#ኃራም የስሜን ፖለቲካ ፕሮጀክት ተሳካለት።

 

#ኃራም የስሜን ፖለቲካ ፕሮጀክት ተሳካለት።
 
 No photo description available.No photo description available.
ስሜን ፖለቲካ ኢትዮጵያን የፀነሳት፣ ያረገዛት፣ የወለዳት፣ ያሳደጋት፣ ያጎለመሳት፣ ያደረጃት የሚስጢር ባለሟል፣ የዕደምታ እጬጌ፣ የተደሞ ንጥረ ነገር ነው። ህወሃትን ጨምሮ የፈለፈላቸው የመንፈስ ዲቃላዎቹ፣ የጡት ልጆቹ ሁሉ ደግሞ ሲነሱ ሲወድቁ ኖረው አሁን ተሳካላቸው።
በመሪያቸው በሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ እና በተደማሪ ሚዚዎች አማካኝነት ከሰኔ 15/2011 ጀምሮ ከዛም ቀደም ብሎ ዋዜማው በማዕከላዊ ጎንደር በሺህ ዘመናት የመፈናቀል ታሪክ ከ80 ሺህ ህዝብ፣ ከስሜን ፓርክ ቃጠሎ ጋር ዛሬ እስካለንበት ጥር ጣና ዘገሊላ ሰሞናት ድረስ በግፍ፣ በበቀል ታረሰ። ለእኔ የሥነ ልቦና ጦርነትም ነው ብዬ አስባለሁኝ።
አሁን ራህቡም፣ ጥማቱም፣ መፈናቀሉም፣ መታረዱም፣ ግፍ መቀበሉም አገራዊ ሠራዊት አልበቃ ብሎ የሱማሌ፣ የኤርትራ፣ የሱዳን ጦር በህብረት ኢትዮጵያ የተሠራችበትን የወርቅ ማህለቅ ሚስጢር ጥሶ ገብቶ አደቀቀው፣ አመሸከው፣ ተቀበለው።
መቃዲሾ ካራማራ ላይ ያጣችውን ድል፣ ኤርትራ ባድመ ላይ ያላገኜችውን ድል፣ ሱዳን መተማ ላይ ያልተሳካላት ህልም በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ የሞጋሳ ብልፅግና አመራር ተሳካለትን። ተዋረድን። ተሸማቀቀቅን።
ሁሉም የችግር አይነት ስሜን ላይ ተፈቀደለት። ጦርነቱን በጥሞና ማዬት ይገባል ብለን የሞገትን ርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ፀጋዬ፣ ጋዜጠኛ ኃብታሙ አያሌው፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት ማዕዛ ማህመድ እና እኔ እራሴ ሥርጉተ ሥላሴ ብቻ ነበርን።
የዓለም ተራዕዶ ድርጅቶች ሳይቀሩ እኛ በሞገትንበት ጊዜ አልነበሩም። አሁንም ቢሆን ተባደግ ነው ዕይታቸው። ፍሬ ነገሩን አላገኙትም።
ስለተጋሩ ቢጮሁም ስለ አማራ ግን አይጮሁም። ይህን የሚያስደርጉት ደግሞ አቅም ያላቸው የተጋሩ ሰዎች ናቸው። ከሚስጢራዊ አካልተአምሳልነታቸው የተነጠሉ። ሊቃናት ማለት አልችልም። ሊቅነት አፍሶ መልቀም አይደለምና።
ወሳኙ ነጥብ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የኢትዮጵያዊነት ሥረ መሠረት የስሜን ፖለቲካ በግርዶሽ ፖለቲካ ተጠልሎ መክሰል አለበት የሚለው በረጅም ጊዜ ተመክሮበት ግን ያልተሳካ ፕሮጀክት እንሆ ፍፃሜ አገኜ።
ቱርኮች፣ ፖርቹጊዞች፣ እንግሊዞች፣ ጣሊያኖች፣ አረቦች ሞክረው ያልተሳካላቸው እንሆ አሁን ህልማቸው ድል ኮረቻ ላይ ይገኛል። ለዚህ ድር እና ማግ፣ ጥሬ ዕቃ አቅራቢው ደግሞ የሞጋሳ "ብልፅግና" ነው።
ኦርቶዶክስም አብራ ትደቃለች፣ ሱዳን ስደት ላይ፣ መተከል ሞት ላይ፣ መቀሌ እርኃብ ላይ ዛሬ ጥምቀተ ክርስቶስ በግራጫማ ሲቃ ይከበራል። ይህ ሽንፈት ነው። ሽንፈቱ የፖለቲካው አስኳላዊ ፍሬ ነገር አለመታወቁ ነው።
#ብራቦ አሲንባ ፓርቲ!
19/01/2021
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።