Toni Dreher-Adenuga GNTM 2018.

ሞዴልToni Dreher-Adenuga
   አፍሪካ የውስጥ ውበት የ2018 
               የጀርመን ቆንጆ ሆና
                  ዛሬ ተመረጠች።

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)  

„ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ጥገኛለህ።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፳፭ እስከ ፳፮)
እሺ የኔዎቹ አፍረካዊነት ዛሬ አማራበት። ቶኒሻ አሸነፈች። ያሸነፈችበት ፎቶ አሁን ያሁ ለጥፎታል ግን ጥራቱ እንብዛም ስለሆነብኝ ሌሎችን መምረጥ ግድ አለኝ። ብቻ ማሸነፍ እንዴት ደስ ይላል? እንዴትስ ይደላል? ደስታ እንዴት ውብ ነገር ነው። ዛሬ ግንቦት 24.2018 እ.አ.አ አቋጣጠር ያን ረጅም ፈተና ተሻግራ አፍሪካዊቷ የ18 ዓመቷ ቶኒ ድንቅዬ የጀርመን ምርጥ ቆንጆ ሆና ተመረጠች። ቶኔ ውበቷ ውስጧም ነው። የተመረጠችው እሷ ብቻ አይደለችም አፍሪካም እንጂ። የተመረጠችው እሷ ብቻ አይደለችም ሙሉ ሞራሏ አንጂ። ይህች የ18 ዓመት ወጣት ለጋራ ሥራ ብቁነቷን በትዕግስት የጠለፈች የመቻቻልም አብነት ናት።

ቶኒ ሁልጊዜ ከፊቷ ፈግግታ የሚታይባት ፎሎቄ ወጣት ናት። ቶኒ ለካፋቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ሁሉ አጽናኝ፤ አበረታች፤ ሃይልና ጉልበት ሰጪ ጠይም ዕንቁ ናት። ቶኒ ተፈጠሯዋን ትወደዋለች። ቀለሟን ትውደዋለች። የሚሰጣትን የቤት ሥራ በአግባቡ ትክውናለች። ታዳምጣለች። ዓላማዋን ያወቀች ወጣት በመሆኗ ከጀርመንም ባለፈ ዓለም ዓቀፍ ዕድሎችን ወደፊት በስፋት እንደሚገጥማት በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ሞድ የጋራ ጉዞ፤ የጋራ ሥራ፤ የጋራ ሃላፊነት፤ የጋራ አክብሮት፤ የጋራ ክንውን የሚጠይቅ ሲሆን መቻቻልን፤ ፍቅርን፤ ትህትናን፤ ፈተናን በጽናት ማሸነፍን ይጠይቃል። የሞድ ኢንደስትሪ የዓለምን አትኩሮት እና ሚደያ የገዛ ግሎባል ተጽዕኖ ፈጣሪ የጥበብ ቤተሰብ ነው። በሞድ ውስጥ ሰብዕና እና ተፈጥሮ በህብረ ቀለማት ተውበው ዓይን የሚያሠርጉ፤ ፈግግታን የሚሸልሙ፤ ሐሤትን የሚያባብሉ፤ሰውነትን የሚያፍታቱ፤ የዛለን መንፈስን ብርታት የሚሸልሙ በርከት ያሉ ቤተ ጥበቦች በውል እና በውህደት ተስተጋብረው የሚገኙበት የመኖር ጌጥ ነው። በዚህ ኢንደስትሪ ቤተኛ መሆን ውስብስብ ግን አያያዙን ላወቀበት መጠነ ሰፊ ዕድል ያለው የኢንደስትሪ ዘርፍ ነው። ሰ ዓት ማክበር ዋናው ወሳኙ ቁልፍ ጉዳይ ነው። 
ይህቼ ወጣት ፈጣሪ አምላኳን እጅግ ትወዳለች። መጀመሪያ ውድድሩን ስትወጥነውም ቤተ እግዚአብሄር ተገኝታ ጸልያ ነበር። በውድድሩም ውስጥ ከባድ የውድድር ዓይነት ሲገጥም ሰብሰብ አድርጋ አቻዎቿን ጸሎት ታደርስና  በአሜን ህልማቸውን ለፈጣሪዋ በመታመን ታሳርገዋለች። ዋ! ቶኒሻ የእኔ ውብ፤ ድንቋ አፍሪካዊቷ ፈርጥ እንኳንም የአፍሪካ ዕንቁ ሆንሽልን። 
አሸንፋ ስትጠዬቅ መጀመሪያ „ጌታዬን አመሰግናለሁኝ። የምናገርበት ቃል የለኝም አለች።“ እኔ እራሴ የመጨረሻው የማሸነፊያ ፎቶ እስኪወጣ ድረስ ነፍሴ ተንጠልጥላ ነበር። ከአራቱ ሦስት፤ ከዛም ሁለት ሲቀሩ ተፈታታኟም የጥቁር አሜሪካዊ ዘር ያለባት በተጨማሪም የጥበብ ቤተሰብ ስለሆነች በአቀራረብ፤ በማድረክ አያያዝ፤ በውበት ፈገግታ የምትስብ፤ በቂ ተመክሮ ስላላት ፈተናውን ከበድ ነበር፤ ግን ይህቼ የጠይም አበባ ልዩ የሳቅ ልዕልት አለፈች። እንዴት ደስ እንዳለኝ።
ቶኒ ባላፉት ወራት በዚህ የቶፕ ሞዴል ውድድር ወደ ሰባት አገሮች ተዘዋዋራለች፤ አብዛኛውንም ሥራም አግኝታለች። አራት ቋሚ ሥራ አሸንፋለች፤ ዛሬ የ100 ሺሕ ኢሮ፤ የአንድ ዓመት ውል፤ የአንድ መኪና ተሸላሚ ሆናለች ሌላም ሌላም … ይህ ዕድል የወደፊት የትዳር ዕድሏን ሁሉ የመወሰን አቅም አለው። አንዱ ዕድል ሲመጣ ሌላውንም ያስከትላል። በሌላ በኩል በእንዲህ ዓይነት ሙሉ ሥነ - ምግባሯ ብቁ የሆነች አፍሪካዊት ዕንቁ አህጉሯን ታስጠራላች። ታኮራለችም። ለሌሎች የጥረት ስኬትም ናሙና ትሆናለች። አቤት እንዴት ፍንክንክ እንዳልኩኝ።

የቤት ሥራቸውን በአግባቡ የሠሩ ወላጆች እንዲህ የልጆቻቸውን እሸት በጥዋቱ ማዬት ይችላሉ። ቶኒ እኮ እጅግ በጣም አማኝ ሆና ያን የቶፕ ሞዴል የፎቶ፤ የስታይሊንግ የፈተና ዓይነት በሚገርም ትዕግስት ነበር ያለፈችው። አንድ ቀን እኔ ራሴ ሳላዬው የቀረሁት ሙሉ ፕሮግራም ነበር። በማግስቱ የእሷ ነገር ስለሚጨንቀኝ ማለፏን ጋዜጣ ላይ በጥዋቱ ተጣድፌ አነበብኩት። ስለምን? ዓለማችን ያሉ ፈተናዎች ከባድ ስለሆኑ ዓይን ፍቀድና እይ ለማለት አቅም ያንሳል። እንደ እኔ ጎንደር ተወልዶ ላደገ ደግሞ እጅግ ከባድ ነው።
ሌላው  በዬዓመቱ የሚገጥመው ፈተና የቀለም ነው። አንዲት የኦስትራሽ ወጣት ከእሷ ጋር የጋራ ሃላፊነት ተስጧት በቡድን ከሰራች በኋዋላ ከጓደኛዬ ጋር ብሰራው የተሻለ ዕድል ይኖረኛል በማለት ሁሉ በድጋሚ ዕድል ተስጥቷ ታዬች፤ ግን ቶኒን ለዛ ወሳኝ ፊርማ ብቻውን ተመረጠች፤ ከሌላ ቡድን ተጨማሪ አንዲት ሞዴል ታስፈልግ ስለነበረ ዛሬ ሁለተኛ ሆነ የወጣችውን ተፎካካሪ ሆና የፈተነቻትን ወጣት ጁሉያናን ወሰዱ። ሁለቱም በጋራ ተልዕኳቸውን በጥምረት የመረጣቸውን ድርጅት አስፈንድቀው ተወጡት።
ይህቺ ሩቅ ዓላማ ያላት ቀንበጥ አብሶ በቀለም የሚደርሰውን መገለለ ያሳለፈችው ፍቅርን በገፍ አቅንታ ነው።
ላገኘችው ዕድል የሰጠችው አክብሮት እና ዕውቅና ከዚህች ውብ ጠይም ለጋ ወጣት በዚህ ዕድሜ የሚጠበቅ አይደለም፤ አልነበረም። በጣም የሰከነች፤ የተረጋጋች እና ውስጧ ብሩኽ የሆነች፤ ቤተሰባዊ ውስጠት ያላት ወጣት ናት። ፈጠራዋ፤ የሚሰጣትን ድርሻ እንዴት አሳምራ፤ አስውባ አዲስ ነገር ጨምራበት፤ አድምቃ፤ ቀለማም እንደምታደርገው የሚገርም ነው። በዚህ ዓመት የስታይሊንግ ሆነ የኮርዮ አሰልጣኞቻቸው አንዲት የዳንስ ባለሙያ እና ዳኛ፤ እንዲሁም አንድ ሞዴል ሁለቱም አፍሪካዊ ነበሩ። ቀለማቸውም ጠይም።እሰቀድሞም ወፍ ያውጣው ውድድር ነበረ ዘንድሮ እንደ ማለት። 
በዬትም ቦታ፤ በዬትም ሁኔታ መልካምነት፤ ደግነት፤ ርህርህና፤ ጥረት፤ አግዚአብሄርን መውደድ ፈተናው ብዙ ቢሆንም ጥሎ አይጥልም። ይህቺ ፈርጥ በጣምራ ነው ያሸነፈችው። ከሁሉም ጋር ስምምነት ነበረች። ሊያርቋት የሚፈልጉትን በፍቅር ሃይል አሸነፋቻቸው። የሰው ልጅ ሁሉንም ፈተና መሸከም አይችልም ፍቅር ግን ይችላል። የፍቅር ደንበሩ ፍቅር መስጠት ብቻ ነው በልግስና።

ጥቁርነት ለሁልጊዜም አዲስ ቀለም ነው!
ጥቁርነት የዓለም ውበት ፀሐይ ነው!
የኔዎቹ ለነበረን አጭርዬ ቆራጣ ጊዜ ክልብ አመሰግናለሁኝ።
·         ሳሰብያ።
ፎቶ ከጉጉል። 

መሸቢያ ጊዜ። ኑሩልኝ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።