ልጥፎች

ከጁላይ 6, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ቤልጀም ብራዚልን አንገት አስደፋ።

ምስል
ቤልጄም ብራዚልን  አንገት አስደፋ። ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „የሚለምኑትን ሰዎች ልመናቸውን ይሰማል።“ (መጸሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፯)                                 ዛሬ ቤልጀሞች ማልዶ ነው የቀናቸው።                                ጨዋታው ግን የሞት የሽረት ያህል ነበር።   ኳስዬ ተደልቃም አሽካክታም ተወቃቅታም የሰናይ መሰረት ናት። ኳስ ፍቅር ነው። ኳስ መሻት ነው። ኳስ ደስታ ነው። ኳስ ሰላም ነው። ኳስ ኪዳን ነው ኮስ ጥበብ ነው። ኳስ መቻቻል ነው። ኳስ መከባባር ነው።  ኳስ ዕውቅና መስጠት - መቀበል - ማግኘትም ነው። ኳስ ተስፋ ነው። ኳስ ድል ነው። ኳስ ትጋት ነው። ኳስ የድካም ሥራ፤ የልፋት ውጤት ነው። ኳስ የማሰብ ችሎታ ነው። ኳስ የእግር ሥራ ሳይሆን የጭንቅላትም ነው። ኳስ ልዩ መክሊትም ነው። ኳስ ህግ  -ዳኝነት - ችሎትም ነው። ኳስ ትውልድ ነው። ኳስ የፈጠራ ሥራ ቤተሰብ ነው። ኳስ ሳቅ  ነው። ኳስ ማስተዋል ነው፤ ኳስ መልካም ነገርን መመኘት ነው ተስፋን። ኳስ ጊዜ ነው።  ኳስ ክውን ያለ ንጡህ መንፈስ ነው። ኳስ ምጥን ያለ ዕቅድ እና ግብ ያለው የመሆን ሁነኛ ነው። ኳስ ነገ ነው። ኳስ ሃብትነቱ ለማህበረሰቡ የማህበረሰቡ አንጡራ ሃብት ነው። ኳስ ዘመናይ ኢንደስትሪ ነው። ኳስ ሲታስብ ዓለም ደንበር ወስን የሌላት ሆና ህሊናን በሰውኛ እንዲጠበብ ያደርጋል። ሁሉም በአንድ መንፈስ ይከትማል በፍሰሃ እና በሰናይ። አሁን አውሮፓ ብቻ ቀረ። አውሮፓውያን ሁሉንም አህጉራት ሸኝተው አንድ ለአንድ ዋንጫው ላይ አስፍስፈዋል። ድንቁ ነገር ያልታሰቡት ቡድኖች ስለሆነ የቀሩት ጨዋታውን ብቻ ሳይሆን ዘመኑን

ፈረንሳይ ኡራጋይን እራቁቱን ሸኘው!

ምስል
ዋው ፈረንሳይ ለወሳኝ ፍልሚያ ዕድል ዛሬ ቀናው ፈረንሳይ ኡራጋይን እራቁቱን መለመላውን ሸኜው።  „እንደሱ ያለ ፈጣሪ ሌላ የለም፤  ለፈጠረው  ፍጥረት ሁሉ እሱ ገዥ ነውና፤" (መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፭) ከሥርጉተ© ሥላሴ 06.07.2018  (ከኮሽ አይሏ ሲዊዚሻ።) ·       ጠ ብታ! ጥዋት ላይ እኔና ጥላዬ ወጣ ብለን ነበር። የማይቀርበት ቀጠሮ ስለነበረን። ያው ርጥበት ጥሩ ነው። ሴቶች ዝናብ አይፈሩም ነው የሚበለው አይደለም? ሙግትም አንፈራም ተብሎ ቢወሰድስ፤ ዛሬ ፈረንሳይ ስላሸነፈ ደስ ብሎኛል ህብሩ ያስደስተኛል። ቀለማም ስለሆነ። ጥቁርነት አዲስ ቀለም ነው። የቀለሞች ህብርነት የሚመሰጠርበት።  ·       ልዕልቷ ድንቡልቡሊት። ድንቡልቡል ዊዲንግ ሻውር ናት ሩስያ ላይ። ታድላ!ስትደሰቅ ከትከት ብላ የምትስቅ፤ ስትላጋ ፈንጠዝያ ላይ የምትሆን፤ ስትነጥር ፏ የምትል፤ ስትገጭ ቧ የምትል፤ ስትጎን ደግሞ ዋው የምትል፤ በተወቂው መደብ ቤት ሆና አቤት ደስታዋ እልልታውን የምታስነካ፤ ይልመድብኝ ዱላሻ፤ ዱላሻ ስከንብኝ፤ ስልጥንም በልልኝ የምትል የሚሊዮን ፍቅረኛ የመቻቻል እጬጌ እቴዋ ድንቡልቡሊት፤ ደማሟ ድንቡልቡሊት እጁን እጥብ አድርጎ የፈጠራት ግን መታጨት፤ መዳር፤ መኳል፤ ግጥግጥ፤ ቅልቅል፤ መልስ ማጫ ሁሉም በዱላ በፈርማሹ ካልተረገጠች ደስ አይላትም … ዋንጫውን እንቺ ያለ ዱላ ብትሏት በጅ አትልም ስላችሁ፤ የውነት ...  ... ስላችሁ ሁካታዋ ፈንደቅያዋ - እስክስታዋ -  ወረቧ መቧረቋ፤ ይሄው ነው። ለዱላ ለርግጫ የተፈጠረች ጉዳኛ … ግን ሚሊዮን ውድድድድፍቅርርቅር ያደርጋል፤ ሸቅርቅር እኮ ናት ታዲያ … በመወቃት ነው… ውበቷ የሚበለጽገው ...

አዋሽም አልጋ ላይ ዋለ። እም!

ምስል
·              ርትህ።            ክፍል ሰባት። ከሥርጉተ ©ሥላሴ 05.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ዪሚያስታርቁ ብፁዕና ናቸው፤  የእግዚአብሄር ልጆች ይባላሉና።“ (ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፱) ·          መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c „ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar “ ከ20.38 እስከ 55.38። ልዑል እግዚአብሄር አላዛሯን ኢትዮጵያ ታደጋት። ውስጡ ውስጧ ያደረገ የአሮን በትር ሰጣት። ተመስገን!እንደ ሴራውማ ነገን ማሰብ ይቸግራል። ዛሬም ሴራን አጥምደው ክፉዎች በስውር እዬታገሏቸው ነው። ሃሳብን በሃሳብ መሞገት ይቻላል። እኔ እማምንበት በዚህ አመክንዮ ይሄ ነው ብሎ መሞገት የተገባ ነው። ነገር ግን አሁንም ወደ ዝብርቁ ቅልቅል መጪ እንዲባል ነው የሚፈለገው። ያን ያህል ህዝብ አዲስ አበባ ላይ ይወጣል ተብሎ ስላልታሰባ የርድት ወረርሸኙ ህም አሰኝቷናል። ፈጣሪ ደግ ነው አሜኑን አትርፎልናል አስከ ቅኑ ካቢኔው! ተመስገን! አሜኑ የኢትዮጵያ የምዕት ሽልማት ነው!ደግመንም አናገኘውም። ብህልምም የማይታሰብ ልዩ ሥጦታችን ነው ለቅኖች።   ·        እፍታ። ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ። ሲዊዚሻ የራስ ዳሽን ተራራ ይምጣብኝ ብላ ከንፈሮቿን አሳብጣ ዠርከከን ልካለች። የበጋ ልብስ ሲሸምት የከራረመውን ኩም እያደረገችው ነው።  ሠመራ ደግሞ ሙቀቷን ለግሳናለች።  እንዲህ። ዛሬ የሠመራ ማጠቃለያውን አቀርባለሁኝ። ምን ያህል እንደተረዳችሁኝ በላውቅም በዚህ ጉባኤ ላይ የ