔ በማሰብ ልቅና የአስተሳሰብ ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ። የነቃው የህሊና ክፍል አዲስ ሃሳብ ሲያፈልቅ ሃሳቡን የሚቀበል ህሊና፤ አዕምሮ ሊኖረው ይገባል። ይህ አዕምሮ ያፈለቀውን አዲስ ሃሳብ የሚመጥን የሰብዕና አቅም የሚኖረው ከአቅሙ ከራሱ በመመንጨቱ ነው።   አዲሱ ልቅና ያለው አስተሳሰብ/ ሃሳብ የትውስት ወይንም የብድር አይደለም። ስለምን? አዲሱ ዬአስተሳሰብ ልቅና ካለው ከራሱ ህሊና፤ የአዕምሮ የአቅም ፏፏቴ የመነጨ ስለሆነ ዲስፕሊኑን የመሸከም ብቻ ሳይሆን በቅጡ አደራጅቶ የመምራት፤ የማስተዳደር አቅሙ ተመጣጠኝ ነው።   .. ብቻም ሳይሆን ሚዛናዊነቱ በራሱ የአዕምሮ የውሃ ልክን የሚያስጠብቅ ተጠባባቂ የሃሳብ ማህበር ዘብም ይኖረዋል። ይህን ሃሳብ ከአቶ እስክንድር ነጋ የባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ የመነሻ መርህ የካቴና ስንቅነት፤ እና በዬዘመኑ የአዲስ አስተሳሰብ ባለቤት ከሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው የማፈለቅ አቅም ኳራንቲ መግባት ጋር እስኪ አስሉት።   እንደገናም የማህበ