ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 11, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

EBS መሥራቹን አጣ፨

ምስል
  የምንኖረው #ለጤዛዊ ጊዜ ለአፍታ ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       ይቺ ዓለም እንዲህም፤ እንዲያም ናት። ስትሞቅ /// ስትቀዘቅዝ፤ ለብ ስትል፤ /// ፍላት ሲያሰኛም እንዲህም እንዲያ ሲያሰኛት ትቆይ እና መራራ ስንብትን ጎምዛዛ ጠምቃ እንዲህ #ዕንባ ታራጫለች። ለብሰን - ስንታይ፤ ቁመን - ስንታይ፤ ስንሞግት ///ስንሞገት፤ ስንስቅ // ሲከፋን ቋሚ ጊዜ የተሰጠን ይመስለናል። ግን የአፍታወች ነን።    ጸጥ እረጭ ካለው ቅዝቃዜ ውስጥ ከተማችን ስለመሆኑ፤ ትዳር ጎጇችን ስለመሆኑ በህይወት እያለን ትዝ የማይለን ብዙወቻችን ነን። ጥልቀት ያለው መራራ ስንብት የፍጥረታት ሁሉ ተመስጥሮ አብሮን የተፈጠረ ስለመሆኑ እንዘናጋለን። ለዚህም ነው ሞት ሁልጊዜ አዲስ የሚባለው።   የሚዲያ ሰብዕና በፈተና #የታጠረ ነው። የመጨረሻው የፈተና ተጋድሎ እንዲህም፤ በዚህም ሁኔታ ይጠናቀቃል። የሚዲያ ተግባር በብክነት የተሞላ ነው። የሚዲያ ሰብዕና የመጨረሻው እረፍት በዘለቄታ እንዲህ ይጠናቀቃል። እንዲህም ይደመደማል። ይደመደማልም። የሠራ ሰብዕና፤ የተጋ ሰብዕና፤ በአዲስ ጎዳና፤ እሸት ሃሳብን አዝምሮ፤ አብስሎ ያሰበለ ሊቀ - ትጉኃን #አሻራው የተሟላ ስለሚሆን፤ ሞተ ከሚባል፤ ከድካሙ #አረፈ የሚለው ትርጉም የሚሻል ይመስለኛል። ሁላችንም ከጽንሰታችን ጀምሮ ተጓዦች ነን። እንከታተላለን።    ትልቅ ሰው በስጋ ቢለይም ሁልጊዜ ተግባሩ፤ ትጋቱ በቋሚነት ይቀጥላል። በብዙ ሁኔታ በዘርፋ በርካታ ባለሙያወችን በማብቀል እናም ተተኪ በመፍጠር የትውልድ በሆነ #ቀና ዕሳቤ ለትውልድ የሚሆን፤ የሚበረክት ተግባርን ፈጽሞ፤ በታታሪነት ተግቶ፤ አስብሎ የአረፈ ሰብዕና በሚሊዮኖች ልበ - ህሊና ው...

#ሁለት ቤተ - አብኖች #ኢህአፓን ወክለው የ2018ቱን ዓም ምርጫ እንደምወዳደሩ አስታወቁ።

  #ሁለት ቤተ - አብኖች #ኢህአፓን ወክለው የ2018ቱን ዓም ምርጫ እንደምወዳደሩ አስታወቁ።   የዘገባው ምንጭ #ሪፖርተር ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። የፓርላማ አባሉ ዶር አበባው ደስአለው እና ዶር. ይህዓለም ታምሩ (የሚያምር ሥም።) ሁለቱም ቤተ - አብኖች የነበሩ ሲሆን አሁን ኢህአፓን ወክለው በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት ውስጥ #ሊወዳደሩ እንደወሰኑ ዘገባው ያመለክታል። በተጨማሪም ዶር. ይህዓለም ታምሩ የአዲስ አበባ የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ እንደነበሩ መረጃው ይጠቁማል።   በውነቱ የእኔ ሁሉም ሚዲያ ጸጋዬ ራዲዮን ጨምሮ ዘገባ አይሠራበትም። ስለሆነም የምርጫ ዘገባም፤ በምርጫ ዙሪያም ያሉ ንቅናቄወችን በጥሞና መከታተሉ ይበጃል። ባለፈውም የፈጸምኩት በዝምታ ነው። አንዳንድ ኮሚክ ሁነት ሲገጥም ብቻ ነበር ሐተታ እጽፍ የነበረው። የተወዳደሩክት #ለማሸነፍ አልነበረም ልሸነፍ ነው የሚል ቧልት አዳመጥኩና ፃፍኩኝ። ሌላም "የብልጽግና አባል #አይደለሁም ግን ወክዬ እወዳደራለሁ" ያሉም ተወዳዳሪ እንዲሁ ገርሞኝ ጽፌ ነበር።    እንጂ በምርጫ ዙሪያ ብዙም መሳተፍ አልሻም። የሆነ ሆኖ በኢህአፓ ላይ ያለው የሚዲያ ጫና ገርሞኝ ስለነበር፤ አንጋፋ መሪወቹንም የኢህአፓ በአካል ስለማውቃቸው በህይወት እያሉ ወጣት ተተኪወቻቸው በፓርላማ የመወዳደር ዕድላቸውን እንዳያፈሱ ትናንት ዘለግ አድርጌ መፃፌ ይታወቃል።    በተጨማሪም "ለህዝቤ የፈየድኩት ነገር ስለለ መጪውን ምርጫ አልሳተፍም" ያሉትን ዶር ደስአለኝ ጫኔ ከምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አክብሬ ምክንያታቸው ስላላሳመነኝ ትናንት በዚህ ዙሪያ ስለፃፍኩኝ፤ የጓዶቻቸው ለመሳተፍ #መፍቀድ ተያያዥ ስለሆነ ነው ለመዘገብ የወደድኩት...