#እኔን። በዛ በመተማ ቃጠሎ እያገለገለ በግፍ ታግቶ የተገደለ ታናሽ ወንድማችን ነው።
#እኔን ። በዛ በመተማ ቃጠሎ እያገለገለ በግፍ ታግቶ የተገደለ ታናሽ ወንድማችን ነው። #እናትህን #አያድርገኝ ። #አዳኝ #ታድኖ እንደምን #በጭካኔ #ይገደላል ???? ተጎጅውስ ማህበረሰቡ አይደለምን??? "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ጭንቅን #ተጋሪወች ፤ #መፍትሄም #አመንጭወች #አዛኞች እና #ተንከባካቢወችን የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያወችን #ማን ይሆን ያላቸው? የህክምና ባለሙያወች አገር አቅኝም ናቸው። የሰው ልጅ አለ በሚባልበት ቦታ ሁሉ በቀን ሃሩር፤ በሌሊት ግርማ ሞገሱን ታግስወ በቅንነት የሚተጉ ሊቀ ትጉኃን። እንደዚህ በየሄዱበት እያገለገሉ ደመ ከልብ ሆነው የሚቀሩ አሳዛኝ ፍጥረቶች ሆኑ። በስንት ድካም፤ በስንት ልፋት የሚገኝ ሙያ እና የጥረት ስኬትም ለባሩድ ጭካኔ ተዳረገ። አገልግሎቱ ቢቋረጥ በዚህ ጭንቅ ጊዜ ምን ትጠቀሙ ይሆን? የቻለ ወደ ተሻለ ቦታ ሄዶ እንዳይታከም ሁሉ ነገር ዝግትግት ብሏል። ማህበረሰቡ ለዓይኖቹ ስለምን ጥበቃ አያደርግም በየተራ????ለምንስ በጋራ አይመክርም??? መፍትሄ ፈልጉ እባካችሁን??? ለሰማቱ ሊቀ ትጉኃን ለመላ ቤተሰቡ ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁኝ። ሥርጉትሻ 2025/11/2025 እግዚአብሄር አምላክ ሁሉ ይቻለዋል እና ሰማያዊ ርትህ ይስጥበት። ውቦቹ ውዶቹ ቤተ ቅንነት እስኪ ደህና አርፍዱ። ቸር ያሰማን። አሜን። /// ከመተማ ኮምኒኬሽን ያገኜሁት ነው። ይህ ግን መፍትሄ አይሆንም። ሌላ ነፍስ አድን የተደራጄ ጥበቃ ለባለሙያወች ሊደረግ ይገባል። መኖር ይፈትናቸዋል። ደግሞ እንዲህ ህይወታቸው ይነጠቃል። " ………በግፍ እና በአሰቃቂ ሁኔታ ሂወቱን ለተነጠቀው ...