የሌሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ድብ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።

 

የሌሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ድብ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
በክርስትና ሆነ በእስልምና መሠረቷ በጸናው ኢትዮጵያ አገራችን በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እዬታዬ ነው። ዘለግ ላለ ጊዜ የቆዬ ንዝረት ሌሊት እንደ ነበረ ዘገባወቹ ይናገራሉ። #ሰውኛነቱ ፈተና ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ በሰው ሰራሽ ድሮን የአማራን ህዝብ #እያፈለሰ#እያሸበረ#መጠጊያ እያሳጣ ነው።
 
ዛሬ ሌሊት የአዲስ አበባ ነዋሪወችን በማስደንገጥ የቀሰቀሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ የአገራችን በዕቶች እንደነዘረ ባለሙያወች ይናገራሉ። በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙትን ከተሞች እና እንዲሁም በአዋሽ፦ ጭሮ ዙሪያ፤ በድሬድዋ፤ ናዝሬት፤ ደብረዘይት፤ ደብረብርሃን፤ መተሃራ፤ ከሚሴ፥ ደሴ ወዘተ ተከስቷል። 
 
ይህን ሰማያዊ የማስጠንቀቂያ #ቃል #ባሊህ ብሎ በፆም በጸሎት፦ በድዋ፦ በሱባኤ ለላይኛው አቤት ማለት ሲገባ በገፍ የአማራ ልጆች #ይታሰራሉ፤ በገፍም ወደ ጦርነት በሚያመሩ ጉዳዮች ሰፊ ሽፋን እዬተሰጠ ይገኛል። #ጭካኔው#ጥላቻው#የአለመደማመጡ ሁኔታ አይሎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጎልቶ ይታያል። 
 
ኢትዮጵያ ሰውኛ፤ ተፈጥሮኛ ፖለቲከኛ ቢኖራት አገራዊ የፀሎት ጊዜ ሊታወጅ በተገባ ነበር። አደብ ገዝቶ ይህን ወቅት በራሱ ወደ ዘላቂ #መፍትሄ ለማምራት ትልቅ አጋጣሚ ነበር። 
 
የሰማይ ቁጣ ማስጠንቀቂያ ከመጋቢት 18/2010 ዓም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ለመምጣት ዋዜማ ላይ እያሉ ነበር ሌሊት በዋዜማው በመቀሌ አቅራቢያ የመሬት ንዝረት የተከሰተው። ከዛም የዶር አብይ የ100 ቀናት ሳይጠናቀቅ ነበር መሰል የሰማይ ማስጠንቀቂያ በጉራጌ ዞን የተከሰተው። ያን ጊዜ አስደንጋጭ ድምጽ ከሰማይ ተሰምቷል። መሬት ከሁለት ተገምሷል። ግን አድማጭ አላገኜም። 
 
አሁንም ጭካኔን በመግታት ወደ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ መንፈስ ለመመለስ ጥሞና ለኢትዮጵያ ፖለቲካ በእጅጉ ያስፈልጋል። እኛም እራሳችን ይህን ጉዳይ ወደ ልባችን አስገብተን ልንታረምበት ይገባል። "#ህግ #መተላለፋ" እከሌ ከእከሌ የለበትም እና።
ክብረቶቼ እንዴት አደራችሁልኝ። ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/02/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?