መትላት በክፋ ዕሳቤም - ድርጊትም - ትብብርም።

 

#መትላት በክፋ ዕሳቤም - ድርጊትም - ትብብርም።
 
No photo description available.No photo description available.
ለዚህ ኑሮ የሴራ ፖለቲካ፣ የሸፍጥ ፖለቲካ፣ የደባ ፖለቲካ፣ የአድመኝነት ፖለቲካ ፋፍሪካ ተከፍቶለታል።
እኔን የምትከተሉ ውዶቼ ዛሬ እራስን መርምሮ እራስን ከአድማ - ከሴራ - ከበቀል - ከምቀኝነት ፖለቲካ ጋር እንፋታ ዘንድ እለምናችሁ አለሁኝ።
#አንዱን ሰው ወደህ ሌላውን ጠልተህ፣
#አንዱን ሞት አዝነህለት ሌላውን ደልቀህበት፣
#አንዱን ራህብ የእኔ ብለህ ሌላውን እልልታ ልከህበት፣ #አንዱን መፈናቀል ውስጥህ አድርገህ ሌላውን ፊት ነስተህ አለሁ አትበል የለህም።
#እነግርኃለሁ የለህም። በሆነው ነገር፣ በሚሆነው ከንቱ ነገር ሁሉ አብረን እንፈር። ውርዴቱ የጋራ ዝቅጠቱም የወል ነው። ከፈፃሚዎቹ የተሻለ ለመሆን ከራስ ይጀመር። #በኃጢያት ተልተናል።
ሰው ሞተ፣ ቤተ መቅደስ ተደፈረ፣ መስኪድ ተቃለለ፣ ቅርስ ወደመ፣ ታሪክ ጠለሼ፣ ሰውነት ተሰደደ፣ መኖር ተዘረፈ ሁሉም ከጎጆ ካልገባ ፋሲካ ነው። ዋዮ!
#ወዮልን! እንደ ኩርድሾቹ ስንሆን ስንቀረቀር ይገባናል። አፈር አልባ መሆን፣ አገር የለኝም ማለት፣ መለያ የለኝም ማለት ቀና ማለት ሳይሆን #አፍ ባለው መቃብር መከዘን ነው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
19/01/2022
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።