አዋሽም አልጋ ላይ ዋለ። እም!

·             ርትህ።
          ክፍል ሰባት።
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 05.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„ዪሚያስታርቁ ብፁዕና ናቸው፤
 የእግዚአብሄር ልጆች ይባላሉና።“

(ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፱)


·         መነሻ።
„ጠ/ / አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar
ከ20.38 እስከ 55.38። ልዑል እግዚአብሄር አላዛሯን ኢትዮጵያ ታደጋት። ውስጡ ውስጧ ያደረገ የአሮን በትር ሰጣት። ተመስገን!እንደ ሴራውማ ነገን ማሰብ ይቸግራል። ዛሬም ሴራን አጥምደው ክፉዎች በስውር እዬታገሏቸው ነው። ሃሳብን በሃሳብ መሞገት ይቻላል። እኔ እማምንበት በዚህ አመክንዮ ይሄ ነው ብሎ መሞገት የተገባ ነው። ነገር ግን አሁንም ወደ ዝብርቁ ቅልቅል መጪ እንዲባል ነው የሚፈለገው። ያን ያህል ህዝብ አዲስ አበባ ላይ ይወጣል ተብሎ ስላልታሰባ የርድት ወረርሸኙ ህም አሰኝቷናል። ፈጣሪ ደግ ነው አሜኑን አትርፎልናል አስከ ቅኑ ካቢኔው! ተመስገን! አሜኑ የኢትዮጵያ የምዕት ሽልማት ነው!ደግመንም አናገኘውም። ብህልምም የማይታሰብ ልዩ ሥጦታችን ነው ለቅኖች።  

  • ·       እፍታ።


ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ። ሲዊዚሻ የራስ ዳሽን ተራራ ይምጣብኝ ብላ ከንፈሮቿን አሳብጣ ዠርከከን ልካለች። የበጋ ልብስ ሲሸምት የከራረመውን ኩም እያደረገችው ነው። 
ሠመራ ደግሞ ሙቀቷን ለግሳናለች። 
  • እንዲህ።

ዛሬ የሠመራ ማጠቃለያውን አቀርባለሁኝ። ምን ያህል እንደተረዳችሁኝ በላውቅም በዚህ ጉባኤ ላይ የተሰጡ መልሶች ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ከተሾሙበት ጀምሮ ከተካሄዱት ስብሰባዎች እና መልሶቻቸው ውስጥ ፍንጮች ጎላ ብለው ስለቀረቡበት ነው አትኩሮቴን የሳበው።

  • ·       „ደርግን የጣለው ራሱ ደርግ ነው።“

ትክክለኛ አገላለጽ ነው። ግን ዶር አብይ አህመድ የወደቀበትን በገለጹበት መንገድ ብቻ አልነበረም ባይ ነኝ እኔው። ክቡሩነታቸው ያሉት „ደርግ ገዳይ እና ጨፍጫፊ ስለነበር ወደቀ“ ነው ያሉት። ኢህአዴግ መራሹ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከፍጥረቱ እሰከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ጨፍጫፊ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጫካ በቆዬባቸው ወቅት የወልቃይት እና የጠገዴን ህዝብ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ጽኑ አቋም የነበራቸውን የትግራይ ልጆችም ያለርህራሄ ጨፍጭፏል። አሁንም ጭፍጨፋውን ቀጥሏል። ለዛውም በአደባባይ። የፈጣሪ እርዳታ እኮ ነበር በሁለት ሰው የ አርበኝነት ከ150 በላይ ወገኖች በቁስለኝነት ቀኑ ያለፈው። እጅግ የማናውቀው የምንጠብቀውም ቀውስጥ ይገባ ነበር። ምክንያቱም ዝግጅቱ ጥንቃቄው ድርጁ አልነበረም። ጦርነቱ የሰርገኛ ጤፍ ጉዳይ ስለመሆኑ ልብ ያለው የለም። በመህረቱ ስለጎበኘን እንጂ ከዬትኛውም የጭፍጨፋ መከራ በላይ የታቀደ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ጭፍጭፋ ዘር በማመከን፤ በመሰውር፤ በድብደባ ብዛት ህሊናን በማሳት ወዘተ … ነው። ዛሬም ህግ አይገዛውም ጨፍጫፊውን ... 

ለወደፊትም በጥናት በተመሠረተ ወደ ህብረ ብሄር ፓርቲነት የማሸጋገር ሁኔታም አባል ድርጅት ሆኖ ይቀጥላል የወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጀት ለሚለው በክፍል ስድት ላይ እንዳመላከትኩት ከባዱ ፈተና ነው። ሌላውም በተባባሪነት፤ በአጋርነት የወያኔ ሃርነት ትግራይ የመተንፈሻ ሆነው የኖሩትም አብረው ህብረ ብሄራዊ ሆነው ይቀጥላሉ ማለት ነው። „በመግደል እና በመጨፍጨፍ ለዛውም በአንድ ጎሳ ብቻ የተከወነ የጨለማው ትእይንት ሥርዓት በጭፍጨፋ እና በግድያ መውደቅ ቢችል ኖሮ 5 ዓመት መቆዬት አይችልም ነበር የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት የበላይነት ሥርዓቱ። አሁን እኮ ጭፍጨፋው መፈነቃሉ ከዚህም ባለፈ ፈንጂ አቅዶ እስከማፈንዳት ያደረሰ ሥርዓት ነው ያለው።

አሁን ደግሞ የኤሌትሪክ አደጋም ተከትሏል፤ የመጠጥ ውሃን በመርዝ ብክለትም ቀጣዩ መካራ ነው። ስለዚህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ የተዋቀረበት በጥላቻ ስለሆነ መንፈሱ እራሱ ሰው ገድሎ በመርካት፤ ሰውን ተበቅሎ በመርካት፤ ተፈጥሮን አስተጓጉሎ በመርካት የተሰናዳ ነው። ጭፍጨፋ አይዲኦሎጂው ነው። ስለዚህ 27 ዓመት ቀርቶ ጨፍጫፊነት ሥልጣን የሚያስለቅ ቢሆን 7 ቀንም አያቆይም።

ይህን ስል መጋቢት 24 ቀን 2010 ያን ያህል ፍሰሃ የወረደው አዲስ የተስፋ ዋዜማ በመምጣቱ ነው። ጨፍጫፊነት ብቻውን ሥርዓት ያስወግዳል ከሆነ፤  በዚህ እሳቤ ከሆነ ሽግግሩን የሚያከብድ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁኝ። ምክንያቱም ችግሮችን ከመሠረታቸው ለማዬት የሚያስችሉ ብልህ ቁምነገር ነገሮችን ስለሚጫነው። በአጠቃለዩ ዕውነት ስንሄድ የሶሻሊዝምን አይዲወሎጂ መመርምር እጅግ አስፈላጊ ነው። ከዛ ከተነሳን ብቻ ነው ትውልድን በዘለቄታ ሊያሻግር የሚችል ቋሚ ሥርዓት እና መስመር መዘርጋት የሚቻለው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ የመከራ ምንጭ ግራ ዘመም የፖለቲካ ንድፍ ነው። መርዝ ነው ይሄ ርዕዮት። ሰውና ተፈጥሮን ተጻሮ የሚነሳ ባሩድ አምላኪ፤ ፈጣሪን የከዳ ሥርዓት ነው። ፈርሃ እግዚአብሄር የለብትም። ግዑዝ ርዕዮት ነው። የተጣበቀ ነው። የኩሬ ውሃ ነው። ዕድገት የማያሳይ ግትር እና አግሬሲብ የሚሆነውም ከዚኸው ነው። ሁልጊዜ ገዢ ሃሳብ የ እሱ እና የ እምልኮው ነው እንዲሆነው የሚሻው። ጆሮ አልፈጠረለትም። ማስተዋል አልሰራለትም። መሰልጠን የመከነበት ነው። ጊዜም ትቶት ያለፈ ነው። 

ስለዚህም ደርግ የወደቀበት እጅግ ጉልህ መሰረታዊ አምክንዮች አሉበት ብዬ ነው እማምነው።  አንደኛው የዘመኑ ባህሪ በመለወጡ ነው። ሌላውን ውጊያው የእርስ በርስ ነበር። ማሸነፍ ማለት ሚስጢር ነው። ወያኔውም፤ ሻብያውም፤ ኦንጉም አብሮ ነው በከፍተኛ ደረጃ የሚሠራው የነበረው በደርግ ጊዜ፤ እንዲያውም ቁልፉ ቦታ ሲመሩት፤ ሲያስተዳድሩት የዚህ ዝንባሌ ያላቸው እና የነበራቸው ስለመሆኑ የፌድራሊዝም አደረጃጀቱ በማሳነስ የተዋቀረ ነበር። ለጎንደር፤ ለሽዋ፤ ለወሎ ይጠቅማቸው የነበረው አንድ በነበረው መልክ መቀጠል እንጂ መሸንሸን አልነበረም። ብዙ ነገር ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ተሰናድቶ ፈርታይል ሆኖ የጠበቃቸው እንዳይቸገሩ። የተቀዬረው ያን ብሄራዊ መልክ የነበረውን ግራ ዘመም ፖለቲካ ወደ ጎሳ አውረዱት። በቃ። ለዛውም አንድ ጎሳን አናጦ የማውጣት በሥነ ልቦናም በባህልም በማህበራዊ ህይወትም በኢኮኖሚም በመወስን አቅምም። 

ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ሚስጢር ይላካል በቃ ሽንፈት ይጠጣል፤፡ ለአንድ ሽምቅ ውጊያ አዬር መቃወሚያ ይንቀሰቃሳል፤ ከባድ መሠሪያ ይንቀሳቀሳል አስርክቦ ያን ይመለሳል። ሴራው፤ ሳቦታጁ፤ ሸሩ፤ ተንኮሉ መስፈሪያ አልነበረውም።
  • ሂደት።


የውጪው ሃይል ሙሉ እገዛ አልጋዊነት፤ እዛው ውስጥ የሚሠሩት እራሱ ትጋታቸው ዕለት ተዕለት መዛል፤ የመፈንቅለ መንግሥቱ እና ክሽፈቱ የፈጠረው የተስፋ ቆራጭነት ስሜት፤ የሊቢራላዊነት አቋም አወሳሰን እና የፓርቲው ሚና በክፍትነት የተሰተናገደበት ሁኔታ።

በሠራዊቱ ውስጥ የነበረው የፓርቲው መዋቅር እና አመራር በመስጠት እና በመቀበል ወታደራዊ ዲስፕሊኑን የጣስ መሆን አንድ 10 አለቃ የፓረቲው መሠረታዊ ድርጅት ተጠሪ ከሆነ የጦሩን ስልት እና ስትራቴጂ ፕላኑን ሁሉ ረቂቅ ሚስጢሮችን ሁሉ ለማወቅ ጠበብት ሳይንቲስት ከፍተኛ ሞኮነኖችን ለመምራት እርምጃ ለመውስድ የነበረው ስርዓት አለበኝነት የሳይንስ እና የተለምዶ ግጭት መፋለስ፤ በዬመሥሪያቤቱ የነበሩት የመሰረታዊ ድርጅት ተጠሪዎች ሙያዊ ክህሎት እና የፓርቲ አባልነት አቅም ምጣኔ ዝበትም ግጭትም ነበረበት።

አንድን ፕሮፌሰር አንድ ተራ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ የመሠረታዊ ድርጅት አባል የሆነ ልምራህ ይላል … አሁንም በዩንቨርስቲዎች ያለው መከራ ይሄው ነው። ይህ የሶሻሊዝም መከራ ነው። ሌሎችም አሁን ለሥልጣን ያልበቁት ዕድሉን ቢያገኙት ቀጣይ ፈጻሚነተቸው 100% ነው ቢዚህ መንገድ ነው የሚሄዱት።

ውጪ አገር እንኳን ያለውን የዴሞክራሲ ስፋት እና የሰውን ተፈጥሯዊ ስብዕና በሚያከብርበት አገር ተቀምጠው ፍዳው እኮ ይሄ ነው። ህይወታችሁ በእኛ ቁጥጥር ሥር ይሁን፤ ልብ ይገጠምላችሁ፤ ብቅ ያለ ሁሉ በዛ ሥርዓት ተዋረድ ነው የሚመራው። ያልተቀበልነው ግማድም ይሄው ነው። ሶሺዝም ሰው ተፈጠረህ እቃ ሆነህ ኑር የሚል መርህን ነው የሚከተለው። አንተ አታሳብም ነው። ራስን ሰርዞ የሚኖርበት ሥርዓት ነው። አብሶ ወጣቶች ይህን የ አብይ መንፈስ በቅንነት፤ በታማኝነት፤ በንጽህና፤ በቅድስና መከተል ካልቻሉ ብክነታቸው በሁለመናቸው ቀጣይ ነው የሚሆነው። 

 ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እንዳሉት የሰው ለውጥ ሳይሆን የአይዲኦሎጂ ለውጥ ነው ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት። ለዚህ ነው በመርዝ የተጠቀለለውን የሽግግር መንግሥት ሴራ እማልቀበለው። ይህን ከተቀበለ የአብይ መንፈስ ኢትዮጵያ በ2030 ትጠፋለች ብሎ እንደ ቀረበው የአሜሪካ ጥናታዊ መረጃ ትከስማለች። ሶሻሊዝም ያረጀ ብቻ ሳይሆን የከረፋም ሥርዓት ነውና።

ወደ ቀደመው ስመለስ …  

የረጅም ጊዜ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብን ተስፋ ላማሟለት የአቅም ውስንነት እና ደርግ ቢወድቅ የተሻለ ሥርዓት ይመጣል በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ ልቡ መሸፈቱ ወዘተ … 

ብልህ መሪዎች ነበሩበት በኢሠፓም ጠንካራ፤ ሰርተው የማይደክሙ፤ ቅን ነበሩበት እኔን የገጠሙኝ ስለነበሩ ግን አድማጭ ያገኙ አይመስለኝም። ስለምን? ቅኖቹ በሚያስቡት መነገድ ከመሄድ ይልቅ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ሻብያ ተልዕኳቸው እንዲሳካ ይፈለግ ስለነበር ቅኖች እዬተገፉ፤ እዬተራገፉም ሸካራዎች መደመጥን አገኙ። ይሄ አደጋ የዶር አብይን ካቢኔ እንዳይገጥመው ስጋት አለኝ። 

በራሱ ጊዜ ከለዘር የፈረሰ ፓርቲ ቢኖር ኢሠፓ ነው። ከውስጡ ነበር የፈረሰው። ከመደበኛ ሠራተኞች ውጪ ወርሃዊ የአባልነት ክፍያቸውን ያቆሙ ሁሉ ብዙ ነበሩ። በተለይም ቀኑን አላስተውሰውም አንድ ቀን ፓርቲው ስለሚከታላቸው አዲስ መንገዶች በራዲዮ ላይፍ ላይ ነበር ሁላችንም የሠማነው። ያ ውስጡን ሙሉ ለሙሉ ያለ ርህራሄ አፈረሰው።

የእነ ጄኒራል ታሪኩ መረሸን ብዙዎቹን መኮነኖች ልብ ያሸፈተ ነበር። በዋላ ደግሞ የእነ ጄኒራል ፈንታ በላይ ሲታከል አለቀ ሥርዓቱ። የሴራው ነገር አንዲት ቅንጣት ነገር ለመፈጸም የነበረው ውጣ ውረድ ከእስከ እስከ አይባልም። ትብትብ የሆነ ነገር ነበረበት። ለሥራ የተፈቀደ መኪና ለሌላ ሥር ተመድቧል እዬተባለ ምን ያህል ጭንቅላት የሚያፈነዳ ጉድ እንደ ነበረ የነበርንበት ሰዎች እናውቀዋለን። 

እንደዛ በ አራቱም ማእዛ ተወጥረን ጎንደር ላይ ሠራዊቱ እንዲነሳ ባይደረግ፤ ሌላው ቀርቶ በነበረችን አንዲት ዕድል ሠራዊት ተማጽነን ስንቅ ባይላክ ኖሮ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በመጣበት እግሩ ይመለስ ነበር። ያ ግን አልተፈለገም ነበር። ሴራው፤ ሸሩ፤ ደባው፤ ተንኮሉ በራሱ ጊዜ ራሱን ያጠፋው። እንተርፋለን ከቀጣዩ ሥርዓት ጋር እንቀጥላለን የተባለው ተስፋም መና ሆኖ ቀረ ...  ዛሬም ይሄ ጠማን ነው የሽግግር መንግሥት ናፋቂዎች የሚሉት … ወያኔ ሃርነትም ከማህል አልታረሥ ከደንበር አልመለስ ብሎ የሚነስተው ይሄው ነው። 

ከእንግዲህ አንዲት ነፍስ ለአንዲት ደቂቃ ያ ሥርዓት እንዲመለስ ህዝብ አልፈልግም ሲል ግራ ዘመምንም ጭምር ነው ... ትርፉ የትውልድ ብክነት ነው። ለዚህ ነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ አምለኮዊ ማንፌስቶውን ገደል ውስጥ ጨመሮ ልቡን መንፈሱን ሰዋዊ እና ተፈጠሯዊ ማድረግ አለበት ብዬ ስኮልም የባጀሁት። 

ቅኖችን የማኖር አቅም የለውም ሶሻሊዝም። ዕውነተኞችን የመደገፍ ንድፈ ሃሳብ የለውም ግራ ዘመም ፖለቲካ። መነጠል፤ መለዬት፤ በሳቢያዎች ላይ መርዝ መነስነስ፤ መክፈል ... ይሄ ነው ግቡ። 

ሌላም አካል ኢህአፓም ሆነ መኢሶን ዕድሉን አግኝተውት ቢሆን ኖሮ ከዚህ ውጪ አይሆኑም። ከዚህ ከለማ ከገዱ ከ አብይ እና ከ አንባቸው መንፈስ ውጪ የሆኑ መንፈሶች ሁሉ የዛው የሶሻሊዝም ቁስ አካላዊ ማህበርተኞች ናቸው። የዳኑ አሉ መ ኢሶንን ብንጽህናው ስለ ድንግልናው መመስከር ይቻላል። ሌሎችን ግን ሶሻሊዝም ማዕከሉ ቁስአካል ስለሆነ ዳገቱን መውጣት አይችሉም። 

ወደፊትም ኢትዮጵያ ከዚህ ቅኝት ሙሉ ለሙሉ እስካልወጣች ድረስ ጉዞው ከባድ ነው። የተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከዚህው ገመና ጋር ናቸው ያሉት አሁንም፤ አዲሶቹ ሳይቀሩ። ለዚህ ነው ፍቅር ሰላም አንድነት የአገር ልጅነት የሚባለው ከቋንቋ በስተቀር በመሆን ውስጥ የሌለው፤ ያልነበረውም። ቂሙ ቁርሾው በቀሉ እኮ ነው ህሊናን አስሮ አንዲት ስንዝር ተራምደን መልካም ነገሮችን ለመቀበል፤ ለማድነቅ፤ ለማጽደቅ፤ አብሮ ለመዝለቅ ቤተኛ ለመሆን ተራራ የተሆነው። በሽታ ነው። ከሊቅ አስከ ደቂቅ የሚታመስበት ይሄው ገመና ነው። አሁን ራሱ ለበጣዊ ቅባዊ ምስላዊ ኩነት ቁጭ ብዬ ስመረምው ማታ ታፈርሳለህ ቀን ገንቢ መስለህ ትቀርባለህ። ሚዲያ ላይ ገንቢ ነህ የጓዳህ ደግሞ ተባይ ያመርታል። እነኝህ ወጣት ሊሂቃን በሁለመና ነው የበለጧቸው። ደራጀውን መድረስ ሳይሆን መተንበይ ሳልልቻሉ መሬት ለመሬት እንደ እባብ ይሳባሉ፤ አሁን ይሄ ትውልድን ከብክነት ስለማያጠርፍ ራስን እያጸዱ ከቅንነት ጋር መሰለፍ ግድ ይላል። 

አሁን እንደማዬው የተጀመረው መንገድ ከነበረው የፖለቲካ መስምር የወጣም ስለሆነ ነው እኔ ሙሉ ለሙሉ ታዳሚ በመሆን ሙሉ ጊዜዬን እዬሰጠሁት ያለሁት። የየአሁኑ ከቁሳአካላዊነት ተወጥቶ ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ነው። ለ እኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ሥርነቀል ነው። ከ አብይ የላቀ ሁለገብ፤ ሁለንትና፤ ሞራላዊ ሊሂቅ መሪም ለእኔ የለም ከለማ በስተቀር። የህዝብ ተወካዮች አፈ ጉባኤ ብቁ ናቸው። ብልህ ናቸው። የተረጋጋዩ ናቸው። ድንቅ ሊሂቅ። ሩህሩህ። 

የሴራ መሪነት በዚህ ውስጥ ያሉ ነገሮች እረፍት ስለነሳኝ ነው እኔ የፍቅራዊነት ፕሮጀክትን እንድጀምር የተገደድኩበት። ሾሻሊዝም ንድፈ ሃሳቡ ሳይሆን ችግሩ አፈጻጻሙን አንጋለው አወላግደው፤ ኮረኮንች አድርገው የጀመሩት ያወረሱት መከራ ነው ለዓለም የተረፈው የመከራ ተራራ፤ የሰው ልጅ እጨዳ ስቃይም ይሄው ነው።

አሁን ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚያሳዬው ግትርነትም ከዚህ የመነጨ ነው። እሱ ብቻ አይደለም "አለባብሰው ቢያርሱት በአረም ይመለሱ" እንደሚባለው የወለሌ ገበታ ላይ ያሉት፤ በማህል ሠፋሪነት የሚገኙት፤ ሚዛን አልቦሽ የሰውን መንፈስ ማህል ላይ መገተር የሚያሰኛቸው ባለ ግራጫ ፖለቲከኞች የአብይን መንፈስ የደገፈን ቅላጼ ወጀብ ህዝቡ መንፈሱን ስላራቀቸው ያነን ለመሰብሰብ ነው እፍ ግብ እያሉ ያሉት እንጂ መርዙን ነቅለው ለማውጣት ፈቃደኞች አይደሉም። ምክንያቱም ያ መርዝ ነው በህሊናቸው ዘውድ ደፍተው እንዲቀጥሉ ጥገታቸው። መልቲ ቪታሚናቸው ነው።  

ስለምን? አቅም አልባ ተኮፍሶ በሰው ደም እና ብርንዶ መኖር የተኖረበት የላንቲካ ፖለቲካ ነው እና። ቀውሱ መቆሙን የሚፈልጉት የእነሱ የታቆረ ሃሳብ ለድል ከበቃ ብቻ ነው። ካልሆነ መስጥረው የሚይዙት ይሄውን ነው። ቀውሱ መቀጠሉ ደስታቸው ነው። ህልም አላቸው ያን የ4ኪሎ ወንበር ከ8 ተርትረው መከፋፈል። ከዛ ደግሞ ህዝበ አዳም ከ8 ተተርትሮ አሸናፊው፤ ተሸናፊውን 7ቱን ለሌላ መከራ በቀል ማወራረጃ ይሆናል። የትውልዱ ብክነት ለእነሰ ምናቸውም አይደለም። አክተሮች ናቸው አይሞቱ አይታመሙ …  የኢትዮጵያ እናት ለእነሱ ቀይ ምንጣፍ ትውለድ፤ ታሳድግ፤ የሰው የሊኳንዳ ቤት ጥሬ እቃ ታምርት። እንጨት ሽጣ፤ ግፋፎ ለቅማ፤ ራሷንም ቸብችባ፤ ተገርዳ … አሳድጋ ለእነሱ የከረባት እና የገበርዲን ሲሳይ …

  • ·       ዋስትና።

ዋስተናው አዲስ ዴሞክራሲ ሥርዓት ነውአሁንም ከግራ ዘመም ፖለቲካ የወጣ መሆን ይኖርበታል። ሁልጊዜም እንደምለው ነጮች ብቻ እንዲቀመጡበት ታስቦ በተዘጋጀው የነጮች ቤተ መንግሥት ጥቁር ፕሬዚዳንትም እንዲኖሩበት የሆነው ቁም ነገሩ ሥርዓቱ በማይናወጽ መሠረት ስለተገናባ ነው። ስለሆነም እኔ በዶር አብይ አህመድ መንፈስ ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለኝም። እሳቸውም በዚህ ጉባኤ አበክረው ገልጸውታል። ከእኛ የሚጠበቀው እንደ ግልም እንደ ጋራም የድርሻን መወጣት ነው። እኔም የድርሻዬን ለመወጣት ነው ይህን ብሎግ ቀንበጥ ብዬ የጀመርኩት።

ለጋ መንገድ ነው የአብይ መንፈስ። ኢትዮጵያን ይዞ ነው የተነሳው።  ድርጁ ጠንካራ እንደብረት ጠንካራ ዘላቂ ማድረግ የሚቻለው ሁሉም በዬተሰጠው ጸጋ እና መክሊት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ክፍተቶችን ለመሙላት ቀን ከሌት መሥራት ሲችል ብቻ ነው። ስለሆነም እሳቸውም ገልጸውታል የፖለቲካ ድርጅቶች በማሸነፍ እና በመሸነፍ ሂደታቸው ውስጥ ቋሚ በሆነው ሥርዓት ማዕቀፍ ብቻ ሊሆኑ ግድ እንደሚላቸው ተናግረዋል። ልክ እንደ አሜሪካ፤ እንደ ጀርመን፤ እንደ ሲዊዝ ወዘተ … ይሄ መቼም አዲስ ዜና ነው። ደግሞም ያደርጉታል። እኔ እንደሌላው ተጠራጣሪ አይደለሁኝም። ሙሉ እምነት ነው ያለኝ። ስለዚህም ዎህ ብያለሁኝ።

  • ·       አላዛሯ ኢትዮጵያም ሐሤት አግኝታለች።

ኢትዮጵያ እንደ አላዛር ናት። ደግነቱ እንደ ወደቀች አለመቀርቷ ነው። በማያወላውል ሁኔታ ከኢትዮጵያ ህልውና በላይ ማንም እና ምንም እንደሌላ አስረግጠው ገልጸዋል ጠ/ ሚር  አብይ አህመድ። ይሄ ለሊሂቃን መርዶ ይሆናል። በሲሶ ፍቅር ነበር አንጋች አሰልፈው የኖሩት። ስለዚህ ኢትዮጵያን የሚጫን፤ የሚኮንን፤ ለማሳሳት፤ ለማኮስመን፤ ለመቀነስ የሚደረገውን ማናቸውም መስዋዕትነት ለመክፍል ካቢኔያቸው ዝግጁ መሆኑን አብሥረዋል። ደንግገዋል። ይሄ መቼም ለእኔ የሠማይ ታምር ነው።
  • ·       ዘርተኮር ሰብዕና።

ዘር ተኮር ሰብዕና ለማስወገድ የሥነ - ልቦና ስንዱነትን የሚጠይቅ ነው። ይህ በዓዋጅም የሚፈርስ አይደለም። የፈለገ ጥናት ቢደረግም ምላሽ ሊሆን የሚችል አይደለም። እጅግ የተጎሳቀሉ ነፍሶች ስላሉ ቁስላቸውን ማስታመሚያ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፤ ተጎድተዋል። ስለዚህ በዚህ ዕሳቤ በተለያዩ ማንነቶች ውስጥ የነበሩ መንፈሶችን ወደ ማህል ለማምጣት የሚደረግ ጥረት እንደሚኖር በዚህ ጉባኤ ላይ አዳምጫለሁኝ። በዛ ላይ የለመደባቸው አሁንም እያነኮሩት ነው። መደመር ሲመጣ ቢጨንቃቸውም አጋጣሚውን ተጠቅመው ያው መንገዳቸውን እያደላደሉበት ነው። ኢትዮጵያ ካልፈራረሰች እረፍት ስለማያገኙ። ይህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ተነጥሎ የሚወቀስበት አይደለም። እእ። የሁሉም የወል በሽታ ነው።
  • ·       አፋር እና ልማቷ።

አፋርን ብቻ ሳይሆን ወሎንም ሳያካልል ከጁቡቲ ተነስቶ ለታላቋ ትግራይ ህልውና ላይ የታቀደው የባቡር ጉዞ ዝበታዊ ሁኔታም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጉዳዩን እንደማያውቁት ገልጸው በሚዛናዊነት እንደሚፈተሽ በዚህ ስብሰባ ፍንጭ ተገኝቷል። ቢያንስ ከተሞችን ረግጦ ማለፍ እንዳለበት። ይህ ማለት የወሎ ጉዳይ በዚህ ወቅት ሊነሳ ባይችልም ለአፋር የሚሰጠው ፍትህ ለወሎም አይቀሬ ስለመሆኑ ግድ ይላል። በዚህ እንግዲህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርብ ሴራ አከርካሪው ይመታል ማለት ነው። አገርን ያቆዬ የአንድ አካባቢ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ደሙን፤ ኑሮውን ገብሮ ነው ያቆያት ይህቺን ኢትዮጵያ።
  • ·       የህግ የበላይነት።


በህግ የበላይነት "ንጉስ አይከሰስ" ሆኖ የኖረው ኢህአድግ ለህግ መገዛት ግድ እንደሚሆንበት፤ ከህግ በላይ ማንም እና ምንም እንደሌለ በአጽህኖት በዚህ ጉባኤ ላይ ተነስቷል።  

እኔ እንዲያውም የአዲስ አበባው ሆነ ሌላም ቦታ ያለው የህግ ተቋማት ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች ህግን ሊያሰከብሩ የሚችሉበት ሥርዓት ከሌለ ስለምን ዩንቨርስቲው አይዘጋም ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር በ2014፤

በተጨማሪም ኢትዮጵያን በራሷ በተፈጥሯዋ ሁልጊዜም እንደምለው ኢትዮጵያ በተጻፈ ህግ እንደሚታዳደሩት አገሮች በተጻፈ ህገ መንግሥት፤ ባልተጻፈ ህገ መንግሥት እንደሚታዳደረትም ባባህላዊ ትወፊታዊ ሪቷላዊ ህግ የምትተዳደር አገር ስለሆነች አብሶ ሲጠቀጠቅ የኖረው የተጻፈው ህገ መንግሥት ሥራ እንደ ጀመረ ማገናዛቢያ ፍንጭ አግኝቸበታለሁኝ። በዚህም ሐሤት አድርጌያለሁኝ።
  • ·       ታማኝነት።

በዚህ ጉባኤ ላይ የሃላፊነትን ታማኝነት በእጅጉ አስፍተው ገልጸውታል ባለቅኔው ጠ/ ሚር። እኔም ቀድሞ የኦህዴድ የጽ/ቤት ሃላፊ በነበሩበት ቦታ ሁሉ ስለው የነበርኩት ነው። ዋናው የዶር አብይ አህመድ ሰብዕና ለራሳቸው፤ ለአገራቸው ለኢትጵያ ለአፍሪካም ጭምር የሚከፍሉት ጉልህ መስዋዕትነት ቢኖር ታማኝ አገልጋይ፤ ታማኝ ተቆርቋሪ ለመሆን የቆረጡ ስለመሆናቸው ነው። ለዚህ ነው እኛን የሚያንጫጨን ነገር ለአሳቸው ኢምኒት የሚሆነው እኛ „ወርቅ ህዝብ“ እንዴት ይባላል ስንል እሳቸው ህዝብ ታማሁበት ስላላቸው "ያድርግላችሁ፤ ያዝልቅላችሁ እንደ አፋችሁ ያድርግልን" በሉ ሲሉ በቅንነት ነበር የተናገሩት።

በነገራችን ላይ ሌላ ቦታ ኩሩ፤ ጀግና ፤ ፍቅር፤ ፈርጥ፤ ታማኝ ህዝብ ሲባል አያንገበግበንም? ግን ለምን? ገና ነን አንደኛው መርዝ ከውስጣችን ስለመኖሩ ሁላችንም አላመንበትም። ያ መተማማኛ ሲገኝ ነው ደግሞ እባካችሁ እናውጣው ተብሎ ደግሞ ተማህጽኖው የሚቀጥለው።

እኔ በግሌ ታማኝነትን ለወላጆችም፤ ለባለትዳሮችም፤ ለልጆችም በጻፍኳቸው መጻህፍት ላይ በአጽህኖት አበክሬ እራሱን አስችዬ ሰርቼበታለሁኝ። ለእኔ ከሁሉም በላይ በላይ በላይ ታማኝነት ነው መለኪዬ። አንዲት ቀን ታማኝነቱን ያጣሁበት ሰው በዛ ሰው መንፈስ ውስጥ ለመቀጠል ፈቃደኛ ሆኜ አላውቅም። አላዳምጠውም። የሰው መለኪያ ዋናው ታማኝነት ነው። ሁለተኛው የአስተሳስብ ለምነት።
  • ·       ተጠያቂነት።

ተጠያቂነትን በሁለት መልኩ ነው ቀርቦ ያገኘሁት። የህዝብ የራሱ ተጠያቂነት  እና የመሪነት ተጠያቂነት። ተጠያቂነት እኮ ሲሸሽ የተኖረ ገመና ነበር። ህዝብ ተጠያቂ በሚሆነበት ብቻ ሳይሆን ተጠያቂ በማይሆንበት ጉዳይም ይከሰሳል፤ ይወነጀላል፤ ይቀጣል፤ ይገለላል፤ ከተውልድ ይነቀላል፤

ተጠሪ መሪ ተወናይ ግን በኢትዮጵያ በቃ እንደ አምልኮ የሚመለክ ነው። ህዝብ እመራለሁ ብሎ ቃል ያፈረስ ስለምን ተብሎ አይጠዬቅም?ህዝብ እመራለሁ ብሎ ሲከሽፍበት እራሱን ነፍሱን ያወጣል መስዕውትነቱ ደግሞ የእኔ የአመራር ክህሎት ማነስ ነው ብሎ አይቀበልም፤ ይቅርታም አይጠይቅም።  እንደገናም ተሰዋልኝም አለበት። የጎንደር መከራም የኸው ነው። ደግሞ በዙር ለእርድ ቅረብልኝ። የሚገርም ጉዱ ይሄ ነው። ያን ስለምን እንዲህ ይሆናል ብሎ የሚጠይቅ ሞጋች ሃሳብ ከመጣ ደግሞ ስደቱን መወስን አለበት ቀድሞ። አገር ውስጥ ብቻ አይደለም ውጪም። የውጪው ይጎፈንናል። ሌሎቹ ስለሚከፈላቸው ነው። እኛ እኮ የሚከፍለን የለም ተጀመሮ እስከሚጨረስ ሁለመናችን ገብረን በነፃ ነው እምናገለግለው ... ራሳችን ረስተን ... 

ተጠያቂነትን የተቀበለ ሊሂቅ፤ ለመቀበል የፈቀደ ሊሂቅ አይቼ አላውቅም። ሁሉም ንጹህ ነው፤ ሁሉም ቅዱስ ነው። ሁሉም ከሰማያ ሰማያት የወረደ መንፈስ ቅዱስ ነው። ደጋፊውም ይህን አምኖ ነው የሚቀበለው። ለዚህም ነው አትንኳቸው ብትነኳቸው ወዮ የምናባለው። ይህ ደግሞ አላዳናቸውም። አጋጣሚዎች ከሚያሰገኙት ጭብጭባ በዘለቀ ቋሚ የሆነ የመንፈስ ሃብትን ለማግኘት ጋዳ ነው ብርድ የሚያንዘፈዝፈው። 
  
በዬትኛውም ሁኔታ የሚጨበጨበለትን ሰው መንካት እራስን ለመማገድ መፍቀድ ነው። እነሱ እንዲናገሩ፤ እንዲጽፉ፤ እንዲመሩ፤ እንዲያወያዩ ሌላውን እስከ አሻቸው እንዲተቹ፤ እንዲያብጠለጥሉ እንጂ ስለሚናገሩት፤ ስለሚመሩት፤ ስለሚያወያዩት፤ ስለሚጽፉት ጉዳይ እንክርዳድ እና ምርጥ ዘር ተንተርትሮ ይሄ ልክ አይደለም ማለት አይቻልም። አንዲት ቅንጣት ትችት ዜግነትነት ያሳጣል። ሁሉም ትክክል ነኝ ብሎ ነው የሚያስበው።

እርግጥ ነው በአንድ ነገር ውስጥ አባል ስትሆን አይታይም። አንድ አልኮህል የሚጠጣ ሰው ስካርን እሱ ሳይጠጣ ሌላው ሰክሮ እንዴት ጎርፍ ሆይ የመሬት ገነት ነህ ብሎ ለሽ ብሎ መተኛት ሲችል ያን ጊዜ ያን ያዬ እኔም ለካ እንዲህ ዝርክርክ ነው የምለው ብሎ ሊመለስ ይችላል። ህሊናው ከኖረ። ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ያልተሻለ መርዝ ተሸክመህ መንፈስን በሃይል ጠቅልዩ ካልያዝኩ ብለህ እዬነገደህ ወያኔ አንባገነን ነው ማለት ያስገምታል።

ምን ማለት ነው ይሄ? ወስጥ ሲኮን አይታወቅም ስህተት እዬሠራን እንዳለን።
በጣም የማዝነው የኢትዮጵያ እናቶች በ43 ዓመት ውስጥ ሚሊዮኖችን የመሃጸን ፍሬ ገብረዋል። ለዚህ አንድም የፖለቲካ ድርጅት፤ አንድም ሊሂቅ ሃላፊነቱን ሊወስድ አይፈቅድም። ግን አክተሮቹ አሁንም አሉ፤ አሁንም ተደራዳሪ ናቸው። ፈገግ የሚያሰኘውም ይሄው ነው። ነገም  የኢትዮጵያ እናቶች ለእነሱ ገብርዲን እና ከረባት ልጆቻቸውን በረድፍ እንዲያሰልፉ ይገደዳሉ። ይቅርታ እኮ አልተጠዬቁም። ምህረትም አላገኙም። ይሄ ጉዳይ በውል መልክ ሊይዝ ይገባዋል ባይ ናቸው ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ። እነሱ ደግሞ አድርገውታል ከወያኔ ሃርነት በስተቀር። እሱ የወሰነውን ሽሮ ነው አሁን መጪ እያለ ያለው። 

ከዚህ ጋር የተያዙ የደባ የሴራ የአድማ ጉዳይ ከደም ጋር የተዋህዱ ናቸው በግራ ዘመም ፖለቲካ። ደሙ ወጥቶ አዲስ ደም ካልገባ እኔ እንጃ … ፈተናው ከባድ ነው።
  • ·       90%

አብዛኛው በሚለው ነው እኔ እምስማማ። ምክንያቱም በደንቢ ዶሎ ጉባኤ ላይ የዬሁትን ስላዬሁኝ። የደንቢደሎው ጉባኤ በፍጹም ሁኔታ ከአዲሱ መንፈስ ጋር ነው ማለት አልችልም። ጽፌበትምአለሁኝ።  ከዚህ ላይ ልቤን የነካው ከእንግዲህ ወደ ዋላ መመለስ እንደማይችል ለ100 ለዓመት ህልመኞች መርዶ ተነግሯቸዋል። ዝጉጁ አይደለንም ነው ያሉት ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ። እጅግ ቆርጠዋል። ወስነዋል። ከዚህ ጋር የአያያዙት የሥርጉትሻ ሞቶ ጋር ስምም ሆኗል። ለዚህም ነው ከህሊናዬ የምወዳቸው። አብዝቼም የምሳሳላቸው። የኢትዮጵያ እናቶች ከእንግዲህ ስለ ልጆቻቸው በሰላም ወጥቶ ስለመመለስ ማሰብ እና መጨነቅ የለባቸውም ነው ያሉት። ተመስገን!አሁን ያለው መንደፋደፍ ጊዜያዊ ነው ... 
  • ·       የግጭት መናህሪያ ለመሆን መፍቀድ ትርፍ እና ኪሳራው።

ይሄ ለአፋር ክልል አለርም ነው። ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። አፋር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ልቡን ገጥሞለታል። ለምንስ ተረሳን፤ ባቡሩ እኛን ትቶ አለፈ ወዘተ የብሶት መዝመር ለመዘመር እንደ ፈለጉ አላውቅም። ይሄን ያህል ጥብቅና ከሳቆማቸው። ለዘለ- ዓለም ይኑርልን እያሉ እኮ ነው የተደመጡት። ሺ ዓመት ንገሥልን ወያኔ ሃርነት ትግራይ እያሉ ነው።  ስሊዚህ ይህ ቅኔ እራሳችሁን ላለማጥፋት አትተባበሩ ነው። ቀጣዩ ድራማ ደግሞ አፋር እንደሚሆን ራቅ ብለው የተነበዩት ይመስላል … ለነገሩ ብዙ ነገራቸው ምርምምር ተኮር ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኤን ለማጥቀት ከቢ እስከ ዜድ ያሉትን ያቅፋል። ሌላው ጉዱን የሚያውቀው ከተሸነፈ በኋዋላ ዘግይቶ ነው። ይህንንም በ2014 ዘሃበሻ ላይ ወጥቶልኝ ነበር። ይባረኩልኝ። 

ይሄ ሃሳብ የሚረዳው ይበልጥኑ ለጎንደር ነው። አሁን ጎንደር ያን ሁሉ መከራ አሳልፎ እንዴት ለሌላ ፓርቲ አባልነት እራሱን እንዳጨ ያማል። የአርበኛ አበበ ካሴን ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ ግርም ነው ያለኝ። በእነሱ ጥልቆነት ሳቢያ ነው ጎንደር ጭፍጨፋን ያስተናገደው። ምኔ ብሎ እንደሆነ ግራ ያጋባል? ስለምንስ ብሎ እንደ ተማገደ አርበኛው ገርሞኛል። ግራሞቴም እስከ አሁን አላለቀም። ትኩስ ነው እንደ ማለት። እባካችሁን ጎንደሬዎች ማገዶ አትሁኑ። ያን መከረኛ ህዝብም እናንተ እዬሄዳችሁ ጥልቅ ባላችሁ ቁጥር አትማግዱት። በኢህአፓ ያለቀው አይበቃንም? ጎንደር ናፍቆቴ እባክህን ወስን። ቁረጥ! ከፋኝ ያለውን ሁሉ አታስጠጋ። ሁሉም ጫካ አለው። ከከፋው በዬጫካው ይመሽግ። 
  • ·       ጎንደር ሆይ!

ይሄ ህብረ ብሄር ፓርቲ ስለሚባለው ማገዶነት ከልብ ሆነ አስብ እና ማገዶነትህን አቁም። ስንት ትውልድ ይታጨድ። ፍሬ ቀርቶ ቡቃያ እኮ የለህም። ስንት ጊዜስ ለሌላ አንጋች ሁነህ ትዘልቀዋለህ? እስከመቼ? ጅልነት ነው። ፍጹም ጅልነት። ብልሆችን አለዬህንም? መገበሩን ለአንተ በምሥራች ሰዓት ጉልህነታቸውን በጉልህ ጥያቄ አጉልተው ይዘው ነው ብቅ ያሉት። ነገም ታያለህ ማን መንበር ላይ ማን ትቢያ ላይ እንደሚቀር … ዕድሜ ይስጥህ። ሚዲያ ላይ ያለውን የግለት ሳቦታጅ ከልብህ ሆነህ ታደምበት። ቢያንስ ከእንግዲህ ልብ ይስጥህ! የግጭት ዓዋድ ትውልዱንም ታሪካዊ ምድሩንም አታድርገው። አብሶ ቅማንቶች ክልብ ሆናችሁ ስሙ። ዘመድ የማይሆነው ዘመድ አይሆንም። በፍጹም። ከአብይ በላይ መንፈስ ማለም ለሞት መቃብርን መቆፈር ነው። 
  • ·       አዋሽ ታሟል አሉ።

አዋሽ በአረንጓዴ አረም በሽታ አልጋ ላይ ውሏል። ይህን ሳዳምጥ ታቦቴ ሎሬት በአጸደ ገነት የታመመ ያህል ነው የተሰማኝ። ለነገሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አዋሳ ላይ „በርበሬ ታመመ፤ ቡና ታመመ“ ሲባሉ። "አዬ እናንተ ምን ያልተማመ ነገር አለእና እኛስ እራሳችን ታመን የለም፤ እኔ እንዲያውም ወንዞች ወደ ደም ይለወጣሉ ብዬ ነበር። ታውቃላችሁ አይደለምን?  የአቤል ደም እንደሚጪኽ“ ነበር ያሉት። አዎን ኢትዮጵያ ውስጥ ያልታመመ ሰው እና የተፈጥሮ ነገር መፈለግ ቀላሉ ይመስለኛል።

ተራራውም ሃይቁም ወንዙም፤ መስኩም ምድሪቱም፤ እጽዋት፤ እንሰሳት፤  አእዋፋትም፤ ቅርሱም ትውፊቱም ታመዉ ነው የኖሩት። እራሷ አላዛሯ ኢትዮጵያ ሳትቀር። ሁላችንም። ሁለመናችን እኮ ተሸቅጦ ነው የባጀው። እግዚአብሄር ምህረትን ያውርድልን አሜን።
  • ·       መልዕከተኛ።

አንድ ወጣት እንዳቀረበው ጥያቄ፤ በጣም ልቤን የነካው ጉዳይ መልዕክተኞችን ሁሉ በዚህ ስብሰባ ልካቸውን ነግረዋቸዋል። አክሰሱ ካለህ ለምታገኛቸው ንገራቸው ምን ታደርጋለችሁ እዛ ብለህ። ክላሽን አይደልም ሰውን የሚሠራ፤ ሰውን የሚሠራ ሰላም እና ስልጣኔ ነው። ይህን የሚመራ የሃሳብ ልቅና ፈጣራ ነው ዕድምታው ይሄ ነው። ባለቅኔው ጠ/ ሚኒስተር እንዲህ ናቸው። መንጩን ነው የሚያጠኑት። 
  • ·       ቁርጥ ያለ ብይን።

ሌቦችን ብታሞቱ ይሻላችል ነው ያሏቸው። ዋው! ለነገሩ ሌባ ሆኖ ከመፈጠር ከሞትም መቃጠል ይሻላል። ምን ያልተሰረቅ አለና? ሥነ - ልቦናው? ባህሉ? ትውፊቱ? ትሩፋቱ? መሬቱ? ደንበሩ? ማንነቱ? ቅርሱ? ውረሱ? ጄነሬተሩ? ወንዙ? ተራራው? ሃላፊነቱ? ሰብዕናው? አንጀት ጉበቱ? ጾታዊ ቅጥፈቱ? ህጉ? ድንጋጌው? አፈሩ፤ ታሪኩ ... በቃ ስስታሙ ሁሉ ሲጎመጅ የባጀበትን ነገር ወሰደው፤ ሰረቀው ከምንል ይልቅ ጋፈፈው አጋሳሱ ማለት ይቀለል … ምን … የቀረ አለና …

  • ·       ምስጋናው።

ምስጋናው ልብ ይነካ ነበር።
„ቢያንስ ሰርቀን እንደማናስከፋችሁ በሙሉ ልብ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ“ ነበር ያሉት። መስረቅ መርዝ ስለሆነ መርዙን ከደማችሁ ለማውጣት የቀደምት ሌቦች ማካካሻ የሰረቃችሁትን ገንዘብ ለህዝብ አገልግሎት ለማዋል ቁረጡ፤ ወስኑ፤ በዛ በሰረቃችሁት ገንዘብ ለህዝቡ ውሃ፤ መንገድ፤ ት/ ቤት ጤና ተቋማትን በመገንባት ከደማችሁ ጋር የተቀላቀለውን መርዝ አውጡት። ያን ካለደረጋችሁ ዕድሜ ልካችሁን በህሊናችሁ ተሰዳችሁ ትኖራለችሁ ነበር ያሉት።

ከሁሉም በላይ አፋር መስረቅ አይደለም የተሰረቀን ተካፍሎ መኖርን ስለማይመርጥ እንደ ትውፊት ለመኖር ወስኑ በማለት እሳርገዋል።

በዚህ ውይይት ውስጥ ስርቆት ሲባል የመንፈስ፤ የአርበኝነት፤ የጀግንነት፤ የብልጥነት ሌብነት ሁሉ አብሮ ነው መስምር እንዲይዝ የሚፈለገው። የግጭቶች መንስዔም ይኸው ነውና። ሌላው የማገዳል በሌላው ማገዶነት ሌላው ይከብራል ይገሳል። ጨዋታው ይሄው ነው። ጎንደር ስሟ በሚዲያ መነሳት ከቀረ ወደ ስንት ወር ሊሆናት ነው ያው የእስረኞችን መደመር አድምጠናል … ያ ለግብር ይውጣ የተቀነባባረ ለጠፍ ነው …

የሆነ ሆኖ ለንጡሁ ለአሜኑ መንፈስ ተዚህ ከገዳማዊቷ ሠፈር ተሲዊዝ መልካም የሥራ፤ የብሥራት፤ የሐሤት ዘመን እንዲሆን ተመኘን! የድል እና የሙሉ ጤና  እድሜ ጋር ይስጥልኝ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ።
የማቱሳላን ዕድሜ ይስጥልኝ ለባቅኔው ጠ/ ሚር ለዶር አብይ አህመድ።

የ እርቅ አርበኞቻችን ነብስ ጌታችን መዳህኒታችን ይጠብቅልን! አሜን!
የማቱሳላን ዕድሜ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ኤልሻዳይ ይስጥልኝ! አሜን!


የኔዎቹ ቅኖቹ መሸቢያ ጊዜን ከልቤ መንፈስ ተላከላችሁ። ኑሩልኝ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።