#የስሜን ፖለቲካ ጆኖሳይድ ተፈፅሞበታል……… ግን ……… የገባው የለም። ያስተዋለው የለም። አጀንዳው ያደረገው የለም። የእኔ ያለው የለም። የእኛ ያለው የለም። ውስጡ ያደረገው የለም።

 

#የስሜን ፖለቲካ ጆኖሳይድ ተፈፅሞበታል………
ግን ………
የገባው የለም።
ያስተዋለው የለም።
አጀንዳው ያደረገው የለም።
የእኔ ያለው የለም።
የእኛ ያለው የለም።
ውስጡ ያደረገው የለም።
 No photo description available.
…… በተቀነባበረ፣ በተደራጀ፣ በተቀናጀ ሁኔታ የስሜን ኢትዮጵያ ንጥረ ነገር በስውር እዬተነቀለ ነው። በስውር እዬታጨደ ነውNo photo description available.
በኦህዴድ + በግንቦት 7 + በገዳ ምርጫ ቦርድ። የባልደራስ ካቴና፣ የኢዴፓ ስረዛ፣ የኢኃን ስረዛ፣ የአብሮነት ድለዛ አብሮ መታዬት No photo description available.አለበት። ጆኖሳይድ ተፈፅሞባቸዋል።No photo description available.
ኦፌኮ አለ፣ የፕሮፌሰር በዬነውም ድርጅት አለ። አንድም የደቡብ ሊሂቅ ፍጅት አልታወጀበትም። ሽፋን ተሰጥቶት በተለያዬ ሹመት ላይ ይገኛል ማህበረ #ደህዴን
#የራስመርዝ ለራስ ሲሰራ።
ህወሃት እራሱ የተፈጠረው እራሱን ለማጥፋት ነበር። እራሱን ለማጥፋት መርዝ አረገዘ። መርዝ ወለደ። መርዝ አሳደገ። መርዝ አስጎለመሰ።
መርዝ እራሱ ፀንሶ፣ መርዝ አርግዞ፣ መርዝ ወልዶ፣ መርዝ አጎልምሶ ለልዕልና ያበቃው የክት ልጁ ምድማዱን አጥፍቶ አከሰለው። አበነንው የገዳው የሉባ ማህበር #ኦህዴድወኦነግ
የሚገርመው የገዳው የሉባ ማህበር ኦህዴድም እንደ ፈጣሪው ፀረ ስሜን፣ ፀረ ተዋህዶ፣ ፀረ አማራ ውርሱን በእጥፍ ድርብ አጠናክሮ ሲቀጥል ፈጣሪው ትህነግም ስሜነኛ ስለነበር እስኪበቃው አድቅቆ ቅርስ አልቦሽ ፈጭቶ ትቢያ አድርጎታል። እሱ በእሱ ማግዶ ስሜንን የዶግ አመድ አድርጓታል።
አንድም የአማራ ተቋም፣ አንድም የተጋሩ ተቋም ከእንቅልፋ አልነቃም። ለሽሽሽሽሽሽ። #¡¿ መልካም የዕንቅልፍ ጊዜ ¡¿
አብን እና ብአዴን የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትህነግ ነበረች ሦስት ዓመት ሙሉ። ትህነግ በበኩሏ ደግሞ አብን እና ብአዴን የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ ነበሩ። እነሱን እያከሳከሰ የገዳ ወረራ፣ የገዳ መስፋፋት፣ የገዳ አስምሌሽን አዲስን፣ ደቡብን እስኪበቃው አዳረሰው።
ጉድ ……
አብን እና ግርባው ብአዴን #ዘረ ኦሮሙማን፣ #ማህበረ ኦነግን #በቶልራንስ ሳይንስ ሲያንፈራስሱ ለትህነግ ቅንጣቢ ፍርፋሪ አያቀምሷትም።
ትህነግ በበኩሏ ማህበረ ኦነግን፣ ኦሮሙማን፣ #በቶልራንስ ስታንቆጠቁጥ አብን እና ብአዴን ደግሞ ይሙት በቃ የተፈረደባቸው ነበሩ።
ሌላው ቀርቶ ትህነግ አልተሳካላትም እንጂ የኤርትራን መንግሥት ትግራይ ትግርኝን ጣዕም ለተኃድሶ #ናለት የምትለውን ሁሉ ላድርግ ብላ ስትማጠን ለራሷ አካል ለአገልጋዮዋ ለግርባው ብአዴን ግን ፊት ሰጥታ አታውቅም ነበር። ቦንብ እና ፈንጅ አከታትላ ትልክ ነበር። ቅማንትዬንም አሰልፋ ትሰጠስጠው ነበር፣ ቬኒ ላይም ትኮረኩመው ነበር።
የአማራ ሊቃናት በመደዳ ሲጨፈጨፋ ፈንድሻ ምርት ላይ ነበረች ትህነግ። በመላ ኢትዮጵያ ቅድስት ተዋህዶ፣ አማራ በገፍ ሲጨፈጨፍ ከበሮ ምርት ላይ ነበረች ትህነግሻ። ቅጭጭ አይላትም ነበር። ሌላው ቀርቶ የጄኒራል ሳህረ መኮነነ ህልፈት ስለምን ብላ አጀንዳ አላደረገችውም ነበር።
ትህነግ ጦርነቱን አህዱ ስትል ሲጠብቋት የነበሩ የአማራ የሠራዊት አካሎቿን ጨፍጭፋ፣ ነዋሪ የአማራ ልጆችን ረሽና ነው። ሌላው መከፋት ስሌለበት ለኦነጉ ሉባ ተጨማሪ ፋሲካ የደገሰችው በማይካድራ ጭፍጨፋ ማህበረ ኦነግ አፍነክንካ ነበር። ለስሜን ሁለመና ሞት ድውለት አማራ እንዲሆን ሽንፈቷን ለራሷ ፈፅማ ነበር።
በዚህ ሁሉ ድቀት፣ በዚህ ሁሉ ውድቀት የኢትዮጵያ ሚስጢር መቦደስ ከቁብ አይቆጠርም ለስሜን ፖለቲከኞች ለአማራም ሆነ ለተጋሩም ሊቃናት ሊሂቃንም። አሁንም የሱዳን ወረራ ለማህበረ ህወሃት የምሥራች ዜና ነው።
የኤርትራውን የእቴጌ ትግራይ በቂም ስትደቅ የትኛው የአማራ ሊቅ፣ ተቋም አወገዘ? ተፈታተሹ እስኪ? አብረን እንፈር። በኳራንቲ ነው ሁለመናው ተከርችሞ በበቀል ውድም ያለው፣ ኦ! 20 አንቡላንስም ወደ ሰማይ አርጓል አሉ¡ ሁሉም ይቅር ሴት እህቶቻችን በጠላት ጦር ሲደፋሩ እንደምን መሽቶ ይነጋል?
ለተጋሩም ሊቃናት ሊሂቃንም ፅንስ ወጥቶ ሲታረድ እንደምን እህል ከጉሮሮ ይወርዳል። የቅድመ አያቶቻችን ጥበብ፣ ሚስጢር የጠቀጠቅን ሩጉሞች። አብረን እንፈር።
በአማራ በኩልም ህወኃት ትውደቅ እንጂ እዳው ገብስ ነው ሞቶ ነበር። ጭካኔው፣ ውድመቱ፣ ፍርሰቱ፣ በግራቀኝ የውጭ አገር ሠራዊት ስሜን መድቀቁ ለሁለቱም ማህበረሰቦች አንቂ ሊቃናት፣ ተቋማት አጀንዳ አይደለም።
ሌላው ቀርቶ ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በሁለቱ ህዝቦች ማህል ቋሚ ቁርሾ መትከላቸው አዲሱ ሹም ዶር ሙሉ ነጋ በማስተዋል ሊመረምሩት አልፈቀዱም።
አንድ አሲንባ የሚባል ድርጅት ከአብንም፣ ከግርባው ብአዴንም ተሽሎ የስሜን ፖለቲካ ድቀት ውስጡ አድርጎ ተመልክቻለሁ። ይህ ብልህነት ነው። ኢትዮጵያንም ይታደጋታል። ኢትዮጵያ አንድ ናት።
ኦነጋውያኑ ከህወኃት // ህውኃትውያኑ ከኦነግ ለኢትዮጵያ አይሻሉም ሁሉም ድውይ ናቸው። ህወሃት ሲወድቅ 40 ሺህ ኦሮሞ ከእስር ፈታን አሉን ዶር ለማ መገርሳ። አሁን ደግሞ 10 ሺህ እስረኛ አለ። አባ ገዳዎች ትግራይ ከመሄድ ለእነኝህ ነፍሶች ይድረሱላቸው። በሬውም ይታረድ።
በኦሮሙማ አማፂ ደጋፊ እና ተቃዋሚ የሞተው በግራ ቀኝ ጨካኞች ቤት ይቁጠረው። ኢትዮጵያ ስንል ይህም ውስጥ ሊሆን ይገባል።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ለራስህ ጥፋት፣ ለራስህ ውድመት፣ ለራስህ ማለቅ፣ ለራስህ መነቀል፣ ለራስህ መጥፈት የምትጥር ስሜነኛ ሁሉ ልብ ይስጥህ።
ኢትዮጵያ ነኝ የሚለውም ስሜን ፈርሶ ኢትዮጵያ እንደለለች ይቁጠረው። ኢትዮጵያ የተጠለፈችበት ሚስጢር እዬተበጣጠሰ ነው። ተዋርደናል። አብረን እንፈር።
የገዳ ምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያን እዬተጫወተባት ነው። ሃግ ሊባል ይገባል። የሎቢ ተግባሩም በዕውቅናው ላይ ሊሠራበት ይገባል። #ብላሽ እና ከንቱ መሆኑን ማጋለጥ ይገባል። ነገ ሳይሆን ዛሬ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
በዚህ ማህል ዘመኑን በጥልቀት አይተው "ስሜት" ያሉትን ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ አናባቢ አቶ ልደቱ አያሌውን አመስግኜ ጉዳዬን ልከውን።
ፋሲል፣ ላሊበላ ቀናችሁ መች ይሆን? ተዶልቶባችኋል እና ሱባኤ ግቡ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/01/2021
ጭምት ፖለቲካ፣ ጭምት ፖለቲካም ይናፍቀኛል።
ጥሞና!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።