ክቡር ተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ።
ለባለግርማው የጥበብ ክህሎት ለተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ ምህረቱን ይላክ አዶናይ „አሜን!“ ከሥርጉተ ሥላሴ 25.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፤ የወይራ ሥራ ቢጓደል፤ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፤ በጎችም ከበረቱ ቢጠፉ፤ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሴት አደርጋለሁኝ። ጌታ እግዚአብሄር ሃይሌ ነው። „አሜን!“ ይሁንልን! ይደረግልን! (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ከ፲፯ እስከ ፲፰) የውስጥ መስመር ... ጥበብ ዘር የላትም፤ ጥበብም ፍቅር ናት፣ ጥበብ ቅርጽ የላትም፤ ጥ...