«ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ « እርዕሱ የፋና ነው።
«ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ « እርዕሱ የፋና ነው።
"መግለጫ" እንደምን እንዳሉት አላውቅም።
«ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ «
ኮሚሽኑ ምን ላይ እንዳለ፤ ቀጣይ አቅጣጫው ምን ሊመስል
እንደሚችል የሚብራራበት ነው።
የሆነ ሆኖ ተያያዥነት እንዲኖረውም ከሶስት ቀን በፊት፤ እንዲሁም
ከስድስት ቀን በፊት የነበረውንም ሊንክ አክላለሁኝ።
የገረመኝ ግን የተወሰነ አትኩሮቱ አቅጣጫው በምክክር ኮሚሽኑ ላይ መሆኑ፤
ጠቅላይ ሚር አብይ ደግሞ በመሃል በቃለ ምልልስ ብቅ ብለዋል።
ያው እንደ ተለመደው አንዱ አመክንዮ ሳይቋጭ ደግሞ ወደ ሌላው የመንፈስ #ብክነት ……
በዚህ መሃል ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ብቅ ብሎ እንዲህም እንዲያም
ያው ያስኮናል።
#ክወና።
የሆነ ሆኖ የአገር ጉዳይ #የትንፋሽ ነውና ማን ይከውነው ማን፤ ይህን መሰል
ግዙፍ አገራዊ ጉባኤ በአትኩሮት መከታተል የተገባ ይመስለኛል።
አገሬን ያለ፤ በዕቴን ያለ፤ መከፋቷን ውስጡ ያደረገ፤ በተለይ በፖለቲካዊ
ጉዳዮች ላይ አትኩሮት ያለው ሰብዕና ስለእናቱ ጉዳይ መከታተል ይገባዋል።
ምን ይሁን ምን? #መሞገትም የሚቻለው በስማ በለው ሳይሆን አክብሮ
ማዳመጥ ሲቻል ነው።
"በየጊዜው እግዚአብሄርን አመስግነው፤
ጎዳናህ የቀና ይሆን ዘንድ ወደ እርሱ
ለምን፤ በጎዳናህ እና በሥራህም ሁሉ
ይከናወንልሃል። በጎውን ምክር ሁሉ
የሚሰጥ እግዚአብሄር ነው።"
(መጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፱።)
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
31/07 026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ