#ሁለት ቤተ - አብኖች #ኢህአፓን ወክለው የ2018ቱን ዓም ምርጫ እንደምወዳደሩ አስታወቁ።
የዘገባው ምንጭ #ሪፖርተር ነው።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
የፓርላማ አባሉ ዶር አበባው ደስአለው እና ዶር. ይህዓለም ታምሩ (የሚያምር ሥም።) ሁለቱም ቤተ - አብኖች የነበሩ ሲሆን አሁን ኢህአፓን ወክለው በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት ውስጥ #ሊወዳደሩ እንደወሰኑ ዘገባው ያመለክታል። በተጨማሪም ዶር. ይህዓለም ታምሩ የአዲስ አበባ የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ እንደነበሩ መረጃው ይጠቁማል።
በውነቱ የእኔ ሁሉም ሚዲያ ጸጋዬ ራዲዮን ጨምሮ ዘገባ አይሠራበትም። ስለሆነም የምርጫ ዘገባም፤ በምርጫ ዙሪያም ያሉ ንቅናቄወችን በጥሞና መከታተሉ ይበጃል። ባለፈውም የፈጸምኩት በዝምታ ነው። አንዳንድ ኮሚክ ሁነት ሲገጥም ብቻ ነበር ሐተታ እጽፍ የነበረው። የተወዳደሩክት #ለማሸነፍ አልነበረም ልሸነፍ ነው የሚል ቧልት አዳመጥኩና ፃፍኩኝ። ሌላም "የብልጽግና አባል #አይደለሁም ግን ወክዬ እወዳደራለሁ" ያሉም ተወዳዳሪ እንዲሁ ገርሞኝ ጽፌ ነበር።
እንጂ በምርጫ ዙሪያ ብዙም መሳተፍ አልሻም። የሆነ ሆኖ በኢህአፓ ላይ ያለው የሚዲያ ጫና ገርሞኝ ስለነበር፤ አንጋፋ መሪወቹንም የኢህአፓ በአካል ስለማውቃቸው በህይወት እያሉ ወጣት ተተኪወቻቸው በፓርላማ የመወዳደር ዕድላቸውን እንዳያፈሱ ትናንት ዘለግ አድርጌ መፃፌ ይታወቃል።
በተጨማሪም "ለህዝቤ የፈየድኩት ነገር ስለለ መጪውን ምርጫ አልሳተፍም" ያሉትን ዶር ደስአለኝ ጫኔ ከምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን አክብሬ ምክንያታቸው ስላላሳመነኝ ትናንት በዚህ ዙሪያ ስለፃፍኩኝ፤ የጓዶቻቸው ለመሳተፍ #መፍቀድ ተያያዥ ስለሆነ ነው ለመዘገብ የወደድኩት።
ዶር አበባው ደስአለው የሚወዳደሩት በ፮ኪሎ ሽሮ ሜዳ መሆኑም ከሪፖርተር ዘገባው ተረድቻለሁኝ። ዶር አበባው የጨመቱ፤ የተረጋጉ እና ሃሳባቸውን አደራጅተው ለማቅረብም የማይቸገሩ መሆናቸውን አስተውያለሁኝ። ይህ አቅምን #እንዲበርደው ከማድረግ ተጨማሪ ዕድልን መፈለግ፤ አማራጮችን አይቶ መወሰን መልካም ይመስለኛል። ይመስለኛል እምለው ከሌላ የፖለቲካ ድርጅት ወደ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ሲመጣ ያለውን ፈተና ከሰሞኑ አብራርቸዋለሁኝ። አልመለስበትም።
ለኢህአፓ የመወዳደሪያ አቅም ግን ጠንከር ያለ አቅምን የመሰብሰብ፤ የማደራጀት እና የመምራት አቅሙን በተለይ #ለምርጫው ወቅት የፋመ የተሳትፎ ሁነት ሊፈጥርለት ይችላል። ከዚህ በላይ ባልሄድ ምርጫዬ ነው።
እንግዲህ "#ይሁነን ብለን #የእኛ ተወዳዳሪወች የሚሳተፋበትን #እዬለቀቅን // #ተፎካካሪወችን እናሳትፋለን" ያሉት ጠቅላይ ሚር አብይን ቃላቸውን ለመተርጎም ያላቸውን የመቻል አቅም የምንፈትሽበት አጋጣሚ ይሆንልናል። ይህ ብቻ ሳይሆን ለፓርላማ አባላት ጥያቄ አቀራረብ፤ መልስ አሰጣጥ ላይም የህዝብ ተወካዮችን #እኩል የማየቱ አቅም #ስስ ሆኖ በተደጋጋሚ አይ ነበር። ስለሆነም ለቀጣዩም በአዲሱ ፓርላማ ሞጋቾቻቸውን በቅንነት፤ በቻይነት፤ እና በሆደ - ሰፊነት ለማስተናገድ ያለፋትን የፓርላማ ቆይታቸውን ጊዜ ሰጥተው፤ አይተው፤ መርምረው ግድፈቶችን ቢያርሙ ጥሩ ይመስለኛል።
በጣም ፓርላማውን ሞናትነስ የሚያደርገው የጥያቄ፤ የአስተያዬት አቅራቢወች #የመግቢያ ርዝመት ነው። ይህም እርምጃ ቢወሰድበት ጥሩ ይመስለኛል። ቆይታው ረጅም ነው። ፬ ሰዓት ነው። ብዙውን ጊዜ የሚገድለው የመግቢው አድሬሲንግ ድግግሞሽ መሆኑ ነው። እጅግ አሰልቺም ነው።
ለተወዳዳሪወች ይቅናችሁ። መልካም የውድድር ዘመን። አሜን።
እነ ቅንነት እንዴት ዋላችሁልኝ? ደህና አምሹልኝ። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን። ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/02/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ