#ፈተናውን የተቋቋመው እኛን የበለጠ ታማኝ ውሻ።

 

#ፈተናውን የተቋቋመው እኛን የበለጠ ታማኝ ውሻ።
 
 No photo description available.
ኢትዮጵያዊው ሰው እኔን ጨምሮ በዚህ ልክ ስለመሆኑ ይፈትሽው። ኢትዮጵያዊው ውሻ ያለው የፅናት አቅም፣ የመታመን ልቅና የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት እስተካቢኔው፣ እስተሚያላግጥበት #የሞጋሳ #ብልጥግና፣ የገዳ ምርጫ ቦርድስ ይኖረው ይሆን? እኛ ስልጣኑም አቅሙም ተደማጭነቱም የለንም እና።
የቤተ - መንግሥቱ ሽማምንት፣ #የኦዳወገዳ ቤተ - መንግሥት ቅልጥመኛ፣ #ፍሪንበኛ፣ አንጣፊ፣ ዕልፍኝ አስከልካይ ሊጋባ ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት ዝልቅ ሚስጢር ዬመታመኑ ልኩ፣ ወቄቱ ከዚህ ቅዱስ ታማኝነት ጋር እቆማለሁ፣ እወዳደር ይለን ይሆን? #ዬልግጫ #ልጣጭ
ሁላችንስ ከዚህ ቀደም ስለ ዓድዋ የዘመርነው፣ የተቃኜነው፣ ፅላታችን ያደረግነው፣ ስለፋሲል፣ ስለ ቴዲ፣ ስለ በላይ፣ ስለ አብርኃም፣ ስለ ካራማራ፣ ስለባድመ፣ ስለ መቅደላ፣ ስለ አሉላ፣ ስለ ዮሖንስ፣ ስለ ዘርዓይ፣ ስለ አብዲሳ፣ ስለ ኃይለማርያም ማሞ የውስጥ ውህድነት በምስክርነት ዛሬ አለን?No photo description available.
#ውሸት ማን ነው?
#ዕብለትስ የማን ነው?
#ሃቅስ ተዬት ነው?
#ክህደትስ ከወዴት ነው?
እጬጌው ዘመን ዝክንትሉን አውጥቶታል፣ ሸግሽጎታል፣ ሸክሽኮታል፣ ፈትጎታል። ተመስገን።
ፓናዊነት ግን የት ናቸው?
ፈተና አላፊና ወዳቂ፣ መቀነስ እና መታከል፣ መጠቅለልና መወረር እንደምን እና እንደምን #በገዳኦዳ?
ከዚህ ሁሉ ኳኳቴ፣ ከዚህ ሁሉ ትርምስ የፀዳ፣ የነጣ፣ የበቃ ታማኝነት በዚህ እንሰሳ ውስጥ ፈልቆ ተገኜ። መማር ከተቻለ የሐዋርያነት ኩነት ተፈፀመ። ተመስገን።
#ውስጥ እስቲ ይመርመር?
#አነስን ወይንስ እኩያ ሆን?
#የት ላይ ይሆኑ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ከእነ ካቢኔዎት?
ይመዝኑት መዝኑት። ይ- መ - ዘ - ኑ - ም።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Serggute©Selassie
19/01/2021

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።