ልጥፎች

ከ2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ማሸነፍ #በሃሳብ #ልቅና #በድርጊት #ልዕልና።

  #ማሸነፍ #በሃሳብ #ልቅና #በድርጊት #ልዕልና ።   "ዳግመኛ አርበኞች ቢከቡኝ እኔ በሱ አመንሁ እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንሁት ያቺኑ እፈልጋለሁ ብሎ እንደ ተናገረ በሱ ያመኑ ሰወች ፍራት የለባቸውም በሱ ያመነ ሰው ለዘላለሙ በሕይወት ይኖራል ከክፋ ነገርም የተነሣ አይፈራም" (መቃብያ ፯ ቁጥር ፫)   #ምዕራፍ ፳።   አዱኛወቼ ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት ነን? ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጵያ እንዴት አድረሽ - አረፈድሽ ይሆን?   #ዕፍታ ላፍታ።   ማሸነፍ ደስታ ይሰጣል። መሸነፍ ደግሞ ውስጥን ያጠነዝላል። ለብልህ ሰው ግን መሸነፍን የመቀበል አቅም ከኖረው ውስጡ ሳይጠነዝል ወይንም ሳይጠወልግ ለቀጣይ የህይወት መስመር ሁሉ ከእግዚአብሄር ነውና አቅሙን አበረታቶ፤ ከአቅሙ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ መክሮ እንደ ገና አወን እንደገና የመነሳት ዕድል ሊኖር ይችላል።   #ማሸነፍ ። የሚያሸንፈው ጥራት ያለው ሃሳብ እና ድርጊቱ ነው። #መሸነፍ ። የሚሸነፈው እና የሚወድቀው ሃሳቡ እና አካሄዱ ነው። #መሸናነፍ ። ቅይጥ ነው ይሄ የኪሳራ እና የትርፍ ምንዛሬ። የታክቲክ እና የስትራቴጂ ክህሎትም።   በጦር ሜድ ብቻ አይደለም የለቱ የወግ ገበታዬ ሊያጋራችሁ ያሰበው። በማህበራዊ፤ በጥበባዊ፤ በሃይማኖታዊ፤ በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በትዳራዊ ወዘተ ገጠመኞች ውስጥ ሰው በሁለት ቢከፍለውም የእኔ ፈንገጥ ያለው ዕይታ #መሸናነፍ የሚል አክዬ ወደ ሦስት ከፍ አድርጌዋለሁኝ። ተጋጣሚው ድህነት ቢሆን ብላችሁ እሰቡት ወይንም ጤና ማጣት ቢሆንስ ብላችሁ ዕድል ስጡት፤ ወይንም ትምህርታዊ ጉዳይስ ቢሆን ብላችሁም ማስላት ትችላላቸው። መኖር እና ጅረቱ ወዘተረፈ ነውና።    #ተዚህ ላይ ፈንገጥ ያሉ ዕይታወቼን ብ...

ኢትዮጵያዊነት የሳሙና #አረፋ ፕሮጀክት አይደለም።

  ኢትዮጵያዊነት የሳሙና #አረፋ ፕሮጀክት አይደለም።   "ዳዊት በእግዚአብሄር አመንኩ፤ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል ብዬ ብሎ እንደ ተናገረ በእግዚአብሄር ባመኑ ሰወች ግን ፍርሃትና ድንጋፄም የለባቸውም።" (መጽሐፈ መቃብያን ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፩።)   #ምዕራፍ ፳።   #ጠብታ ።   የእኔ ክብረቶች እንዴት አደራችሁ? አረፈዳችሁ? ዋላችሁልኝ? ፈላስፊት ኢትዮጵያስ በአያሌው እንደምን አለሽልኝ? ከቶ አዳርሽ እንደምን ሆኖ ይሆን? #አይዞሽ እናቱ። ስለ ኢትዮጵያዊነት እኔ ስጽፍ በመኖር ውስጥ ሆኜ ፈትኜ ያገኜሁትን ቁም ነገር ነው የማጋራችሁ። ኢትዮጵያዊነትን ከፖለቲከኞች አንፃር ሰፍሬው አላውቅም።    ኢትዮጵያዊነት ከፖለቲከኞች በፊት የቀደመ ስለሆነ፤ ከእነሱ ጋር ማፎካከር የኢትዮጵያዊነት ደረጃ ይፈቅደዋል የሚል ዕምነት የለኝም። ኢትዮጵያዊነት ከኦርጋኒክ የተገኜ፤ አርቲፊሻል ወይንም ፌክ ያልሆነ ስለመሆኑ መኖሬ አስተምሮኛል እና።    ስለሆነም የእኔን የልብ ትርታ፤ መንፈሴን ስገልጽ የኢትዮጵያዊነት የሥልጣኔ ክህሎት ለውስጤ ብርኃን አመንጭነቱን ደርሶኝ የምመገበው የመንፈስ የማይነጥፍ #ጥሪቴ ስለሆነም ነው። ከእቅፋ ፈቅ ብዬ አላውቅም። ስለሆነም ማህባው፤ ጸዳሉ፤ ማዕረጉ ይሁን ሞገሱ ተነጥሎኝ አያውቅም።   በመዋለ ዕድሜዬ በኢትዮጵያዊነት ላይ በሚያላግጡ፤ በሚያቃልሉ፤ ቅናት ድብን አድርጎ እንደ እህል በሚወቃቸው፤ የሚቁነጠነጥ መንፈስ በሚኖራቸው ፤ የሚረገርግ ስሜት ያላቸውን ነፍሶች አላዳምጥም። በሽታ በጊዜየ ለመግዛት ፈቃደኛ አይደለሁም እና። ቁርጡን ስነግራቸው ኢትዮጵያዊነ መንፈሱ #የማይደረስበት ማንነት ስለመሆኑ ማህተም አለበት።   "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"...

#ጨርሶ - #መጨረስ #መጫረስም #ዛሬን #ያደርቀዋል- ነገን ያጨሰዋል።

  #ጨርሶ - #መጨረስ #መጫረስም #ዛሬን #ያደርቀዋል - ነገን ያጨሰዋል።   "አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በዕውነት አድርገኃልና ከፍ ከፍ አደርግኃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ።" (ትንቢተ ኢሳያስ፤ ምዕራፍ ፳፭ ከቁጥር ፩ - ፪)   (ምዕራፍ ፳።)   ክብሮቼ ማህበረ ሥርጉትሻ ቅኖቹ የውስጦቹ እንዴት አደራችሁልኝ? እንደምን አረፈዳችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ እናንተን ይዤ ምንም አልሆንም። ትህትናችሁ፤ ሙግታችሁ፤ ቅንነታችሁ ቁሞ አዘውትሮ ያስተምረኛል። ለእኔ ዩንቨርስቴወቼ ናችሁ። ኑሩልኝ። አሜን።   #በር እንደ መግቢያ።   ዕድሜ ስክነትን፤ ዕድሜ እርጋታን፤ ዕድሜ ጭምትነትን ካልሰጠ እኔነት ይሰወራል ወይንም ይሸሻል። ወጣቶች ዕድሜያቸው የሚያስገድዳቸው ሁነቶች አሉ። ተሎ ተስፋ መቁረጥ፤ መበሳጨት፤ ትዕግስት ማጣት፤ መቸኮል፤ መጣደፍ፤ መጓጓት፤ መቆጣት ረጃጅም የሆኑ የኩርፊያ አስፓልቶችን መዘረጋጋት። ይህን አታድርጉ፤ እንዲህም አትሁኑ ወጣቶችን ለማለት አይቻልም። ትክክልም ነው ብዬ አላምንም።   ምክንያቱም እኛም አልፈንበታልና። ግን ነገር ግን የተሻለውን መንገድ የማሳየት ግዴታ ከታላላቆቻቸው ይጠበቃል። ወጣቶችን አግልሎ፤ ከውስጥም አርቆ፤ ደንበር ይሁን ወሰን ሠርቶ ሳይሆን እንደ እራሳችን የአብራክ ይሁን የመሃጸን ፍሬ አድርጎ መቀበል ቀዳሚው ተግባር ከታላላቆች የሚጠበቅ ይመስለኛል።   #ከውስጤ ለውስጤ።   ጨርሶ የውስጥን ብስጭት የግዴታ መስመር መከተል፤ በባሩድ ብቻ ሳይሆን በአሽሙር ይሁን ይፋዊ ግሳጼ ሰብዕናን ያለገደብ መዳፈር፤ ለዛሬም ለነገም ሳያስቀሩ መደፋፈር ይሁን እላፊ መሄድ፤ አጋጣሚው ሲገኝም ለዘር ሳያስቀሩ ሙልጭ አድርጎ የክፋ ሃ...

#ደስታን መጥኖ ስለማስተዳደር። እዮራዊ ምርቃት እንዳይነሳ።

  #ደስታን መጥኖ ስለማስተዳደር። እዮራዊ ምርቃት እንዳይነሳ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስ።" አሜን። (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፲)   #ምዕራፍ ፳። (20) ተመስገን።   #ለውዶቼ ለአዱኛወቼ ትሁታዊ ጤና ይስጥልኝ። ለማህበረ - ቅንነት፤ ለቤተ - ሥርጉትሻ ውዶች ህሊናዊ ክብር እና ትሁታዊ ሰላምታ እንሆ። እንዴት አላችሁልኝ። የምር ንፍቅቅ ብላችሁኛል።    የዕውነት የውስጤ ውስጥ መሆናችሁ የሚገለጥልኝ እንዲህ ሳላያችሁ ስስነብት ነው። ስንብቾው እንዴት ነው። እንቁጢ እንዴት አለፈች?   በመስከረም በርካታ ወገኖቻችን ልዩ የበዓል ሴሪሞኒ አላቸው። በዚህ አጋጣሚ እንኳን አደረሳችሁ። በዘርፋ ደካማ ነኝና፤ ሳላስታውስ ስቀር እለፋኙ።    በተረፈ 2019 ሰላም በእያንዳንዳችን ቤት የሚገባበት ያድርግልን። አሜን።    1) #ደስታና ሐሤት ምን እና ምን ናቸው በሥርጉዬ - ፍልስፍና። 1.1) ደስታ ምድራዊ፤ ሰው ሠራሽ፤ ጊዜያዊ እና ቆይታውም የማይታመን፤ ትነት ሊገጥመው የሚችል። 2.2) ሐሤት ሰማያዊ እና አማኑኤል ሠራሽ ገኃዱ ዓለምንና መንፈሳዊውን ዓለም የሚያገናኝ ቋሚ እና ዘላቂ ድልድይ። የምድራዊውን ደስታ በሚመለከት የመጀመሪያ ጹሁፌ የመቀሌ በመከላከያ ሥር ገባች ርችት፤ ፈንጠዝያ፤ ፌስታ ጊዜ ነበር የፃፍኩት። ከዛም በኋላ በተለያዬ ጊዜ የተንጠራራ የፌስተ ድለቃ ሳስተውል በልክ ያዙት በማለት ማሳሰቢዬ አልቀረም።   2) #ለምን ?   2.1) ባለ ደስታው ተጨማሪ ደስታ ሲያገኝ #መደርደሪያ እንዳያጣ፤ ማስቀመጫው፤ እንዳይጠበው። 2.1) ባለ ደስታው ደስታው እየራቀው ሲሄድ ተስፋ ቆራጭ ሆኖ ለሥነ - ልቦና #ህመም እንዳይዳረግ። 2....