ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 19, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እናትዋ ጎንደር | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Offici...

ምስል

በላይ | አሰቻለው ፈጠነ (አርዲ) | አስቻለ አልበም | Belay | Aschalew Fetene (Ardi) | T...

ምስል

በፍቅር የተጎዳው ያፈቀረውን ያጣው አስቹ ክራሩን ይዞ መነነ..በስራው የብዙዎችን ልብ ያሸነፈው የጊዜው ምርጥ አልበ...

ምስል

ትዝታ ዘ ቻግኒ| አሰቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Tizita | Aschalew Fetene (Ardi) | Track 12

ምስል

ካሲናው ጎጃም | አሰቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Kasinawu Gojam | Aschalew Fetene (Ardi) ...

ምስል

አድዋ | አሰቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Adwa| Aschalew Fetene (Ardi) | Track 10

ምስል

አስቻለ | አሰቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschale | Aschalew Fetene (Ardi) | ( Officia...

ምስል

እንገር ወሎ | አሰቻለው ፈጠነ (አርዲ) | አስቻለ አልበም | Enger Wello| Aschalew Fetene (A...

ምስል

#የስሜን ፖለቲካ ጆኖሳይድ ተፈፅሞበታል……… ግን ……… የገባው የለም። ያስተዋለው የለም። አጀንዳው ያደረገው የለም። የእኔ ያለው የለም። የእኛ ያለው የለም። ውስጡ ያደረገው የለም።

ምስል
  #የስሜን ፖለቲካ ጆኖሳይድ ተፈፅሞበታል……… ግን ……… የገባው የለም። ያስተዋለው የለም። አጀንዳው ያደረገው የለም። የእኔ ያለው የለም። የእኛ ያለው የለም። ውስጡ ያደረገው የለም።   …… በተቀነባበረ፣ በተደራጀ፣ በተቀናጀ ሁኔታ የስሜን ኢትዮጵያ ንጥረ ነገር በስውር እዬተነቀለ ነው። በስውር እዬታጨደ ነው ። በኦህዴድ + በግንቦት 7 + በገዳ ምርጫ ቦርድ። የባልደራስ ካቴና፣ የኢዴፓ ስረዛ፣ የኢኃን ስረዛ፣ የአብሮነት ድለዛ አብሮ መታዬት አለበት። ጆኖሳይድ ተፈፅሞባቸዋል። ኦፌኮ አለ፣ የፕሮፌሰር በዬነውም ድርጅት አለ። አንድም የደቡብ ሊሂቅ ፍጅት አልታወጀበትም። ሽፋን ተሰጥቶት በተለያዬ ሹመት ላይ ይገኛል ማህበረ #ደህዴን ። #የራስመርዝ ለራስ ሲሰራ። ህወሃት እራሱ የተፈጠረው እራሱን ለማጥፋት ነበር። እራሱን ለማጥፋት መርዝ አረገዘ። መርዝ ወለደ። መርዝ አሳደገ። መርዝ አስጎለመሰ። መርዝ እራሱ ፀንሶ፣ መርዝ አርግዞ፣ መርዝ ወልዶ፣ መርዝ አጎልምሶ ለልዕልና ያበቃው የክት ልጁ ምድማዱን አጥፍቶ አከሰለው። አበነንው የገዳው የሉባ ማህበር #ኦህዴድወኦነግ ። የሚገርመው የገዳው የሉባ ማህበር ኦህዴድም እንደ ፈጣሪው ፀረ ስሜን፣ ፀረ ተዋህዶ፣ ፀረ አማራ ውርሱን በእጥፍ ድርብ አጠናክሮ ሲቀጥል ፈጣሪው ትህነግም ስሜነኛ ስለነበር እስኪበቃው አድቅቆ ቅርስ አልቦሽ ፈጭቶ ትቢያ አድርጎታል። እሱ በእሱ ማግዶ ስሜንን የዶግ አመድ አድርጓታል። አንድም የአማራ ተቋም፣ አንድም የተጋሩ ተቋም ከእንቅልፋ አልነቃም። ለሽሽሽሽሽሽ። #¡¿ መልካም የዕንቅልፍ ጊዜ ¡¿ አብን እና ብአዴን የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትህነግ ነበረች ሦስት ዓመት ሙሉ። ትህነግ በበኩሏ ደግሞ አብን እና ብአዴን የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ ነበሩ። እነሱን እያከሳከሰ የገዳ ወረራ፣ የገዳ መስፋፋት፣ የገዳ አስምሌሽ

18.01.2020 ኢትዮጵያዊነትን አማራነት ያነበዋል፣ ይተረጉመዋል፣ ያመሳጥረዋል። ውስጥህን ስትፈትሸው እሚነግርህ ሚስጢር አለ። ሚስጢረኛ ብታደርገው አማራነት ጥበብ ነው። ሁንበት! ኑርበት! ታተርፋለህ ልቅና።

ምስል
 አማራነት የማይሸነፍ ማንነት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie      ተፈሪነታችን ልቅና በልዕልና ነው። ስለሆነም ተፈሪነታችን ንጥረ ነገራችን ስለመሆኑ አሳምረን እናውቀዋለን። አማራነት ይለምልም! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራ በመሆኔ ሐሤት አደርጋለሁ። አማራነት ይስፋ አማራነት ይንሠራፋ! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  በአማራነቴ በውስጤ ያለውን ጥልቅ መንፈሳዊ ኃብት እማውቀው እኔ ብቻ ነኝ። ስለዚህም አማራነቴን አመሰግነዋለሁ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራነት የህሊና መክሊት ነው። ስለዚህም አቅመ ቢስ ጊዜ ሰጥ መሪዎች አጥብቀው ይፈሩታል። አይፈረድባቸውም። አማራነት ሱቅ ተሂዶ የሚገዛ አይደለም እና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  የአማራነትን የጥሞና ልክ ገላጩ፣ ሚስጢረኛው፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው አረንጓዴ ቢጫ ቀዪ ብቻ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  ኢትዮጵያዊነትን አማራነት ያነበዋል፣ ይተረጉመዋል፣ ያመሳጥረዋል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራነት ያብባል ገና! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አማራ ስትሆን ድምቅ ስትል ሁለመናው ያምርብኃል። እና ማህበረ ፀረ አማራ የፈጣሪን ፀጋ ለማምከን ይተጋል። ግን አይሳካለትም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie    ዝም ብለህ እሰበው አማራነትህን። በሰብአዊነት፣ በተፈጥሯዊነት ውስጥ ስለመስከንህ ያጫውትኃል። መሆኑን አንተው አሳምረው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie    ውስጥህን ስትፈትሸው እሚነግርህ ሚስጢር አለ። ሚስጢረኛ ብታደርገው አማራነት ጥበብ ነው። ሁንበት! ኑርበት! ታተርፋለህ ልቅና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  አስተውለው። ጥሙና አጉርሰው። አገር ማበጀት

አገር ጠልቶ አገር መምራት አለ ወይ???

 አገር ጠልቶ አገር መምራት አለ ወይ??? ሥርጉትሻ 18.01.2024

#ችኮላ #አይገጠግጠኝም።

ምስል
  #ችኮላ #አይገጠግጠኝም ።   በጓዳ እዬመጣችሁ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን የሞተ ዘመድ የለሽም ወይ? እንደ ሌለ ቁጠሪው የምትሉኝ ቅኖች ችኮላ አያስፈልግም። ይህንን ጭብጥ በተለያዬ ጊዜ ፅፌዋለሁኝ። ወቀሳ፣ ነቀሳ፣ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ማስወገድ ከተፈለገ ፊት ለፊት ብዙ ቀኖች አሉ። ይደረስበታል። ወት ብርቱካን ሚዲቅስ ስንት ግብር የከፈልኩላት እኮ ይኽው በራሷ ጊዜ ከስንት ዓመት በኋላ በእሷ ምክንያት በሉላዊ ሁኔታ ባን ካሰደረጉኝ ጋር መከተሟ ሳይሆን ድርጊቷ ቋሰኛ መሆኑ ከውስጤ ወጣች። በቃ። ይደረስበታል። እኔ የተስፋ አቀንቃኝ ነኝ። የመጀመሪያው የአዋቂዎች የግጥም መድብል መፀሐፌ "ተስፋ" ነው። በ2008 በተመሠረተው የፀጋዬ ድህረ ገፅ ላይ #ተስፋ የሚል አንድ መምሪያ ነበረኝ፣ #የሎሬት ተስፋ የሚል የልጆች ዝግጅት በድምፅም በፁሁፍም ነበረኝ። ለ13 ዓመት የዘለቀው የፀጋዬ ድምፅ ራዲዮ በወር ሁለት ጊዜ በሚቀርበው መሰናዶ መግቢያው #በተስፋ #ተስፋ የተቀመረ ነው። ከፊደል "ተ"ን ከሥም "ተስፋን" እወዳለሁኝ። ስለዚህ ተስፋ ባለበት ቦታ ተስፋዬን አድርቄ አልማስንም። እስከ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽንም፣ ኮሚሽነሩንም ዶር ዳንኤል በቀለን ተስፋዬ አድርጌ አያቸዋለሁኝ። ክፍት ሲለኝም ለእሳቸው በግል እፅፋለሁ፣ አቤት እላለሁ። ይህን ፈጣሪ ያስቀጥልልኝ ዘንድ እማፀናለሁኝ። ኮሚሽኑ የሚወስናቸው፣ ዳታ የሚያበዛባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ ደግሞ በአክብሮት ወቀሳዬን አቀርባለሁኝ። … እንጂ መብራቱን ድርግምግም አድርጌ በጨለማ አልደናበርም። ብርኃን አለ፣ በዛ ተጉዤ ተጨማሪ ሙሉ ይሆን ዘንድ ሃሳቤን አጋራለሁኝ። አንድ እሱ ብቻ ተቋም መጠለያ የተስፋ ጥግ ኑሮ እሱንም ለመንቀል አዕምሮ ውስጥ መ

#ኃራም የስሜን ፖለቲካ ፕሮጀክት ተሳካለት።

ምስል
  #ኃራም የስሜን ፖለቲካ ፕሮጀክት ተሳካለት።     ስሜን ፖለቲካ ኢትዮጵያን የፀነሳት፣ ያረገዛት፣ የወለዳት፣ ያሳደጋት፣ ያጎለመሳት፣ ያደረጃት የሚስጢር ባለሟል፣ የዕደምታ እጬጌ፣ የተደሞ ንጥረ ነገር ነው። ህወሃትን ጨምሮ የፈለፈላቸው የመንፈስ ዲቃላዎቹ፣ የጡት ልጆቹ ሁሉ ደግሞ ሲነሱ ሲወድቁ ኖረው አሁን ተሳካላቸው። በመሪያቸው በሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ እና በተደማሪ ሚዚዎች አማካኝነት ከሰኔ 15/2011 ጀምሮ ከዛም ቀደም ብሎ ዋዜማው በማዕከላዊ ጎንደር በሺህ ዘመናት የመፈናቀል ታሪክ ከ80 ሺህ ህዝብ፣ ከስሜን ፓርክ ቃጠሎ ጋር ዛሬ እስካለንበት ጥር ጣና ዘገሊላ ሰሞናት ድረስ በግፍ፣ በበቀል ታረሰ። ለእኔ የሥነ ልቦና ጦርነትም ነው ብዬ አስባለሁኝ። አሁን ራህቡም፣ ጥማቱም፣ መፈናቀሉም፣ መታረዱም፣ ግፍ መቀበሉም አገራዊ ሠራዊት አልበቃ ብሎ የሱማሌ፣ የኤርትራ፣ የሱዳን ጦር በህብረት ኢትዮጵያ የተሠራችበትን የወርቅ ማህለቅ ሚስጢር ጥሶ ገብቶ አደቀቀው፣ አመሸከው፣ ተቀበለው። መቃዲሾ ካራማራ ላይ ያጣችውን ድል፣ ኤርትራ ባድመ ላይ ያላገኜችውን ድል፣ ሱዳን መተማ ላይ ያልተሳካላት ህልም በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ የሞጋሳ ብልፅግና አመራር ተሳካለትን። ተዋረድን። ተሸማቀቀቅን። ሁሉም የችግር አይነት ስሜን ላይ ተፈቀደለት። ጦርነቱን በጥሞና ማዬት ይገባል ብለን የሞገትን ርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ፀጋዬ፣ ጋዜጠኛ ኃብታሙ አያሌው፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት ማዕዛ ማህመድ እና እኔ እራሴ ሥርጉተ ሥላሴ ብቻ ነበርን። የዓለም ተራዕዶ ድርጅቶች ሳይቀሩ እኛ በሞገትንበት ጊዜ አልነበሩም። አሁንም ቢሆን ተባደግ ነው ዕይታቸው። ፍሬ ነገሩን አላገኙትም። ስለተጋሩ ቢጮሁም ስለ አማራ ግን አይጮሁም። ይህን የሚያስደርጉት ደግሞ አቅም

#ትቢያነት አስተሳሰባዊ እርከኑ።

ምስል
  #ትቢያነት አስተሳሰባዊ እርከኑ።   ለዚህ መኖር የሴራ ስልጠና፣ ለዚህ መኖር የቁማር ተቋም፣ ለዚህ መኖር የኢንትሪንግ ብልፅግና፣ ለዚህ መኖር የቂም ድሪቶ፣ ለዚህ መኖር የበቀል እንድርቺ እንድርቺ፣ ለዚህ መኖር የግለኝነት ቅልሞሽ፣ ለዚህ መኖር የበቀል ሥልጣኔ። ትቢያነት አስተሳሰብ። #ህዝባችን ይሄን ይመስላል። ለዕለት ጉርስ ያልበቃ። በማረፊያው ጊዜ ማስኖ ለመኖር ያልተፈቀደለት። የደላው ደግሞ እስረኛን ለመጠዬቅ የክት እና የዘወትር ይበጅለት፣ እኛ ዜግነቱን የሰረዝነው አሳርኛ ለምን ከወገኖቹ ጋር ገጥ ለገጥ ተገናኜ ብሎ ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ኩፍትርትር ይላል። እርግማን። አብሮነት ጠላቱ #የገዳኦዳ #ምርጫ #ቦርድ ፣ #የህወኃት ማንፌስቶ ተህገ-መንግሥት ብቻ ሳይሆን ነፃነት የናፈቀውም ሆኖ ስታዩት የውስጥ አቅሉ፣ የአስተሳሰብ ዲካው #ጎግማ ፣ #ቆባ ፣ #እጭ ላይ እዬዳከረ እንደሆን ታያላችሁ። መሥራት አለብን። ውስጣችን ወና ነውና። አልበቀለበትም ልቅና። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። 19/01/2021 ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

#ፈተናውን የተቋቋመው እኛን የበለጠ ታማኝ ውሻ።

ምስል
  #ፈተናውን የተቋቋመው እኛን የበለጠ ታማኝ ውሻ።     ኢትዮጵያዊው ሰው እኔን ጨምሮ በዚህ ልክ ስለመሆኑ ይፈትሽው። ኢትዮጵያዊው ውሻ ያለው የፅናት አቅም፣ የመታመን ልቅና የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት እስተካቢኔው፣ እስተሚያላግጥበት #የሞጋሳ #ብልጥግና ፣ የገዳ ምርጫ ቦርድስ ይኖረው ይሆን? እኛ ስልጣኑም አቅሙም ተደማጭነቱም የለንም እና። የቤተ - መንግሥቱ ሽማምንት፣ #የኦዳወገዳ ቤተ - መንግሥት ቅልጥመኛ፣ #ፍሪንበኛ ፣ አንጣፊ፣ ዕልፍኝ አስከልካይ ሊጋባ ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት ዝልቅ ሚስጢር ዬመታመኑ ልኩ፣ ወቄቱ ከዚህ ቅዱስ ታማኝነት ጋር እቆማለሁ፣ እወዳደር ይለን ይሆን? #ዬልግጫ #ልጣጭ ። ሁላችንስ ከዚህ ቀደም ስለ ዓድዋ የዘመርነው፣ የተቃኜነው፣ ፅላታችን ያደረግነው፣ ስለፋሲል፣ ስለ ቴዲ፣ ስለ በላይ፣ ስለ አብርኃም፣ ስለ ካራማራ፣ ስለባድመ፣ ስለ መቅደላ፣ ስለ አሉላ፣ ስለ ዮሖንስ፣ ስለ ዘርዓይ፣ ስለ አብዲሳ፣ ስለ ኃይለማርያም ማሞ የውስጥ ውህድነት በምስክርነት ዛሬ አለን? #ውሸት ማን ነው? #ዕብለትስ የማን ነው? #ሃቅስ ተዬት ነው? #ክህደትስ ከወዴት ነው? እጬጌው ዘመን ዝክንትሉን አውጥቶታል፣ ሸግሽጎታል፣ ሸክሽኮታል፣ ፈትጎታል። ተመስገን። #አኔዊነት ፣ #አገራዊነት ፣ #ብሄራዊነት ፣ ፓናዊነት ግን የት ናቸው? ፈተና አላፊና ወዳቂ፣ መቀነስ እና መታከል፣ መጠቅለልና መወረር እንደምን እና እንደምን #በገዳኦዳ ? ከዚህ ሁሉ ኳኳቴ፣ ከዚህ ሁሉ ትርምስ የፀዳ፣ የነጣ፣ የበቃ ታማኝነት በዚህ እንሰሳ ውስጥ ፈልቆ ተገኜ። መማር ከተቻለ የሐዋርያነት ኩነት ተፈፀመ። ተመስገን። #ውስጥ እስቲ ይመርመር? #አነስን ወይንስ እኩያ ሆን? #የት ላይ ይሆኑ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ከእነ ካቢኔዎት? ይመዝኑት መዝኑት። ይ- መ - ዘ - ኑ

መትላት በክፋ ዕሳቤም - ድርጊትም - ትብብርም።

ምስል
  #መትላት በክፋ ዕሳቤም - ድርጊትም - ትብብርም።   ለዚህ ኑሮ የሴራ ፖለቲካ፣ የሸፍጥ ፖለቲካ፣ የደባ ፖለቲካ፣ የአድመኝነት ፖለቲካ ፋፍሪካ ተከፍቶለታል። እኔን የምትከተሉ ውዶቼ ዛሬ እራስን መርምሮ እራስን ከአድማ - ከሴራ - ከበቀል - ከምቀኝነት ፖለቲካ ጋር እንፋታ ዘንድ እለምናችሁ አለሁኝ። #አንዱን ሰው ወደህ ሌላውን ጠልተህ፣ #አንዱን ሞት አዝነህለት ሌላውን ደልቀህበት፣ #አንዱን ራህብ የእኔ ብለህ ሌላውን እልልታ ልከህበት፣ #አንዱን መፈናቀል ውስጥህ አድርገህ ሌላውን ፊት ነስተህ አለሁ አትበል የለህም። #እነግርኃለሁ የለህም። በሆነው ነገር፣ በሚሆነው ከንቱ ነገር ሁሉ አብረን እንፈር። ውርዴቱ የጋራ ዝቅጠቱም የወል ነው። ከፈፃሚዎቹ የተሻለ ለመሆን ከራስ ይጀመር። #በኃጢያት ተልተናል። ሰው ሞተ፣ ቤተ መቅደስ ተደፈረ፣ መስኪድ ተቃለለ፣ ቅርስ ወደመ፣ ታሪክ ጠለሼ፣ ሰውነት ተሰደደ፣ መኖር ተዘረፈ ሁሉም ከጎጆ ካልገባ ፋሲካ ነው። ዋዮ! #ወዮልን ! እንደ ኩርድሾቹ ስንሆን ስንቀረቀር ይገባናል። አፈር አልባ መሆን፣ አገር የለኝም ማለት፣ መለያ የለኝም ማለት ቀና ማለት ሳይሆን #አፍ ባለው መቃብር መከዘን ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። 19/01/2022 ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ፀሎት የፅናት ወተት ነው።

ምስል
 ፀሎት የፅናት ወተት ነው።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/01/2021

በ2019 ነው እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የደወል ንቅናቄ እንድትጀምር በትህትና ያሳሰብኩት። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም። " ቢሰሙን ይበጅ ነበር።

ምስል
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን። ይድረስ ለብፁዐን ቅዱሳን አባቶቼ። ባሉበት።   በአለፈው ሳምንት አንድ ቁልፍ ነገር አንስቼ ነበር። የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ አላወቀችውም እንጂ የቁም እስረኛ ናት። በጠቅላላ እንቅስቃሴዋ ሁሉ በኦሮሙማ የደህንነት ተቋማት ሥር ነው። ይህንን አውቃ ቤተክርስትያናችን ቀለል ያሉ ሰላማዊ ዬትግል መስመሮችን ደፍራ መጀመር ይኖርባታል። በተለይ በአዲስ አበባ። " ተማህፅኖ " የተባለው ቀልድ ነው። በዚህ ውስጥ ያለው ዕውነት የመንፈስ የሥነ ልቦና ካቴና ነው። ስለሆነም ቀደም ባሉ ቀናት እንደፃፍኩት የደወል አቤቱታን ለእዮር የምታቀርብበት ንድፍ ሊኖራት ይገባል። አሁን ሦስት ቀን ምህላ አውጃለች። ከምህላው ፍፃሜ በኋላ በሁሉም አብያተ ቤተክርስቲያናት የአንድ ሰዓት የደወል ፕሮግራም ሊኖራት ይገባል። ይህን ሳያቋርጡ በተለይ አዲስ አበባ በሁሉም አድባራት በዬሳምንቱ ለምሳሌ ከጥዋቱ ፬ ሰዓት እስከ ፭ ሰዓት በደወል ፈጣሪያውን መጠዬቅ። ይህ አንድ ሰው ብቻ የሚፈፅመው ቀላል፣ ሥልጡን፣ ብዙ ሚስጢራትን የያዘ ተጋድሎ መስክ ነው። የኔታዋ የኦሮሙማ ፖለቲካ መተንፈሻዋን ሙሉ ለሙሉ ከመከርቸሙ በፊት፣ መንበረ ፓትርያርኩ ከመደፈሩ በፊት፣ ብፁዐን ወቅዱሳን አባቶቻችን ከማጣታችን በፊት ቢያንስ የደወል አቤቱታ ፕሮግራሙን ደፍራ ትጀምረው። ወስብሃት ለእግዚአብሄር።