#ለምህረት ይሁን #ለይቅርታ #ቅድመ ሁኔታም ይሁን #ቀጠሮ አያስፈልገውም።

 

#ለምህረት ይሁን #ለይቅርታ #ቅድመ ሁኔታም ይሁን #ቀጠሮ አያስፈልገውም።
 
"እግዚአብሄርም እንዲህ ይላል፦ -----
በመንገድ ላይ ቁሙ፤ ተመልከቱም ፥
የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤
መልካሚቱ መንገድ ወዴት
እንደሆነች እወቁ፥ በእርሷም ላይ
ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ፤
እነርሱ ግን፦ - አንሄድባትም አሉ።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፲፮።)
 
 May be an image of one or more people, braids and people smiling
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
የሰው ልጅ ፍጥረተ - ነገሩ ከታወቀው ከሥጋ፤ ከአጥንት፤ ከመንፈስ፤ በሃይማኖት እራሱን የቻለ የአፈጣጠር ሚስጢራት አሉ። አቨው ይሂዱበት፤ እኔ በገሃዳዊው ዓለም መኖርን በማኖር ሂደት ያሉ ቅይጥ ሁነቶች ላይ ብቻ ነው አትኩሮቴ።
 
ብቻ የሰው ልጅ ከተፈጠረባት #ትንፋሽ ባላነሰ ይቅርታም፤ ምህረትም፤ እርቅም፤ ትህትናም፤ አድማጭነትም፤ መታመንም፤ መሰጠትም፤ አክብሮት፤ መቀበልም፤ ቅንነትም፤ ትህትናም፤ ደግነትም፤ ሐሤትም፤ አብሮነትም፤ ትዕግስትም፤ ማፍቀርም፤ መፈቀርም፤ መውደድም፤ መቻቻልም፤ መወደድም፤ እሽታም፤ ምርቃትም፤ ሃቅ፤ ምስጋናም፤ ስጦታም፤ ዕውቀትም፤ መክሊትም፤ ጥሪም ወዘተ ከተፈጠረበት ቅብዓ ንጥረ ነገሮች ጋር ተነጣጥለው ሳይሆን እሱነቱ ከተዋቀረበት አካላቱ፤ ሚስጢራቱ ጋር #ተዋህደው ተፈጥረውለታል።
 
የሰው ልጅ - ከወደደ፤ የሰው ልጅ - ከፈቀደ፤ የሰው ልጅ መቻሉን ካስቻለ #ተመርቆ በተፈጠረበት ልክ መሆን ይችላል። #ከልካይ የለበትም። እንደ እኔ ፅኑ እምነት የሰውልጅ ተባርኮ፤ ጸድቆ፤ ጹሞ ነው የተፈጠር ብዬ አምናለሁኝ።
 
ውዷ ዓለማችን ግን የተፈጠርንበትን የምርቃት ንጥረ ነገር የምታስቀጥልበት #ቋሚ ተቋም የላትም። ስለሆነም የሰው ልጅ #መሰጠት #ብክነት ገጠመው ብዬ አስባለሁኝ።
 
የሰው ልጅ በራሱ አፈጣጠሩ - በሚስጢር፤ ለሰማያዊ ሚስጢር ዕውንነት የተፈጠረ፤ ዘለግ ባለ ሁኔታ ለሊቅነት ይሁን ለሊህቅነቴ #የዊዝደም ሚስጢርም በምልዓት የተሰጠው ነው ብዬ አስባለሁኝ። አምናለሁኝ።
 
ግን የሰው ልጅ በልኩ ለመኖር እንዳይችል ያደረገው ወደ መሬት ሲመጣ #የሚቀበለው ክፋ ሃሳብ ይፈትነዋል። ክፋ ሃሳብ ያጠምደው እና አብሮት ያድጋል፤ ይጎለምሳል፤ ያረጃል እራሱን ሳያርምም ፍፃሜ ሊሆን ይችላል። በቅድስት ተዋህዶ ዕምነት ለንሥኃ ለፍታት ሳይበቃ ይቀራል። የሰው ልጅ በተፈጠረበት ረቂቅ ጸጋ እና ክብረት ውስጥ ለመኖር አለመቻሉ የተፈጠረበትን እዮራዊ ሚስጢር #ያፈሳል
 
የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ሚስጢር ሲነጠል የክፋ ሃሳብ ተገዢ ይሆናል። #ምርቃቱም ይነሳል። ስንክልክል፤ ብትልትል፤ ብክንክን ዕጣ ፈንታም ይሆናል። ቢሳካ እንኳን የውስጥ ሰላም፤ የውስጥ ሐሤት ይርቃል። 
 
ሁልጊዜ መንፈስ ጎስቁሎ ወይንም ጓጉሎ #ስደት ይሆናል። ከራስ ጋር ተስማምቶ መኖር የማይቻልበት ሁኔታ ይከሰታል። ለእኛ በተፈጠረ ዓለም በቁዝምታ ተወጥኖ በቁዝምታ ዘመን ይጠናቀቃል።
 
ክፋ ሃሳብ በዓለም የምናያቸው ጸረ - ሰው፤ ጸረ - ተፈጥሮ ፈፃሚ እና አስፈፃሚም ነው። ወንጀል፤ ጭካኔ፤ ብስጭት፤ ግለት፤ ጫና፤ ግድያ፤ ጥላቻ በበቀል፤ ቂም፤ ቅናት፤ ምቀኝነት፤ ግላዊነት፤ አሉታዊነት፤ ተንኮል፤ ሴራ ወዘተ ሁሉም ለእኛ #የተፈጠሩ አልነበሩም።
 
መዳናችን፤ ፈውሳችን፤ ጸጋችን፤ ክህሎታችን፤ መቻላችን፤ መሆናችን በተሰጠን ሚስጢር ልክ ይሆን ዘንድ ወደ ተፈጥሯችን ልንመለስ ይገባል። ብዙ - አጥፍተናል። ብዙ - ተበዳድለናል። በብዙ - ተቀያይመናል ይህን #በምህረት በመጠዬቅ፤ በመስጠት እና በመቀበል፤ በይቅርታ በመጠየቅ፤ በመስጠት እና በመቀበል ውስጣችን #ይታጠብ ዘንድ ብንፈቅድ ምርቃታችን ይመለስልናል።
 
ለይቅርታ ይሁን ለምህረት ቀነ - ቀጠሮ ወይንም ቅድመ ሁኔታ #አያስፈልግም። የግል ንጽህናን መፍቀድ ውስጥን ያጥባል። ህሊናን ያጸዳል። ቆይታችን በጣም አጭር ነው። የእኔ የምንለው #ሰከንድ የለም። ሰከንዱ የፈጣሪያችን፤ የአምላካችን፤ የአላኃችን ነው።
 
የዘመን ጸጋ ባለቤት አለው። ፈጣሪው። እኛ የዘመን ባለቤት አይደለንም። ስለሆነም ቀናችን ሳይጠናቀቅ ለምህረትም፤ ለይቅርታም #ቅርብ እና ናፋቂም ልንሆን ይገባል። በኢትዮጵያ በአስተሳሰባቸው፤ በሃይማኖታቸው የሚገፋ፤ የሚገለሉ፤ ጫና ያለባቸው፤ የሚገደሉም የሚሰወሩም፤ የሚሰወሩም፤ የሚታገቱም ወገኖች አሉን።
 
ፈጣሪ የፈጠረው ፍጡር፤ ከፍ ያደረገው ሩህ የአንድ አገር ሹመኛ፤ የሃይማኖት መሪም ሊሆን ይችላል የአምላክን ውለታውን ቢያንስ በበዛ ትዕግስት ውስጥ ሆኖ #በምህረት እና #በይቅርታ ወገኖችን በድርጊት ለማስተማር ቢተጋ የፈጣሪ ምርቃት #ይበረክታል። በስተቀር ግን ብክነቱም ይሁን መባተሉ የውርንጫ ድካም ይሆናል። ትውልድም አያበረክትም።
 
በጣም የሚናፍቀው ክስተታዊ ነገር #ወጣትነት ነው። የወጣትነት ጊዜ እንዴት ባጀህልኝ ስስቴ ብየዋለሁኝ።
 
ቤተ - ሥርጉትሻ ውዶቼ ኑሩልኝ። አሜን።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
30/07/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።