ልጥፎች

ከጃንዋሪ 26, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል::

የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል:: "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 አስቸኳይና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡ ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝብና አሕዛብን፣ ሰውና መላእክትን፣ ፍጡራን እና ፈጣሪን ይልቁንም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ልዩነት አጥፍቶ የሰው ልጅ ሁሉ በቋንቋ፣ በቀለምና በጐሣ ሳይከፋፈሉ በአንድነት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ የተወለዱ በማየ ገቦ የተጠመቁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲሆኑ ልዩነት የሌለባትን ዘለዓለማዊት መንግሥተ እግዚአብሔር እንዲወርሱ በደመ ክርስቶስ የተመሠረተች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የተነሣባትን ፈተና ሁሉ አልፋ ከእኛ ዘመን ደርሳለች፤ ምንም እንኳ ከቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ ከኦርቶዶክስ ትምህርተ ሃይማኖት ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን በጐሣና በቋንቋ የመለየት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንግዳ ክስተት ቢሆንም ቤተ ክርስቲየን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጠባይዋ በተለየ፣ ታሪኳንና ሥርዓቷን በማይመጥን፣ ከሕግ መንፈሳዊ፣ ከሕግ ጠባይአዊ እና ከሕገ አእምሮ በወጣ መልኩ የደረሰባት ጥቃት፣ እና የመፈንቅለ ...

ዬዋለ - ያደረ - ቀድሞ የታቀደ - ወረራ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከ2010 - 2015። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ #አትበዬድም። ፈፅሞ።

ምስል
  ዬዋለ - ያደረ - ቀድሞ የታቀደ - ወረራ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከ2010 - 2015። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ #አትበዬድም ። ፈፅሞ። #የአቡነ ሳዊሮስ ጉዞ አሪወሳዊ ነው። መፈንቅለ ኢትዮጵያ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት ባጃችሁ ክብሮች። ለእኔ አዲስ ነገር የለውም። ያስደነገጠኝ ነገር ዬለም። ለምን? ምክንያታዊ ስለሆነ። ዬዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ በውል ስለተገነዘብኩት። ኢትዮጵያ መፈንቅል እንደ ተካሄደባት አምስት ዓመት ሙሉ ላልተገለጠል ይህ መቀስቀሻ ይሆንለታል። እንጂ በኢህአዴግ ኦነግ መፈንቅል አካሂዷል። በስልት እያለዘዙ ሲያጓጉዙ ባጅተዋል። የሆነ ሆኖ ……… 1) ዬዘመኑ የዬፖለቲካ ባህሪን ገና ከጥዋቱ አቋም ስለያዝኩበት አልደነግጥም። ዬሚሆነው የሚሆነው ከሥርዓቱ ባህሪ ነው። የገዳ ታሪክ ጽልመት ነው። ድሉ በደም ዋንጫ ዬቀለመ ማፍረስ፤ ማቃጠል፤ ማውደም። ስንቁ ቀውስ። ዬሚገርመው ዬዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ ከዶር አብይ አህመድ የሥልጣን ሱስ ቀለም ነው በማለት የሚተነትኑ አሉ። "ዬተረኝነት" ዬሚሉትም አሉ። ይህ መሰል አዝለኝ ቁጭ አድርጎ እዬነዳ ናደ። አሉታዊ ዴሞግራፊን ዕውን ላደረገ ሥርዓት ማስታመሙ የመከራ ማባዣ ነው። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አፈጣጠር እና ውድቀቱ መነሻው አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው። መስፋፋት፣ ወረራ፣ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን አስኳሉ ፋሺዝም ነው። ይህን በጥዋቱ አይቻለሁኝ። ስለዚህም አቅሜ አይባክንም። መንፈሴም አይናወጠም። ተከታዮቼንም በሰከነ መስመር ይጓዙ ዘንድ አስተምሬያለሁ። ያባከንኩት ጊዜ የለም። በአደብ ማጥናት፤ ማዳመጥ ሲያሰኜኝ ጊዜ ወስጄ ጥሞና ዕወስዳለሁኝ። ላንካካ ዬማልሻቸው ጉዳዮች ሲኖሩም ተከታዮቼ መንፈሳቸው እንዳይጎዳብኝ ዝም እላለ...

እዮባዊቷ ቅድስታችን።

ምስል
እዮባዊቷ ቅድስታችን። በማዕከላዊ መንግሥት ሁነኛ ልጅ የሌላት እናታችን። አባቶቻችን ቅድስና አላነሳቸውም። አቨው ልቅና አልጎደለባቸውም። ብፁዓን መንፈሳዊ ፀጋ አልሳሳባቸውም። ደናግላን ገሃዳዊ የቀለም ትምህርትም አልነጠፈባቸውም። ሁሉም አላቸው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   አንዳንድ ነገር አዳመጥኩኝ። ቀረ፣ ጎደለ ስለሚባለው አመክንዮ። ግፍ ነው። በጣም። እርግማን እንዳይሆንም ፈጣሪ ይርዳን። አሜን። ብፁዑ አቡነ ኤርምያስ የሠሩት ገድል በቂ ነው፣ የማስተዳደር፣ የመምራት፣ የማደራጀት፣ የርህራሄ ክህሎታቸውን አይተንበታል። ይህ ሁሉ ሰርክ በግብረ ሰላም ዬሚሽሞነሞነው ዘመነኛ ባለስልጣን ሁሉ የሳቸውን ሲሶ ያክል አቅም ቢኖር የሚሊዮን ደም እና ዕንባ በቅድስት አገር ኢትዮጵያ ምድር ባላጎረፈ ነበር። በብዙ እኮ ተዋርደናል። አንገታችንም ተደፍቷል። ዬእኛ አባቶች ተረጋግተው ጥሪያቸውን እንዳይከውኑ ዘጠኝ አብያተ ቤተ ክርስትያናት በጅጅጋ በማቃጠል፣ በማንደድ ነበር የአብይዝም ዘመን አህዱ ያለው። ብፁዑዓኑ አበው አንድም ወር፣ አንድም ወቅት፣ አንድም ሳምንት፣ አንድም ዓመት፣ አንድም ጊዜ ከወከባ እርፍ ብለው ተረጋግተው የአደባባይ በዓላትን ያከበሩበት ጊዜ አልነበረም። አስተዳደራቸውን ሰክነው ለመምራት አልታደሉም። እነሱን የሚዋጋ የሰለጠነ ሾተላይ ዘመን ላይ ነውና የባጁት። በርካታ ቤተ መቅደሶች ሹግ ሆነዋል። ማህበረ ምዕመኑ፣ ማህበረ ካህናት እስከ ቤተሰቦቻቸው ሰማዕትነት በተለያዬ ጊዜ ተቀብለዋል። ሰብሳቢም የላቸውም። አጥቢያ አድባራት ዬፈረሱት ፈርሰው፣ የቀሩት ተዘግተዋል። ማህበረ ምዕመኑ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በሃዘን፣ በዕንባ፣ በዋይታ ዬከተመ ዘመነ ምፅዓት። እንደዚህ ዘመንም በርከት ባለ ሁኔታ ብፁዑ ቅዱሳን ጳጳሳት በሥጋ ዬተለዩን ዘመን የለም። አ...

ዬኦሮሞ ልጆች በጥዋቱ ዕውነትን ወግነው ቁመዋል። ህወሃት 27 ዓመት ያን ሁሉ ማት ሲያወርድ ይህን መሰል የተጋሩ ሊቃናት ሲጋፈጡ አላዬሁም።

  ዬኦሮሞ ልጆች በጥዋቱ ዕውነትን ወግነው ቁመዋል። ህወሃት 27 ዓመት ያን ሁሉ ማት ሲያወርድ ይህን መሰል የተጋሩ ሊቃናት ሲጋፈጡ አላዬሁም። የኦሮሞ ልጆች ግን በግል የሚሰማቸውን ሳይቀር ገና በጥዋቱ ነው ፊት ለፊት ወጥተው የተቃወሙት። በአገራቸው በኢትዮጵያ ያላቸው ውስጥነት እራሳቸውን ማግደው ነው የሚታገሉት። ዛሬ ብቻ አይደለም። ባለፋት የመከራ ዓመታት ሚዲያ ያገኙ እህት ወንድሞቻችንፊት ለፊት፣ ገጥ ለገጥ ወጥተው ይቅርታ ሁሉ ጠይቀዋል። እስከዚህች ቀን ድረስ ከተጋሩ አልሰማነም። አሁን እንኳን በኦህዴድ እዬተቀጠቀጡ ሞት የተፈረደበትን አማራን ሲከሱ ውለው ያድራሉ። ይህም ብቻ አይደለም በመተማ፣ በሁመራ ከሱዳን ጋር የሚያጠፋት ጥፋት፣ በጦር ባጠቁት ዬአማራ፣ የአፋር ላደረሱት ጥፋት ውግዘትም፣ ፀፀትም ዬለም። 30 ዓመት ሙሉ። የኦሮሞ ሊሂቃን ግንፊት ለፊት የወጡት ማልደው ነው። በቅድስት ተዋህዶ ፈተናም በጥንካሬ፣ በብርታት እዬሞገቱ ነው። ዝንፍ አላሉም። እዬተከታተልኩት ነው። ውስጣቸው ሲነድ ይታያል። እንደ አንድ አደራጅ እኔ ያዬሁት ይህንዕውነት ነው። ይህ ተው ኢትዮጵያዊነት፣ አገራዊነት፣ ብሄራዊነት። " ዬቤትህ ቅናት በላኝ። " መልካም ምሽት። ዬጠነከረ ዬተደሞ ጊዜ እመኛለሁኝ። ሥርጉትሻ አገልጋይ። • https://www.youtube.com/watch?v=8NMi8JjO_Pw ሰበር ዜና የኦሮሞ ተወላጅ የሆነችው ሜቲ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዘረኝነት እና ተረኝነት በአደባባይ አጋለጠች ! • https:...