ብጹዑ አባታችን በመከራችን ሁሉ ቀድመው የሚገኙ #ሐዋርያችን ናቸው። ማገዶነት ለብጹዕነታቸው ብርቃቸው አይደለም። የኖሩበት ነው።

 

ብጹዑ አባታችን የመከራችን ሁሉ #ሐዋርያችን ናቸው። ማገዶነት ለብጹዕነታቸው ብርቃቸው አይደለም። የኖሩበት ነው።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
በዛ ግራጫማ ህወሃታዊው ዘመን እንኳን ሳይፈሩ፤ ሳያርዱ ከተከፋ ልጆቻቸው ጋር ሆነው #ግማድ የተሸከሙ፤ አንደበተ #ርዕቱ፤ ብቁ እና #ጥንቅቅ ያሉ ስጦታችን ናቸው። እንደምን ያለ #እብድ ዘመን እንደሆነ ትናንት አየሁኝ። በብፁ አባታችን አቡነ አብርኃም ፎቶ ላይ #ኤክስ ምልክት እንደምን ያለ መዳፈር ነው? እንደምንስ ያለ ህግ መተላለፍ ነው? ክርክር አላስፈለገኝም። መራራ ስንብት ነው ከወዳጄ ጋር ያደረኩት። 
 
ከዚህ ቤት፤ ከቤተ - ቅንንነት እንኳንስ #ሐዋርያትን ማንም ሰብዕ፤ እንሰሳ፤ ዕጽዋት ሳይቀር የሚከበርበት ነው። የሰብዕን ፎቶ #መዘቅዘቅ ፈጽሞ #አይፈቀድም። በማንኛውም ሰው ላይ የኤክስ ምልክት ማድረግም የተከለከለ መንገድ ነው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ፤ ሰብለ ሕይወት የማንን ጎፈሬ እማበጥር ይመስላችኋል። ነገረ ትውልድ ትርታዬ ነው። ስለ ትውልዱ ስጽፍ በፆም በጸሎት በመጠሞን ነው። ከልጆች መፃህፍት ቅንጣት ዝበት አታገኙም። ልጆቻችን እኛ ባለፍንበት ትርኪ ምርኪ፤ ግፋፎ ሁነት ማለፍ የለባቸውምና።
 
ስለሆነም ከባህላችን ውጭ የሆኑ ፆታ ነክ ጉዳዮን ተደፍረው ከዚህ ቤት አይለጠፋም። ካገኜሁም አይቀሬው ስንብት ይሆናል። ሌላው ቀርተው በቋንቋችን ውስጥ ያሉ ጸያፍ የሆኑ አገላለፆችን መጠቀም እንኳን አይፈቀድም። አማርኛ ቋንቋ #ዲታ የለማ ቋንቋ ነው። እንደ ጀርመንኛ ቋንቋ። 
 
አንድ ፊደል ብቻውን ከትርጉም አልፎ ዕጣ ነፍሱን #ቅኔን ይቃኛል። ዕርዕስ መሆን ይችላል። #ቃ የሚለው አንድ ፊደል ዘርፈ ብዙ ትርጉም አለው። ለምሳሌ ነው ያነሳሁት። እንትን ከማለት ይልቅ (በፆታቸው የሚተዳደሩ፤ አግብተው የፈቱ፤ ያላገቡ) ወዘተ የሚሉ ቃሎችን መተካት ይቻላል፤ ተፈጥረው ግን ለውስጥነት የማይመቹትን ቃላት እንኳን አቻ ትርጉማቸውን ለመሥራት ችግር የለብንም። 
 
በእያንዳንዱ እርምጃችን ትውልድን #እየናድን ሊሆን አይገባም። በጥንቃቄ፤ በስክነት ልንጓዝ ይገባል። ኢትዮጵያ የምትመዘነው በትውልድ የሥርዓት፤ የሞራል አቅም ነውና። የልጆች ኃላፊነት ከመምህራን ቀጥሎ የእኛም ነው። አክሰሱ ላላቸው ልጆቻችን እራሳችን አርመን መነሳት ውዴታ ሳይሆን ግዴታችንም ነው። አቅም ከሌለን፤ እንደ ሳሙና የሚኩረፈረፍ ስሜት #የሚንጠን ከሆነ ዝም። 
 
ቢያንስ በእጅ በሚገኝ ጉዳይ ስለምን ጥንቃቄ ያንሳል? ከዚህ ቤት ትርፍ ቅጥያ፤ ቅጥልጥል #ዘለፋ፤ ፈጽሞ አይፈቀድም። አማርኛችን #ከሮኬት የበለጠ ሞጋች ቃሎች፤ የግሥ እርባታወች ያሉት፤ የውስጣችን ስሜት ገላጭ #ፍቱን የሆኑ ቃሎችን ለማቅረብ ድህነት ትውር የማይልበት ብቃት ያለው #ሊቅ ቋንቋ ነው። ጠፋ፤ ጎደለ የምንለውን ሁሉ ከህግ ጋር ከሚያያዙት በስተቀር ጠንካራ ቃላትን በመጠቀም ሙግታችን ማስነካት እንችላለን።
 
"#መከበር በከንፈር።" በመደዴ … ለመደዴ የተሰጠን የአባቶቻችን ትውፊት አይደለም። ማክበር፤ መከባበር እኮ #አደራም ነው። ለአደራ በቅተው፤ ለአደራ እንድንበቃ የደከሙ ቀደምት እመው እና አበውን አጥንት አናስቀይም። ከመቃብር አውጥተንም አንቀጥቅጥ።
ብጹዑ አባታችን ሊቀ - ትጉኃን ምስብሃካችን አቡነ አብራኃም ላይ ዘመቻ? ጎንደሮች ባለ ቅኔወች ናቸው እና "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ። ልካችን እንወቅ እላለሁኝ በትሁት መንፈስ። አባታችን ሆይ! የማቱሳላን ዕድሜ ይስጥልኝ። አሜን። ሳይገባን እና ሳንመች ነው እናንተን የመሰለ በሁለመና #ሰፊ የመቻል ጸጋ ያላችሁን አባት የሰጠን። ተመስገን።
 
ትጋት ወዘተ እነኝህን መሰል ብርቱ ቃላት ብጹዑ አባታችነን ይገልፃቸዋል። "አልሰደድም" ነው የሚሉት። ለማገዶነት በየዘመኑ የተዘጋጁ ብርቱ፤ የማይሰበሩ ፈተናን የሚጋፈጡ፤ የማይበገሩ፤ የግንባር ሥጋ፤ ፊት ለፊት የሚገኙ ብቁ እረኛ፤ ሐዋርያ አባት አምላካችን ስለሰጠን አመሰግነዋለሁኝ።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ኑሩልኝ። አሜን።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/11/2025
 
የተሰጠንን ማስተዋል ሥራ ላይ ለማዋል አንለግም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።