ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 24, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የሌሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ድብ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።

ምስል
  የሌሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ድብ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     በክርስትና ሆነ በእስልምና መሠረቷ በጸናው ኢትዮጵያ አገራችን በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እዬታዬ ነው። ዘለግ ላለ ጊዜ የቆዬ ንዝረት ሌሊት እንደ ነበረ ዘገባወቹ ይናገራሉ። #ሰውኛነቱ ፈተና ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ በሰው ሰራሽ ድሮን የአማራን ህዝብ #እያፈለሰ ፤ #እያሸበረ ፤ #መጠጊያ እያሳጣ ነው።   ዛሬ ሌሊት የአዲስ አበባ ነዋሪወችን በማስደንገጥ የቀሰቀሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ የአገራችን በዕቶች እንደነዘረ ባለሙያወች ይናገራሉ። በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙትን ከተሞች እና እንዲሁም በአዋሽ፦ ጭሮ ዙሪያ፤ በድሬድዋ፤ ናዝሬት፤ ደብረዘይት፤ ደብረብርሃን፤ መተሃራ፤ ከሚሴ፥ ደሴ ወዘተ ተከስቷል።    ይህን ሰማያዊ የማስጠንቀቂያ #ቃል #ባሊህ ብሎ በፆም በጸሎት፦ በድዋ፦ በሱባኤ ለላይኛው አቤት ማለት ሲገባ በገፍ የአማራ ልጆች #ይታሰራሉ ፤ በገፍም ወደ ጦርነት በሚያመሩ ጉዳዮች ሰፊ ሽፋን እዬተሰጠ ይገኛል። #ጭካኔው ፤ #ጥላቻው ፤ #የአለመደማመጡ ሁኔታ አይሎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጎልቶ ይታያል።    ኢትዮጵያ ሰውኛ፤ ተፈጥሮኛ ፖለቲከኛ ቢኖራት አገራዊ የፀሎት ጊዜ ሊታወጅ በተገባ ነበር። አደብ ገዝቶ ይህን ወቅት በራሱ ወደ ዘላቂ #መፍትሄ ለማምራት ትልቅ አጋጣሚ ነበር።    የሰማይ ቁጣ ማስጠንቀቂያ ከመጋቢት 18/2010 ዓም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ለመምጣት ዋዜማ ላይ እያሉ ነበር ሌሊት በዋዜማው በመቀሌ አቅራቢያ የመሬት ንዝረት የተከሰተው። ከዛም የዶር አብይ የ100 ቀናት ሳይጠናቀቅ ነበር መሰል የሰማይ ማስጠንቀቂያ በጉ...

የሰባዊነት ልዩ #ዓርማ የነበሩት የሆኑትም የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር የዶር አንጌላ ሜርክል ፓርቲ (CDU+ CSU)ወደ ቁልፍ ሥልጣን ተመለሰ።

ምስል
  የሰባዊነት ልዩ #ዓርማ የነበሩት የሆኑትም የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር የዶር አንጌላ ሜርክል ፓርቲ (CDU+ CSU)ወደ ቁልፍ ሥልጣን ተመለሰ።   "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤  እግዚአብሄርግን አካሄዱን ያቃናለታል።"  (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)       በእኔ ዘመን ከተከሰቱ ድንቅ #ክስተት መሪወች፤ #ዕንባን አድማጭ የዓለም ሊሊቀ - ሊቃናት፤ ለየትኛውም አገር የሰባዕዊነት፤ የየንግሥታት ችግር ልዩ #አትኩሮት እና #ቅድሚያ ከሰጡ መሪወች በቁጥር አንድ የእኔ ልዕልት ዶር አንጊላ ሜርክል ናቸው። ፍፁም ሰውኛ፤ ፍፁም ተፈጥሮኛ #በ100 ዓመት ፕላኔታችን ደግማ የማታገኛቸው ልዩ የዓለም #ሥጦታ ናቸው። እኔ ቀጣዩን #የተመድ #ቁልፍ ቦታም ቢሰጣቸው የዓለማችን ምስቅልቅል ፖለቲካ #ፈውስ ያገኛል ብዬ አምናለሁኝ። አድማጭነታቸው፤ የእናትነት ፀጋቸው የመሰጠታቸው አቅም ልዩ ነውና። እኔ በክብርትነታቸው ሁልጊዜም ለምንጊዜም አምላኬን መማኑኤልን አመሰግናለሁኝ።    የሆነ ሆኖ በዚህ ዓመት የጀርመን የምርጫ ሂደት ልብ አንጠልጣይ ስለነበር፦ በተወሰነ ደረጃ ተከታትዬው ነበር። ትናንት ከምወደው የጀርመን ሚዲያ ውስጥ አንዱ በሆነው #በRTL ሂደቱን ተከታትዬው ነበር። ነፍሴ ተንጠልጥላ። ግሩንም እድገት ማሳዬቱን ተመልክቻለሁኝ። የሰብዓዊ መብትን ጥሰት፤ ድህነትን ሽሽት ወደ አውሮፓ የሚጎርፈው ስደተኛ ህይወት እንዴት ይሆን በማለት ነበር የተከታተልኩት።   እርግጥ ነው ስደተኛ የየአገሮችን #ህግ በማክበር፤ በጨዋነት፤ በዲስፕሊን፥ #ዕድልን በማክበር፦ መኖር ሲገባ ጭራሽ በወንጀላዊ ድርጊት መሳተፍ፤ ያስጠጋን አገር ህዝብ ስለስጋት መዳረግ፤ ተጨማሪ ጫና መፍጠር፤ #ህይወትን #ያስቀጠ...