ዬዋለ - ያደረ - ቀድሞ የታቀደ - ወረራ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከ2010 - 2015። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ #አትበዬድም። ፈፅሞ።
ዬዋለ - ያደረ - ቀድሞ የታቀደ - ወረራ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ከ2010 - 2015።
ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ #አትበዬድም። ፈፅሞ።
#የአቡነ ሳዊሮስ ጉዞ አሪወሳዊ ነው። መፈንቅለ ኢትዮጵያ።
እንዴት ባጃችሁ ክብሮች። ለእኔ አዲስ ነገር የለውም። ያስደነገጠኝ ነገር ዬለም። ለምን? ምክንያታዊ ስለሆነ። ዬዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ በውል ስለተገነዘብኩት።
ኢትዮጵያ መፈንቅል እንደ ተካሄደባት አምስት ዓመት ሙሉ ላልተገለጠል ይህ መቀስቀሻ ይሆንለታል። እንጂ በኢህአዴግ ኦነግ መፈንቅል አካሂዷል። በስልት እያለዘዙ ሲያጓጉዙ ባጅተዋል።
የሆነ ሆኖ ………
1) ዬዘመኑ የዬፖለቲካ ባህሪን ገና ከጥዋቱ አቋም ስለያዝኩበት አልደነግጥም። ዬሚሆነው የሚሆነው ከሥርዓቱ ባህሪ ነው። የገዳ ታሪክ ጽልመት ነው። ድሉ በደም ዋንጫ ዬቀለመ ማፍረስ፤ ማቃጠል፤ ማውደም። ስንቁ ቀውስ። ዬሚገርመው ዬዘመኑን የፖለቲካ ባህሪ ከዶር አብይ አህመድ የሥልጣን ሱስ ቀለም ነው በማለት የሚተነትኑ አሉ። "ዬተረኝነት" ዬሚሉትም አሉ። ይህ መሰል አዝለኝ ቁጭ አድርጎ እዬነዳ ናደ።
አሉታዊ ዴሞግራፊን ዕውን ላደረገ ሥርዓት ማስታመሙ የመከራ ማባዣ ነው። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አፈጣጠር እና ውድቀቱ መነሻው አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው። መስፋፋት፣ ወረራ፣ አስምሌሽን እና ዲስክርምኔሽን አስኳሉ ፋሺዝም ነው። ይህን በጥዋቱ አይቻለሁኝ። ስለዚህም አቅሜ አይባክንም። መንፈሴም አይናወጠም። ተከታዮቼንም በሰከነ መስመር ይጓዙ ዘንድ አስተምሬያለሁ። ያባከንኩት ጊዜ የለም። በአደብ ማጥናት፤ ማዳመጥ ሲያሰኜኝ ጊዜ ወስጄ ጥሞና ዕወስዳለሁኝ።
ላንካካ ዬማልሻቸው ጉዳዮች ሲኖሩም ተከታዮቼ መንፈሳቸው እንዳይጎዳብኝ ዝም እላለሁኝ። በእኔ ልክ ተረዱት፤ አቋም ያዙ ብዬ መጫን አያስፈልግም። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው ያጠራዋል። ማን ምን እንደ ሆነ። ዬገፊ ኃይሉ መጣበቅ እና መዘዙም ዘመን ያንተረትረዋል።
ስለዚህ ማንኛውንም ክስተት ቁመናውን እምመዝነው ከዚህ አንፃር። ተገነባልኝ ብሎ የሚጨፍረው እዬተናደ ስለመሆኑ፣ እዬተነቀለ ስለመሆኑ አይታዬውም። ቀጥ ያለ መሠረት ያለው ግንዛቤ የጠራ የፖለቲካ ተጋድሎ ይጠይቃል።
ከደቂቁ እስከ ግዙፋ ብሄራዊ ጉዳይ ድረስ ሁሉም የህልውና አደጋ ላይ ነው። ግን በዚህ ልክ የመንፈስ ዕውቅና የመስጠት አቅሙ ዬለም። ለብ ለብ ነው ነገር አለሙ። የለማወአብይ መንፈስ ሥራውን እዬሠራ ነው። መደናቀፍ ዬለም። መሠረቱን የጣሉት ዶር ለማ መገርሳ ናቸው። አፈፃፀሙን በኢትዮጵያዊነት እያማለሉ ዶር አብይ ከብርኃን በቀደመ ፍጥነት 50 ዓመት ኦነግ ያነኮረውን ዕውን እያደረጉት ነው። ያውም እራሱን ለማፍረስ በፈቀደ ሚሊዮን መንፈስ ተደግፎ።
2) በቤተክርስትያናዊ ጉዞም ዬቀደሙ ዬተከወኑ አውራ ጉዳዮች ነበሩ። ለቅኖች ስገልጽላቸው ቆይቻለሁኝ። ለዚህም ነው በጽናት ከጽኑው ፓትርያርከ ዘ ኢትዮጵያ ብፁዑ ወቅዱስ አባ ማትያስ ጎን በጥዋቱ የቆምኩት። ቅንነታቸው ገና ያልተተረጎመ አመክንዮ ነው። ለእኔ የተገለጠልኝን ያህል ለሌላው ተገልጦለታል ብዬ አላምን። የፀዳ ቅንነታቸው ተቋሜ ነው።
……ሂደቱ እንዲህ ነበር።………
2.1 ዶር ለማ መገርሳ አውሮፓ ያሉትን የኦሮሞ ወገኖቻቸውን እዬተዘዋወሩ ያሰባስቡ ነበር። እኢአ በ2010።
2.2 በዶር አብይ አህመድ አሊ ዬተመራው የስሜን አሜሪካ ቲም ዋና ተልዕኮው የኦሮሞ ሊሂቃንን፣ ሊቃናትን ማሰባሰብ ነበር። ከሚስጢራዊ ስብሰባው ወ/ት ብርቱካን ሜዴቅሳም አሉበት።
በዚህ ውስጥ አብረው ስብሰባ ላይ ይገኙ አይገኙ ባላውቅም የአሁኑ "የኦሮምያ ፓትርያርክ ምድብ ውስጥ" አቡነ ቀስጣጢወስ ቲም ለማ በአካል አግኝተዋቸዋል ብዬ አምን ነበር። ማግኜት ብቻ ሳይሆን ቀጣዩ ፓትርያርክ እንዲሆኑም አወያይተዋቸዋል ብዬ አምናለሁኝ።
#ከተሳሳትኩ እታረማለሁኝ። የምለው ስለ አቡነ ቄስጣጢወስ ነው።
2.3 ዬዕምነቴ መሠረቱ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ አቡኑ ቄስጣጢወስ በዘመነ ቅንጅት ለአጣሪነት ከተመረጡት ከእነ ዳኛ ፍሬህይወት ሳሙኤል ጋር ዬነበሩ ናቸው። ብዙ ተጋድሎ እንዳደረጉ አዳምጫለሁኝ። ሚዛናዊ ዕይታቸውን አዳምጫለሁኝ።
አሜሪካን አገር ይኖሩ ነበር። በቃለ ምልልሱ እንደ ተረዳሁት ዬውጩም፣ የአገር ውስጡም ሲኖዶስ ደጋፊ አልነበሩም። እኔ በተረዳሁት ልክ ዝንባሌያቸው የማዕከል ይባል ከነበረው ይመስለኛል እሱንም በስሱ።
ከዛ ወደ አገር እንዲገቡ ዬተደረገው ቅዱስ ሲኖዶስ የውጩ አገር ከገባ በኋላ ብቻቸውን በታዋቂ ሰወች ደረጃ ከፍ ባለ ማዕረግ ነበር።
ወደ አገር ከመግባታቸው በፊት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢሳት ስትዲዮ ዘለግ ያለ ቃለ ምልልስ ለአቡነ ቄስጣጢወስ አድርጎላቸዋል። ያን ጊዜ በጨመተው ሰብዕናው ልክ ቃለ ምልልሱ በላቀ አክብሮት እና ደረጃው ከፍ ባለ ሁኔታ ነበር ያደረገው። ያ ለእኔ አንድ ግብረ ምላሽ አበረከተልኝ። ጎን ለጎን የታቀደው ተግባር አለ እንድል።
እማስታውሰው በቃለ ምልልሱ በመጨረሻ እስኪ በኦሮምኛ ቋንቋ መልዕክት ያስተላልፋ ብሎ ጠዬቃቸው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና። ለእኔ ተርኒግ ፖይንቴ ያ ሂደት ነበር።
2.4 ከዛ በከበረ የአጓጓዝ ሥርዓት ኢትዮጵያ ገቡ። ሲገቡ እጩ ፓትርያርክ የመሆን አቅም ያለው #ዬተመሰጠረ ተደሞ ነበረው ብዬ አምናለሁኝ።
2.5 ዬ2011 ዓ.ም ዬጥር ጥምቀት ሁለት ፓትርያርክ ባለባት ኢትዮጵዬ ቡራኬ ለጥምቀት ዬሰጡት እሳቸው ነበሩ።
በወቅቱ አባይ ሚዲያ ዘገበው። እኔ ደግሞ አናርኪዝም ጉዞ በአህዱ አለ ብዬ ብሎጌ ላይ ፃፍኩት። ከውስጤ እከታተለው ስለነበር።
እኔ ከኢንጂነር ስመኜው በቀለ ህልፈት በኋላ ዬቲሙ ጉዞ ገደል ሊሆን እንደሚችል ለተስፋችን ተርጓሚ አላስፈለገኜም ነበር። ዬአባይን ታሪክ በእጅ ለማስገባት ስለመሆኑ ግልጽ ነበር ለእኔ። ከዛ በኋላ ቅንጣት አቅም አዋጥቼ አላውቅም። በትውልድ ግንባታ በማያቸው መልካም ነገሮች ካልሆነ በስተቀር። አቅሜ ቁጥብ ነው።
እጩ ፓትርያርኩን ብዙም ፊት ለፊት አያወጧቸውም። ግን ድፍን አምስት ዓመት ሙሉ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዬደረሰው መከራ እሳቸውን ፓትርያርክ ለማድረግ የታሰበውን ለማሳካት የቅጣት ጊዜ ነበር።
ጫናው፣ ሰማዕትነቱ ለሳቸው መንበረ ፕትርክና ነበር። እሳቸውም ያምኑበታል ብዬ አስባለሁኝ። እርግጥ ከአቡነ ቄስጣጢወስ ወደ አቡነ ሳዊሮስ እንደተዛወረ አላውቅም። ይህ አዲስ ክስተት ነው።
3. የፃድቁ ብፁዑ ወቅዱስ አቡነ መርቀርዮስ እረፍተ ሥጋ በፈጣሪ የሚመረመር ሆኖ ለተመሰጠረው መፈንቅለ ሲኖዶስ ግን ድልዳል ይሆን ዘንድ ዬታለመ ነው።
ዬጽናት አባቴ ብፁዑ ወቅዱስ የቁም ሰማዕቱ አቡነ ማትያስ ከብረት ቁርጥራጭ ዬተሠራ ሰማያዊ ጽናት፤ አይበገሬንት ሌላ አማራጭ እንዲያስቡ ግድ ብሏል። እንጂ አስቀድመው ነበር ቦታውን ያጩት። ቲም ለማ ስሜን አሜሪካ ዬሄደው ግዙፋ ፕሮጀክቱ ይህም ነበር። በውጭ የነበረው ቅዱስ ሲኖዶስ አቅሙ አይደፈሬ ነበር።
4. በማስተዋል ላላችሁ ወገኖቼ የማሳስባችሁ ሁልጊዜ ደቡብ ክልል ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሲንቀሳቀሱ አቶ ሽመልስ አብዲሳ አብረው መሄዳቸው ደቡብን ስለመጠቅለላቸው ያመሳጥርልኛል ብዬ በተደጋጋሚ ገልጫለሁኝ።
አሁን የሹመቱን የሥራ ድልድል ሳዳምጥ አዲስ አልሆነብኝም። ደቡብም ታክሏል። ምስራቅ፤ ምዕራብም እንዲሁ። ምክንያቱም ደቡብ ሙሉው ወደ ኦሮምያ በቁሙ ተውጧል። ቀሪውን የጫካው ክንፋቸው ያጠቃልለዋል። በመንፈስም ከአዲስ አበባ ጀምረው ግዛታቸውን አጠናቀዋል። ዬአሁኑ የስሜን ሽዋ፤ የከምሴ ጦርነትም በአራት ኪሎ መንግሥት የሚመራ ነው።
ዬሚገርመኝ የሊሂቃኑ መደንዘዝ ነው። ዬመንግሥት ካቢኔው በሙሉ በኦነግ ተይዞም ታቱ የሚል መንፈስ ዬለም። ንቅናቄ የለም። ስንት ጊዜ የካቢኔ ሹም ሽር ተደረገ? ግርዶሹ እኮ እያለማመዱ መጠቅለል ነው።
በድጋሚ እማስገነዝበው በሰሞናቱ የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፁሁፍ አይቻለሁኝ። እግዚአብሄር ቢፈራ እላለሁኝ። ልብ እና ኩላሊትን ዬሚመረምር አምላክ ስላለ።
የውጩ ሲኖዶስ በነበረ አቅሙ ቢቀጥል ቅድስት ተዋህዶ ይህን ያህል አትደፈረም፣ አትዋረድም፣ ሰማዕት አትሆንም ነበር። ጥድፊያው ልክ እንደ መከኑት የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ለማድረግ ታስቦ ነው።
ግን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብይ ሠራሽ አይደለችም። በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ የፋንታዚ ዳንቴል #እምትበዬድ አይደለችም።
ምክንያት ሰማያዊ ክብሯ ዬመንፈስ ቅዱስ ርባቤ፣ የቅዱሳን ይባቤ፥ የፈቃደ እግዜብሔር ቅባዕ ስላላት። ምን አልባትም በሠው ሠራሹ ምድራዊ ኩነት የተከፋ የተዋህዶ ልጆች አህቲነት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበራበት ብሩህ ዘመን ይሆናል። በተለይ ለስሜን ሊቃናት የደመ ነፍስ ሩጫ ሰማያዊ ሐዋርያ ሊሆንላቸው ይችላል። አንዱን ይዞ ሌላውን አንጠልጥሎ ስለሆኑ። ግንድነታቸውን በፈቃዳቸው ደርምሰው በጭፍጭፍጫፊ ስለሚጨፋጨፋ። ፀፀትም ስላልሠራላቸው።
ትናንትም፣ ዛሬም፣ ወደፊትም እኔ ከሰማዕቱ አባቴ ከብፁዑ ወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ፃድቁ አባ ማትያስ ጎን ነኝ። ማንኛውንም መከራ ከጎናቸው ቆሜ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። አባ አባት ዓለም ይፍቱኝ።
ሌላ አደባባይ ሚዲያን በብርቱ ጠብቄው ነበር እስከ አሁን ምንም አላለም። EMS ትናንት እሁድ ነው አልነበረም። ዛሬ እጠብቃለሁኝ። አቤ ቱኩቻው አዲስ አጀንዳ ጋር ይንከላወሳል። ደሬ በድፍረት እዬሞገተ ነው። አንከር ሚዲያም ዘገባው ላይ አተኩሯል።
ሥጋ ነፍስ ፍትጊያ ላይ ናቸው። ዬእግዚአብሄር ፈቃድ ዕውን ይሆናል። የቀደመችው አህቲ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ታሸንፋለች። ጽኑ፤ የቆረጡ አቨው ቅዱሳን ስለሰጠን አምላካችን እናመሰግናለን። በፀሎት እንረዳዳ።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እንኳን እያሉ ይህቺ ዓለም በቃኝ ስትላቸውም እሳቸውን አውቆ መተንበይ ጋዳ ነው። ለእኛ ብቻ አይደለም። አደጋው ለዓለምም ነው። አሳቻ ናቸውና።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/01/2022
የቤተ እግዚአብሄር ቋንቋ እጬጌው ግዕዝ ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ