EBS መሥራቹን አጣ፨
የምንኖረው #ለጤዛዊ ጊዜ ለአፍታ ነው።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።


ይቺ ዓለም እንዲህም፤ እንዲያም ናት። ስትሞቅ /// ስትቀዘቅዝ፤ ለብ ስትል፤ /// ፍላት ሲያሰኛም እንዲህም እንዲያ ሲያሰኛት ትቆይ እና መራራ ስንብትን ጎምዛዛ ጠምቃ እንዲህ #ዕንባ ታራጫለች። ለብሰን - ስንታይ፤ ቁመን - ስንታይ፤ ስንሞግት ///ስንሞገት፤ ስንስቅ // ሲከፋን ቋሚ ጊዜ የተሰጠን ይመስለናል። ግን የአፍታወች ነን።
ጸጥ እረጭ ካለው ቅዝቃዜ ውስጥ ከተማችን ስለመሆኑ፤ ትዳር ጎጇችን ስለመሆኑ በህይወት እያለን ትዝ የማይለን ብዙወቻችን ነን። ጥልቀት ያለው መራራ ስንብት የፍጥረታት ሁሉ ተመስጥሮ አብሮን የተፈጠረ ስለመሆኑ እንዘናጋለን። ለዚህም ነው ሞት ሁልጊዜ አዲስ የሚባለው።
የሚዲያ ሰብዕና በፈተና #የታጠረ ነው። የመጨረሻው የፈተና ተጋድሎ እንዲህም፤ በዚህም ሁኔታ ይጠናቀቃል። የሚዲያ ተግባር በብክነት የተሞላ ነው። የሚዲያ ሰብዕና የመጨረሻው እረፍት በዘለቄታ እንዲህ ይጠናቀቃል። እንዲህም ይደመደማል። ይደመደማልም። የሠራ ሰብዕና፤ የተጋ ሰብዕና፤ በአዲስ ጎዳና፤ እሸት ሃሳብን አዝምሮ፤ አብስሎ ያሰበለ ሊቀ - ትጉኃን #አሻራው የተሟላ ስለሚሆን፤ ሞተ ከሚባል፤ ከድካሙ #አረፈ የሚለው ትርጉም የሚሻል ይመስለኛል። ሁላችንም ከጽንሰታችን ጀምሮ ተጓዦች ነን። እንከታተላለን።
ትልቅ ሰው በስጋ ቢለይም ሁልጊዜ ተግባሩ፤ ትጋቱ በቋሚነት ይቀጥላል። በብዙ ሁኔታ በዘርፋ በርካታ ባለሙያወችን በማብቀል እናም ተተኪ በመፍጠር የትውልድ በሆነ #ቀና ዕሳቤ ለትውልድ የሚሆን፤ የሚበረክት ተግባርን ፈጽሞ፤ በታታሪነት ተግቶ፤ አስብሎ የአረፈ ሰብዕና በሚሊዮኖች ልበ - ህሊና ውስጥ ቋሚ ነዋሪ ነው።
እግዚአብሄር አምላክ የአቶ አማን ፍሰሃጽዮንን እረፍት የጽድቅ፤ የሰላም ያድርገው። አሜን። ለመላ ቤተሰቦቻቸው፤ ለባልደረቦቻቸው እና ለአድናቂወቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁኝ። #ተለመደ እንዲህ #ህመም ሳይሰማ ድንገት መለየት። በዘርፋ፤ ለዘርፋ ላበረከቱት ሁለገብ ተሳትፎ እና ትጋት #ቅኔዋ ኢትዮጵያ ስታመሰግናቸው ትኖራለች። ፈላስፊት ኢትዮጵያም እንዲህ በበቃ ዕሳቤ የገዘፈ የትጋት አብነቷን ስታጣ ይቀርባታል እና እግዚአብሄር ያጽናት። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/02/ 2026
የሃዘን ዳርቻ የአድርገው። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ