#ችኮላ #አይገጠግጠኝም።

 

በጓዳ እዬመጣችሁ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን የሞተ ዘመድ የለሽም ወይ? እንደ ሌለ ቁጠሪው የምትሉኝ ቅኖች ችኮላ አያስፈልግም።
ይህንን ጭብጥ በተለያዬ ጊዜ ፅፌዋለሁኝ። ወቀሳ፣ ነቀሳ፣ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ማስወገድ ከተፈለገ ፊት ለፊት ብዙ ቀኖች አሉ። ይደረስበታል።
ወት ብርቱካን ሚዲቅስ ስንት ግብር የከፈልኩላት እኮ ይኽው በራሷ ጊዜ ከስንት ዓመት በኋላ በእሷ ምክንያት በሉላዊ ሁኔታ ባን ካሰደረጉኝ ጋር መከተሟ ሳይሆን ድርጊቷ ቋሰኛ መሆኑ ከውስጤ ወጣች። በቃ። ይደረስበታል።
እኔ የተስፋ አቀንቃኝ ነኝ። የመጀመሪያው የአዋቂዎች የግጥም መድብል መፀሐፌ "ተስፋ" ነው። በ2008 በተመሠረተው የፀጋዬ ድህረ ገፅ ላይ #ተስፋ የሚል አንድ መምሪያ ነበረኝ፣ #የሎሬት ተስፋ የሚል የልጆች ዝግጅት በድምፅም በፁሁፍም ነበረኝ።
ለ13 ዓመት የዘለቀው የፀጋዬ ድምፅ ራዲዮ በወር ሁለት ጊዜ በሚቀርበው መሰናዶ መግቢያው #በተስፋ #ተስፋ የተቀመረ ነው። ከፊደል "ተ"ን ከሥም "ተስፋን" እወዳለሁኝ።
ስለዚህ ተስፋ ባለበት ቦታ ተስፋዬን አድርቄ አልማስንም። እስከ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽንም፣ ኮሚሽነሩንም ዶር ዳንኤል በቀለን ተስፋዬ አድርጌ አያቸዋለሁኝ።
ክፍት ሲለኝም ለእሳቸው በግል እፅፋለሁ፣ አቤት እላለሁ። ይህን ፈጣሪ ያስቀጥልልኝ ዘንድ እማፀናለሁኝ። ኮሚሽኑ የሚወስናቸው፣ ዳታ የሚያበዛባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ ደግሞ በአክብሮት ወቀሳዬን አቀርባለሁኝ።
… እንጂ መብራቱን ድርግምግም አድርጌ በጨለማ አልደናበርም። ብርኃን አለ፣ በዛ ተጉዤ ተጨማሪ ሙሉ ይሆን ዘንድ ሃሳቤን አጋራለሁኝ።
አንድ እሱ ብቻ ተቋም መጠለያ የተስፋ ጥግ ኑሮ እሱንም ለመንቀል አዕምሮ ውስጥ መጣደፍ አይገባም ባይ ነኝ። ሰው አለ ብሎ ማሰብ እራሱ ጤና ነው።
ዕውነት ብነግራችሁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምክንያት #አንጀቴ ህመምተኛ ነው። አንዳንድ ቀን ጥፍት እምለው በሃኪሞቼ ምክር ነው። አልችልም።
እና ለህመሜ ፈውሴ እንዲህ ተስፋ የማደርግባቸው ተቋማት ናቸው። አሁን ስለመተከል ጋዜጠኛ ተስፋ ወልደሥላሴ፣ ስለታገቱት ልጆቻችን ማዕዚ፣ እና አቶ ሰለሞን ኃይሌ፣ ስለአዲስ አበባ አቶ አዱገነት ለእኔ ፈውሴ ናቸው።
ውስጤ ሩህሩህ ነው። በአገሬ ሃዘን ተጎድቷል። ስለዚህም ለውስጤ መዳህኒት እንደ ዶር ዳንኤል በቀለ ዓይነት ጭምት ዬሰባዕዊነት መሪ ይሻል።
ተቋሙ በሰው ኃይል ብቃት እጥረት፣ ኢትዮጵያን በከበባት አውሬያዊ አዬር ከሁሉ በላይ ሥም የለሹን የዶር አብይ አህመድ #ቁንጥንጥ አመራር አስክኖ ኃላፊነትን መወጣት ግማድ ነው።
በአንድ ውይይት አወያይ ሞገተን ብለው ውይይቱን ኃራም ብለው የራሳቸው ጎጆ የሚቀለሱ፣ አቅል የሚያንሳቸው፣ መንፈሳቸው ስስ የሆኑ ግን የፖለቲካ ታጋዮች ባለበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጠቅላዩ ጋር መሥራት ግማድ ተሸክሞ መኖር ነው። ከእሺ ውጪ አይን አይፈቅዱም ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ።
ሌላው በተቋሙ ውስጥ ቅምጥ ፍላጎት ያላቸው አይኖሩም ማለት አይቻልም። የሎጅስቲክስ አቅርቦቱም እንዲሁ ሌላው መከራ ነው። ከሁሉ በላይ #የሚፈቀድለት እና #የማይፈቀድለት መከራም አለ።
እና በዚህ ትብትብ ሁኔታ ፍንጣቂ #ኢስክራ ከተገኜች ተመስገን ነው። ዘመኑ ከገባን።
ሌላው አሁን ላለሁበት ሙሉ ዕድሜ፣ ከጋሜ እስከ ግራጫማ ፀጉር ለተደረሰበት የፖለቲካ ተመክሮም መቻኮል አይገባም። ችኩል ልሁን ቢባልም አይፈቀድም።
ይልቅ የጎደለውን እዬሞላን የተሻለ ሞጋች ሆኖ ይቀርብ ዘንድ በሃሳብ እንገዘው። እኔ ግን ሥርጉተን ተውሻት፣ ተበድሬያት ሳይሆን እራሷ መሆኗን ተረዷት።
ውራጅ ሰብዕና ድርሽ ብሎብኝ አያውቅም። ጎርፍ አምጥቶ የከመረኝ የፖለቲካ ታጋይም አይደለሁም……… ገብሬ መድህን በርጋ በፅኑ አቅም የቀረፃት ናት ሥርጉትሻ፣ ገብሬን ታውቁታላችሁ ለፖለቲካ ሰብዕና ዩንቨርስቲ ነው። ሌሎችም ብዙ ደክመዋል እኔን በፖለቲካ ሰብዕና፣ በራዲዮ ጋዜጠኝነት አንፆ ለማብቀል።
#ሥርጉተ ሥላሴ //
#Sergute Selassie//
#Sergute Selassie ሥርጉተ ሥላሴ// ብላችሁ አጤ ጉግል ይጠዬቅ፣ ይነግራችኋል ቢያንስ ከ2008 ጀምሮ ያለውን ከዛም በፊት ብዙ በጣም ብዙ ቁምነገር ተከውኗል። የማይታፈርበት። ትናንትም፣ ዛሬም እሷ እሷ ናት።
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ትሞግታለች፣ ድንቅ የሰሩትን ታመሰግናለች፣ ሲስቱ ትወቅሳለች።
ቀድሞ ነገር የትኛውም ፖለቲከኛ የሰው ሥም አንስቶ የሚያሞግሥ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ የለም። ሲሞቅ እና ብዙ ተከታይ ሲገኝ አይደለም። ያን ለአሸብሻቢዎች። በዛ ነግሰው ተቀድሰው ለዘለቁ …
ሥርጉትሻ እንዲያውም ሠርተው ደክመው ችል ሲባሉ፣ ምስጋናቸው ሲነጥፍ ነው አጉልታ የምታወጣ። በዚህ ለራስ ክብር፣ ለራስ ዝና ሌት እና ቀን በሚማሰንበት ዘመን።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
19/02/2021
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ማለፊያ ቀን ተመኜሁ።
ኑሩልኝ ጭምት ተከታዮቼ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።