በ2019 ነው እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የደወል ንቅናቄ እንድትጀምር በትህትና ያሳሰብኩት። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም። " ቢሰሙን ይበጅ ነበር።

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን። ይድረስ ለብፁዐን ቅዱሳን አባቶቼ።
ባሉበት።
 No photo description available.
በአለፈው ሳምንት አንድ ቁልፍ ነገር አንስቼ ነበር። የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ አላወቀችውም እንጂ የቁም እስረኛ ናት። በጠቅላላ እንቅስቃሴዋ ሁሉ በኦሮሙማ የደህንነት ተቋማት ሥር ነው።
ይህንን አውቃ ቤተክርስትያናችን ቀለል ያሉ ሰላማዊ ዬትግል መስመሮችን ደፍራ መጀመር ይኖርባታል። በተለይ በአዲስ አበባ። " ተማህፅኖ " የተባለው ቀልድ ነው። በዚህ ውስጥ ያለው ዕውነት የመንፈስ የሥነ ልቦና ካቴና ነው።
ስለሆነም ቀደም ባሉ ቀናት እንደፃፍኩት የደወል አቤቱታን ለእዮር የምታቀርብበት ንድፍ ሊኖራት ይገባል። አሁን ሦስት ቀን ምህላ አውጃለች። ከምህላው ፍፃሜ በኋላ በሁሉም አብያተ ቤተክርስቲያናት የአንድ ሰዓት የደወል ፕሮግራም ሊኖራት ይገባል።
ይህን ሳያቋርጡ በተለይ አዲስ አበባ በሁሉም አድባራት በዬሳምንቱ ለምሳሌ ከጥዋቱ ፬ ሰዓት እስከ ፭ ሰዓት በደወል ፈጣሪያውን መጠዬቅ። ይህ አንድ ሰው ብቻ የሚፈፅመው ቀላል፣ ሥልጡን፣ ብዙ ሚስጢራትን የያዘ ተጋድሎ መስክ ነው።
የኔታዋ የኦሮሙማ ፖለቲካ መተንፈሻዋን ሙሉ ለሙሉ ከመከርቸሙ በፊት፣ መንበረ ፓትርያርኩ ከመደፈሩ በፊት፣ ብፁዐን ወቅዱሳን አባቶቻችን ከማጣታችን በፊት ቢያንስ የደወል አቤቱታ ፕሮግራሙን ደፍራ ትጀምረው።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።