ልጥፎች

ከኦክቶበር 31, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አደብ ለወዘተረፈ።

ምስል
ወዘተረፈ። „የእግዚአብሄረ ቃል ወደ ሰለሞን መጣ፤ --- እንዲህ ሲል ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት በሥርዓቱ ብትሄድ፤ ፍርዴንም ብታደረግ ትመላለሰብትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ።“ መፅሐፈ ነገሥት ምዕራፍ ፮ ከቁጥር ፲፩ እስከ ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 31.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        መ ነሻ። „Hiber Radio: የአቻም የለህ ታምሩና የሁንዴ ዱጋሳ ሞቅ ያለ ውይይት ( ክፍል አንድ ) ያድምጡት ያሰራጩት“ http://www.hiberradio.com/?p=5047 መነሻዬ ይህ ነው። በዚህ ቃለ ምልልስ መነሻነት ውስጤ የሚለኝን ነገር ለማለት ነው የፈለግኩት። በክርክሩ ላይ አልታደምም። ነገር ግን በዚህ ውስጥ ያሉ ቁምነገሮችን በማስተዋል ማዬት ይገባናል ብዬ አስባለሁኝ። ክፍል ሁለትን መጠበቅ አላስፈለገኝም። ምክንያቱም ሙግቱ ጠቅላላ ይዘቱን አይደለም እኔ ልሄድበት የፈለግኩት። እኔ አስተያዬት ልሰጥ የምፈልገው የሥር - ነቀል ለውጥ ፍላጎት እና ያለው ተጨባጭ አቅም ስለገረመኝ ብቻ ነው ይህን መጻፍ የፈልግኩት። የምንፈልገው እና አለን የምንለው ነገር ይገረመኛል ሁልጊዜ። የውይይቱ መንፈሱ ኢህአዴግ ራሱን አፍርሶ እንዬው ስለሆነ ያ በመዳፋችን ካለው አቅማችን ጋር ሚዛን ውስጥ ለማስቀመጥ የሚቸግርበት አመክንዮ መኖሩ ብቻ ሳይሆን በመቻቻል እና አፍርሶ በመገንባት ያለውን የራሴን ዕድምታ ለማቅረብ ነው። ይልቅ የአክቲቢስት ሁንዴ ዱጋሳ የጭብጥ መነሻ ለእኔ ስሜት ቅርቤ ሆኖ አገኝቻለሁኝ። አሁን ኦነግ አረካሁም ስላለ ትጥቅ አልፈታም ብሏል፤ ውጤቱን አብረን እምናዬው ይሆናል። 27 ዓመት ሙሉ አንድም የነጻነት ሃይል አን