ሂደቱ ዬ5 ዓመታት መሰናዶ ነበር።

ሂደቱ ዬ5 ዓመታት መሰናዶ ነበር።
ብጹዑ አቡነ ቀውስጦስ (ዶር) አገር ሲገቡ ቃለ ምልልስ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ተደርጎላቸው ነበር። ልዩ ሁኔታ ነበረው። ዛሬም ዬእሱን ዕይታ ሳደምጠው ያን ጊዜ እጠረጥር በነበረው ልክ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ዬገዘፈ መከራን ያዘለ ነው። ትናንት ሳዳምጠው «ከህግ ውጪ ዬወጣን ነገር በህግ ብቻ መፍታት አይቻልም» በማለት ማስፈራራት፤ መጫን፤ ትዕዛዝ መሰል ዕይታ ሲቃርብ ጨርሼ ማድመጥ ተስኖኝ አቋርጬ ወጣሁኝ።
እሰሩ ሲል ሲታሰርለት። ፍቱ ሲል ሲፈታለት አፈ ካቢኔ ሆኖ ባጅቷል። አሁን ቀድሞ በሰራው እጅ ሥራ ደግሞ በድፍረት ሲናገር ሰማሁት። ቀደም ባለው ጊዜ ዬበዛ ክብር ስለነበረኝ ስሙን ብዕሬም ብራናዬም አንስተውት አያውቅም። ዬአሁኑ ግን ድፍረቱ እጅግ ገረመኝ።
ለሰማይ ለምድር ዬገዘፈች አገር በእጇ ላበጀች ቤተ ክርስትያን ይህን ያህል መጫን ዬጤና አይመስለኝም። ሌላው ቀረቶ ዬዛሬ 5ዓመት ዬነበረ ትህትና ዛሬ አላዬሁም በብፁዑ አቡነ ቀውስጦስ (ዶር) በመታብይ ብትፈጽሙ ባትፈጽሙ ውርድ ከራሴ ሲሉ ገልጸዋል። ማህከነ። እግዚዖ ተሳህለነ። ።
ጥበቃው ዬፈጣሪ ስለሆነ አንድዬ ይሁነን። አባታችን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛብዙውን ከድነው፤ አያሌውን ህፃፅ ወደ ራሳቸው ወስደውታል። እራሳቸውን ነው ዬወቀሱት ከእንግዲህ ዬሳቸውም ህይወት ጥበቃ ያስፈልገዋል። ብልሆች ቢያስቡበት ጥሩ ነው።
እሳቸው እራሳቸው ክስተት ናቸው። ማድመጥ ለመሪነት ተሰጥዖ ነው። ይህ ግዴታም ነው። በጉልህ ዬተነሳው ዬማድመጥ ችግር ነው። ዬሆነ ሆኖ ጉዳዩ ይህ አይደለም። በአገር ላይ አገር ዬመገንባት ሂደት ነው። ዬወደቁ መላዕክት እንዳሉ ሁሉ እንደ መጸሐፈ ሲራክ ሚስጢራት ይህም ዘመኑን በምድራችን በምልሰት አሳይቷል።
አሉታዊ ዴሞግራፊ በህጋዊ መልክ ዬተፈፀመባት አገር ጉዟዋ ፋሺዝም ነው። ሁሉን ነቅሎ፤ ሁሉን ጥሶ መሄድ በገሃዱ ዓለም ይቻላል። በቅድስት ተዋህዶ ግን ሉላዊ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን መሰረቷ ዊዝደም ስለሆነ አይቻልም።
በሰው ሰውኛ ዬኩሬ ውሃ ሰርቶ ቅርስ እንደማድረግ ቅለት አይደለም። ከሌሎች ዬተዋህዶ ጋር ለማነጣጠር እንኳን በጅ ዬማይሉ ልዕለ አቅም በልቅና አላት። እሷ በራሷ ዩንቨርስም ናት።
በእጅ ዬያዙት ወርቅ ሆኖ፤ ወርቅነቷ፥ ዕንቁነቷን ዬሚሸከም አቅል፤ አደብ መጥፋቱ ምክንያታዊ ነው። ዬአባታችን መመለስ ዬመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ታላቅ ዕልልታም በሰማይም በምድርም ያጎናፀፈ። ቃለ ምልልሱ የታቀበ፤ ርጋታ ዬረበበት ነበር። ብሩክ ማዕልት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
MK TV || ወቅታዊ መረጃ || "የሚሾሙኝ" እነማን እንደሆኑ እንኳን አላውቅም ነበር || መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።