ፈረንሳይ ኡራጋይን እራቁቱን ሸኘው!

ዋው ፈረንሳይ ለወሳኝ ፍልሚያ ዕድል ዛሬ ቀናው
ፈረንሳይ ኡራጋይን እራቁቱን መለመላውን ሸኜው።

 „እንደሱ ያለ ፈጣሪ ሌላ የለም፤ 
ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ እሱ ገዥ ነውና፤"

(መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፭)
ከሥርጉተ© ሥላሴ 06.07.2018 
(ከኮሽ አይሏ ሲዊዚሻ።)


  • ·      ብታ!

ጥዋት ላይ እኔና ጥላዬ ወጣ ብለን ነበር። የማይቀርበት ቀጠሮ ስለነበረን። ያው ርጥበት ጥሩ ነው። ሴቶች ዝናብ አይፈሩም ነው የሚበለው አይደለም? ሙግትም አንፈራም ተብሎ ቢወሰድስ፤ ዛሬ ፈረንሳይ ስላሸነፈ ደስ ብሎኛል ህብሩ ያስደስተኛል። ቀለማም ስለሆነ። ጥቁርነት አዲስ ቀለም ነው። የቀለሞች ህብርነት የሚመሰጠርበት። 


  • ·      ልዕልቷ ድንቡልቡሊት።

ድንቡልቡል ዊዲንግ ሻውር ናት ሩስያ ላይ። ታድላ!ስትደሰቅ ከትከት ብላ የምትስቅ፤ ስትላጋ ፈንጠዝያ ላይ የምትሆን፤ ስትነጥር ፏ የምትል፤ ስትገጭ ቧ የምትል፤ ስትጎን ደግሞ ዋው የምትል፤ በተወቂው መደብ ቤት ሆና አቤት ደስታዋ እልልታውን የምታስነካ፤ ይልመድብኝ ዱላሻ፤ ዱላሻ ስከንብኝ፤ ስልጥንም በልልኝ የምትል የሚሊዮን ፍቅረኛ የመቻቻል እጬጌ እቴዋ ድንቡልቡሊት፤ ደማሟ ድንቡልቡሊት እጁን እጥብ አድርጎ የፈጠራት ግን መታጨት፤ መዳር፤ መኳል፤ ግጥግጥ፤ ቅልቅል፤ መልስ ማጫ ሁሉም በዱላ በፈርማሹ ካልተረገጠች ደስ አይላትም … ዋንጫውን እንቺ ያለ ዱላ ብትሏት በጅ አትልም ስላችሁ፤ የውነት ...

 ... ስላችሁ ሁካታዋ ፈንደቅያዋ - እስክስታዋ -  ወረቧ መቧረቋ፤ ይሄው ነው። ለዱላ ለርግጫ የተፈጠረች ጉዳኛ … ግን ሚሊዮን ውድድድድፍቅርርቅር ያደርጋል፤ ሸቅርቅር እኮ ናት ታዲያ … በመወቃት ነው… ውበቷ የሚበለጽገው ...

ደብድቡኝ ለደስታዬን
አትለፉት እልልታዬን 
እንዲያመራችሁ ኮለልታዬ ትለናለች ... 
እቴጌዋ! 
ድንቡልቡሏ! 
ዱላ ክፍሏ። 

መቼም እንደ ድንቡልቡል ዱላ የሚወድ በምድር አልተፈጠረም። መረብ እማ ለምኝታ ነው ፍቅር ለቀመር። ትራስ ከፍ አድርጎ እሷን ለማስተኛት በፍቅር ለመኮልኮልልልል። 

ዛሬ ትንሽ አይዋ መቻቻል ግጥሚያ ቢጤ ቢገጥመውም ግን አውጥቶታል። ብቻ ሜዳውም - ሚዜውም - አራጋቢውም - ባለፊሻካውም ምን አለፋችሁ 5 ተጨማሪ ደቂቃ ታክሎ 95 ደቂቃ መንፈስን እንዳጠለጠሉ ተናካሹን ስዋርስን ወደ ቤትህ ብለው አድመው ባዶ ሆዱን ሽኝት። የዋዛ ፈረንሳይ … ቀን ሲከፋ እንዲህ … የቀን ልግመት ይኸው ነው።

ይሆናል የሚባለው አይሆንም፤ አይሆንም የሚባለው ደግሞ ሁነት መሆን ዕውንነት። ደስ ሲል ሚስጢረ ድንገቴ። አሁን በኢትዮጵያ ያለው የነገረ ሙሴም እንዲህ ነው ዱብ ያለ ተሰማይ … የኔ ሉዑል  ድንገቴ ተመስገን ተባል። ተመረቅም። ብሩክ ቅዱስ ሁንልኝ! እኔ እህትህን እርፍ አደረከኝ። ብክነት ቀረ፤ ቦስጣ ቤት ለቦስጣ ቤትም መከራተት ቅርት … አረፍንንንን ---  ዕድሜ ለአንተ ለቆመሱ ድንገቴ …

 … ዘንድሮ ስመ ጥር የአውሮፓ ቡድኖች ሾለክ ሾለክ እያሉ የኋልዬሽ እንደ ጉም ሽንት አሰኛቸው እና ከእናካቴው … ህልም ዕልም ሆኑ ያልታሰቡት ነው የወጡት።

ለዚህ ነው ልብንም --- ቀልብንም እንደላማው እንደ ገዱው ጠልጥል፤ ገዛ፤ ሳብ ያዝ ጨበጥ ማድረግ የቻሉት … ከእነወዙ አዲስ ትይንት እንዲህ ወክ እንዲህ እያለ ዘንከት እጥፍ ዘርጋ ሲል ጥሩ ነው …. ደስ ይላል … በለመደብኝ ይልመድብኝ ግን ብዙም …

  • ·      ነገረ የጠይም ዕንቁ ህብርነት … ፍሬ ነገር


ፈረንሳዮች „የአሸባሪነት“ ሰላባ ሆነው፤ የፍርሃት ቀጠና ሆነው፤ የየዕንባ ፊስቶ በዬፈርማታው ተከፍቶ ያን ሁሉ መከራ አሳልፈው፤ ያን መሰል ተከታታይ የግፍ መስዕውትንት ታግሰው ነበር በ2014 የፊፋን አውሮፓን የእግር ኳስ ውድድር በፍጹም የባለቤትነት ስሜት ያስተናገዱት። 

ሰፊ ስጋት ነበር። ለጥበቃ፤ ለደህንነት ያወጡት መዋለ ንዋይ ሆነ ያፈሰሱት የሰው አቅም የዋዛ አልነበረም። ያው ህዝቡም ከሳቅ ጋር እንዲገናኝ፤ የጠቆረው ተስፋ እንዲመለስ። ያን ጊዜ እኮ ፈረንሳይ ቱሪስት ተራቁቶባት ሁሉ ነበር … አኮ… ህም።

ያን ጊዜ ነበር እነኝህን የአሁኖቹን እንደ ጥንድ እንዝርት የሚሾሩትን የሚበሩትን እነ ግሪዝማን ኮከብ ሆነው የወጡት። እከሌ ተከሌ ያነሳል በማይባልበት ሁኔታ ነበር ቲሙ „እንኳን ደህና መጣችሁ ወደ ፍቅራማዊቷ ፈረንሳይ“ ያለው … ምርጡ ቡድን፤ ብቁ፤ ድርጁ፤ አቅሙ ተከታታይ እና ቋሚ የሆነ ቡድን ነበር ያን ጊዜ በፈረንሳይ አገር በተካሄደው የአውሮፓውያኑ የፊፋ የእግር ኳስ የዋንጫ ጉግስ።


ያልታዬ ትዕይንት ዓይነት አልነበረም፤ የጋዜጠኛ ዘገባ፤ የደጋፊ አዲሳዊነት አርት፤ የዳኞች ትወና ፍጹም ሳቢ እና ማረኪ ነበር። ዘንድሮ ግን ዳኞች ጭመት ሆነዋል፤ የሲዊዝ አድባር ዞር ዞር ብሎባቸው አንድም በታዋናይነት የሰለጠነ አላዬሁም፤ ጭጭ ያለ ጉድ … እኔ ከጨዋታው የ አሰልጣኞች መድረክ ነበር የሚስበኝ። ዘንድሮ ግን ኩም አደረጉኝ።

 ለነገሩ የጦቢት ጮሪት ዜናም ቀልቤን ጨብጦ ወድሮ ይዞ አላንቀሳቀስ ብሎኝ ነው የከራረመው … በአደብ አልተከታተልኩትም ነበር እንደ ማለት ያመለጠኝ ሊኖር ይችላል …
  • የአወሮፓ መባጃ በዕንባ በስጋት ነበር ባለፉት ዓመታት …

በዛ የእልቂት ሰሞናት እኔም የቤልጀም እና የፈረንሳይን ሰቆቃ እዬተመለከትኩ ከውስጤ አዝን ስለነበር ከልብ ነበር በደጋፊነት የሁለቱን ቡድኖችን በመንፈሴ የተከታተልኩት። በዛ ውስጥ እናቶች ልጆች አሉ።

እኔ ከሁለቱ አንዱ ዋንጫውን እንዲወስዱ ነበር ምኞቴ በ2014። ግን ያን የመሰለ ጨዋታ ያሳዩት ሁለቱ ጠንካራ ቡድኖች ሳይሆኑ ፖርቹጋል ነበር የወሰደው ዋንጫውን። 

እርግጥ ነው ፖርቹጋል ቢወሰዱትም አልከፋኝም። ለእነሱም እንኳን በለስ ቀናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኙት ዕድል የነበረ ይመስለኛል … በዓመቱም በ2017 ፓርቹጋል ቀናቸው እና ኢሮ ቪዥን ሶንግን አሸነፊ ሆኑ። ወፍ ሲያወጣ እንዲህ ነው … ተመጨመር ላይ መጨመር፤ ከመታከል ላይ መታከል። ትክለት እንዲህ ነው … በዕድሊት ልዕልቲት፤ በዕዱሉ ልዑሉ።  
  • ምልስት ወደ ፈረንሳይ ሲሆን ….

ዛሬ በነበረው የኡራጋይ እና የፈረንሳይ ጨዋታ ከኡራጋይ ጥንካሬ አንጻር የተመጣጠነ ውጤት ይኖራል፤ ቢያንስ የጨዋታው ጊዜ ይራዘማል፤ ከዛም ልክ እንደ ኮሎንብያ እና እንደ ብርቴን ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ። ነገር ግን በሰፋ ልዩነት በመደበኛ ጨዋታ ኡራጋይ ባዶ እጁን መራራ ስንብት አደረገ። መጀመሪያ ላይ በአንድ ክንፍ ፈረንሳዮች ክፍተት ሲሳዩ ፈርቼ ነበር። ረዘም ላላ ደቂቃ ክፍት ነበር … በዛ ክፍተት ኡራጋይ ስልቱን ቀይሮ የማጥቃት ሙከራ ማድረግ አልቻለም …

በሌላ በኩል ፈረንሳዮች በሜዳቸው ላይ ዋዘኞች ሆነው አይቸቸዋለሁኝ። የተፎካካሪያቸው ሜዳ እስኪመስል … ዘና ማለትን የማብዛት፤ እንደ እኛ በሌለን አቅም ቀንጣ፤ ዘመንም እንደምንለው በልግመኛው ፓለቲካ ዕሳቤ ማለት ነው … 
  
እንግዲህ ቤልጄም እና ብራዚል ቀጣይ ጨዋታ ይኖራቸውል ከ30 ደቂቃ በሆዋላ፤ አንዱ የፈረንሳይ ተጋጣሚ ይሆናል ማለት ነው አሸናፊው። ቤልጄም ቢያሸነፍልኝ ምኞቴ ነው ከብራዚል ጋር በሚኖረው ጨዋታ። 

ዛሬ ብራዚል ከቀናው በመሬታቸው ላይ በተካሄደው ጨዋታ በኳሳዊ ጨዋታ ሴራ ኮከባቸው ኔማር በደረሰበት ድንገተኛ ምክንያት የሞተው ተስፋቸው ነፍስ ይዘራበታል። የጠበቅኩትን ያህል ጥንካሬ ግን አላዬሁም ባዬሁት ጨዋታ። ያው ኳስ ዕድልም ነው … ብራዚል ካሸነፈ ግን ዋንጫው ...የመወስድ ዕድል ይኖረዋል። እልህኞች ናቸው።

ብራዚል ቢሸነፍልኝ እናም ሁለቱን ማለት የምወዳቸው ቡድኖች ቤልጄም እና ፈረንሳይ ሜዳ ላይ ፉክክራቸውን ማዬት ይናፍቀኛል። ግን ልጄም ብራዚልን ከረታ ነው። ባለፈው ጊዜ ደከም ብለው ነው ያዬኋዋቸው። ዕድል ረድቷቸው ነው በአለቀ ሰከንድ ጨዋታው ሳይራዘም ያሸነፉት፤ እንጂ እኩል ለእኩል ሆኖ ጨዋታው ተራዝሞ ቢሆን ኖረ ምን አልባት ይህን ዕድል ላያገኙ ይችሉ ነበር። 

እኔ እንደማስበው የብራዚሉን ቡድን በዛ መልክ እንደማያስተናግዱት በበቂም ድክመቶቻቸውን አሻሽለው እንደሚገቡ ተስፋ አደርጋለሁኝ።
ሁለቱም በዚህ ጨዋታ ፈጣሪ የረዳቸው ልዩ ሁኔታ ስለነበረ። እድልን  በአግባቡ መጠቀም የተስፋ ዝልቅነት ነው። ኢትዮጵውያንም ይህችን  ተእዮር የተላከቸውን መክሊት ጠበቅ አድርጎ መያዝ ይጠበቀብናል። 


ዛሬም ጠይም ዕንቁዎችን በህብርነት ያሰተናገደው የፈረንሳይ ቡድን ኡራጋይን ቤሳ ቤስቲ ሳይጥልለት እራቁቱን አሰናበተ ለዛውም ስዋርስን …. ዋው። ድንቅ ነገር። 

በነገራችን ላይ እንግሊዝም ዋንጫ ቢወስድ ደስ ይለኛል። ዘንድሮ  ልብ ሸምተው ከአንድ ሰው አምልኮ ወጥተው ብቁዎችን አቀርበዋል፤ በዛ ላይ ዘንድሮ ዓለምን በተግባር ያስተማረ ቤተመንግሥታዊ መቻቻል አሳይተዋል። ጥቁር መፈቀር የሚችል የፈጣሪ ፍጡር ስለመሆኑ አመሳጥረዋል። ቅኔንት በቅንነት አውሮፓ ላይ ዕድምታዊ ተደሞ ነበር።

ውዶቼ ስለ ዛሬ አትጨነቁ፤ ዛሬ የተሻለ ስለሆነ፤ ነገ ግን አስፈሪ ግራጫማ ነው። ስለሆነም ስለ ነገ የመቻቻል ድል ማድረግ ነው ማሰብ። 

እኛ የጎሼ ዓለም አውርሰን እንዳንሄድ ነው ንጉሴ ስለሆነ ለእኔ ንጉሥ ሐሪ ቻርልስ ያን ድንቅ ተግባር የፈጸመው። ለነገ ትውልድ 6 ዩንቨርስቲ ወደላይ ቢካብ አይመጥነውም ተግባሩ። ውሳኔው ፍልስፍናም ነው። ውሳኔው የመቻቻል አዲስ መጸሐፍ ነው። ዓለምን ያዳነ ወደፊትም የሚያድን ፍልስፍና ነው። መድህን ነው።  የነጮችን ፖፕሊስትነትን በዝምታው ውስጥ አፈር ያስጋጠ የዘመን አውራ ጀግና!

አሜሪካ ላይ አሁንም ጥቁሮች ይገደላሉ … ያ የፍቅር ንጉሥ ሐሪ ቻርልስ ግን ፍቅራዊነትን አነገሰ በራሱ ህይወት ውስጥ ፍቅራዊነትን ፈጠረው አበጀው! ታላቅ የዘመኑ የአክብሮት መሪ! የተፈጥሮ መሪ!
ፍቅራዊነት በውል የከተመበት ኳስ ብቻ ነው!

የኔዎቹ መልካም ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።