#መድህን።

 

"ከመምህራን ዘንድ ምክርን ፈልግ፤
 
 
 May be an image of map and text that says 'ኤርትራ Eritrea ባህረ ነጋሽ ትማራይ Tigray ጎንደር በጌ ምድር Begmender Wello Gojjam ወለጋ Welega ሸዋ Shewa पजन ኡማ ጋባቦር niubabor ሐረርጊ Hararghe Kalfa Gamu Gofa ባሌ Bale Sidamo ሲዳሞ'
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
መድህን #መዳኛ#መፈወሻ ማለት ነው። ቃለ ወንጌልም ነው።
ህመማችን ዝልቅ መፍትሄችን ሩቅ ሆኖ ትውልድ ሲገበርበት ኖረ።
ዘመን #ይፍታህ ለማለት ፍቱን መዳህኒቱ ለእኔ ይህ የቀደመው፤
የኢትዮጵያ ካርታ ብቻ ይመስለኛል። 
 
#ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ወንዞችን፤ ተራሮችን መለያ፤ መወሰኛ አድርገው
አቨው እና እመው ወደ ሠሩልን አቅጣጫ ብንመለስ ዛሬ እንዲህ ህሊናችን
እምስምስ ከሚልበት ትርምስ ወጥቶ ዘመን ሰጥ ሥልጣኔወች ጋር ማተኮር
በተቻለ።
 
በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ የምክክር የጉባኤ አባላት ከሚወያዩበት በህረ ጉዳይ
ይህ ነውና መድከም ካልቀረ #የሰመረ ጣፋጭ ውሳኔ ላይ ቢደረስ መልካም
ይሆናል። 
 
"#የድሮ ናፋቂ " ይባላል ሰላምን መኖርን የሚለግሥ ከሆነ ስለምን አይናፈቅም።
 
#አንድ ዶላር እና አንድ የኢትዮጵያ ብር እኩል የሆነበት ዘመን፤ በግ ተገዝቶ ቆዳው ተሽጦ ሥጋው ነፃ የሆነበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም?
#ለትምህርት ወደ ውጪ የተላከው ሁሉ ስደትን አሻም ብሎ ወደ አገሩ የሚመለስበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም?
#አንድ ኩንታል ጤፍ በጥቂት የብር ኖቶች ይገዛ የነበረበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም?
#ሰው መሆን ብቻ ቁምነገር የሆነበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም?
#የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከክብሩ ወርዶ የማይነድበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም?
#ዜጋ በባዕቱ የማይሳደድበት፤ ሥልጣኔው የማይነቀፍበት ወይንም የማይነቀልበት ዘመን ስለምን አይናፍቅም?
ወዘተ ……… ወዘተ ……… ………ወዘተ ………
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን፤ አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን፤ አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
31.07.026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።