የሰባዊነት ልዩ #ዓርማ የነበሩት የሆኑትም የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር የዶር አንጌላ ሜርክል ፓርቲ (CDU+ CSU)ወደ ቁልፍ ሥልጣን ተመለሰ።

 

የሰባዊነት ልዩ #ዓርማ የነበሩት የሆኑትም የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር የዶር አንጌላ ሜርክል ፓርቲ (CDU+ CSU)ወደ ቁልፍ ሥልጣን ተመለሰ።
 
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
 እግዚአብሄርግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
 (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
 
 
 
በእኔ ዘመን ከተከሰቱ ድንቅ #ክስተት መሪወች፤ #ዕንባን አድማጭ የዓለም ሊሊቀ - ሊቃናት፤ ለየትኛውም አገር የሰባዕዊነት፤ የየንግሥታት ችግር ልዩ #አትኩሮት እና #ቅድሚያ ከሰጡ መሪወች በቁጥር አንድ የእኔ ልዕልት ዶር አንጊላ ሜርክል ናቸው። ፍፁም ሰውኛ፤ ፍፁም ተፈጥሮኛ #በ100 ዓመት ፕላኔታችን ደግማ የማታገኛቸው ልዩ የዓለም #ሥጦታ ናቸው። እኔ ቀጣዩን #የተመድ #ቁልፍ ቦታም ቢሰጣቸው የዓለማችን ምስቅልቅል ፖለቲካ #ፈውስ ያገኛል ብዬ አምናለሁኝ። አድማጭነታቸው፤ የእናትነት ፀጋቸው የመሰጠታቸው አቅም ልዩ ነውና። እኔ በክብርትነታቸው ሁልጊዜም ለምንጊዜም አምላኬን መማኑኤልን አመሰግናለሁኝ። 
 
የሆነ ሆኖ በዚህ ዓመት የጀርመን የምርጫ ሂደት ልብ አንጠልጣይ ስለነበር፦ በተወሰነ ደረጃ ተከታትዬው ነበር። ትናንት ከምወደው የጀርመን ሚዲያ ውስጥ አንዱ በሆነው #በRTL ሂደቱን ተከታትዬው ነበር። ነፍሴ ተንጠልጥላ። ግሩንም እድገት ማሳዬቱን ተመልክቻለሁኝ። የሰብዓዊ መብትን ጥሰት፤ ድህነትን ሽሽት ወደ አውሮፓ የሚጎርፈው ስደተኛ ህይወት እንዴት ይሆን በማለት ነበር የተከታተልኩት።
 
እርግጥ ነው ስደተኛ የየአገሮችን #ህግ በማክበር፤ በጨዋነት፤ በዲስፕሊን፥ #ዕድልን በማክበር፦ መኖር ሲገባ ጭራሽ በወንጀላዊ ድርጊት መሳተፍ፤ ያስጠጋን አገር ህዝብ ስለስጋት መዳረግ፤ ተጨማሪ ጫና መፍጠር፤ #ህይወትን #ያስቀጠለ መንግሥትን እና ሥርዓትን ማወክ በፍፁም የተገባ አይደለም። ወረታ ከእግዚአብሄር ዘንድ ይሁን እንጂ ደጋግ አገሮች ቢያንስ ሰላማቸው እንዳይታወክ #በጥንቃቄ መኖር የስደተኛ ግዴታ ሊሆን ይገባል። ተወልጄውን ሆነ ነዋሪውን #ማሳቀቅ በፍፁም ሁኔታ የተከለከለ መንገድ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ።
 
ለዚህም ይመስላል ልጅ እግር ፓርቲወች ከጠበቁት በላይ የተሻለ የድምጽ በዚህኛው ምርጫ #ውጤት ያገኙት። በእጥፍ ደጋፊ ያገኙ በተለይም በወጣቶች የተደገፋ ፓርቲወች የነገው የትውልዱ መስመር መሆኑን ሳስብ፦ ስደተኞች እራሳቸውን ቀጥተው የየአገሩ ህግ፤ ድንጋጌ እና ደንብ በሚፈቅደው ልክ ለመኖር ከአሁኑ ማቀድ እና ወደ ተግባር መቀዬር መለወጥም ያለባቸው ይመስለኛል። ያው እኔም ስደተኛ ነኝ እና ይመለከተኛል። 
 
በሌላ በኩል ሰባዕዊ መብት ጥሰትን እንደመደበኛ ተግባራቸው አድርገው የያዙ ኢትዮጵያ እና መሰል አገሮችን የሚመሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ወደ ተፈጥሯዊነት፤ ወደ ሰባዊነት መመለስ ይኖርባቸው። በጭካኔ ድርጊታቸውም ሊያፍሩ ይገባል። ሥልጣኔ አጥተው በስጋት እና ህዝባቸውን በማሸበር ያገኙትን ሥልጣን ሊመረምሩት ይገባል። ሥልጣኔ አልቦሽ ከመሆን በላይ አሳፋሪ ድርጊት የለም። ቀደምት አገርን ባልሰለጠነ አመራር መምራት አሳፋሪ ክስተት ነውና። በፀፀት ወደ ቀልባቸው ሊመለሱ ይገባል።
 
የሆነ ሆኖ #SPD የአገኜው ነጥብ ዝቅ ያለ በመሆኑ ሥልጣኑን #ለCDU ጥምረቱን ለሚመራው በሰላማዊ ሁኔታ ለማስረከብ ግድ ብሎታል። አሁንም ከSPD ጋር ጥምረት ማድረግ ከተቻለ የተሻለ ተስፋ ለሰባዕዊነት ይኖራል የሚል የባለሙያወች ዕይታ አለ። የሆነ ሆኖ እስከ ቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ስደተኞች ግድፈታቸውን በማረም ወደ ትክክለኛው #ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ሰብዕና የመለስ ግድ ይላል። በተለይ በወጣቶች የሚደገፋ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደፊት የመምጣታቸው ምክንያት የህዝቡ መማረር ምንጩ ዲስፕሊን በዋናነት ስለሚጠቀስ እራስን ማረም፤ ማረቅ እና #ከህግ #በታች ሆኖ ለመኖር መፍቀድ ይገባል።
 
በሌላ በኩል የዚህን ምርጫ ውጤት ስመለከተው የጀርመን #መንፈስ #የሥልጣኔ ደረጃ አስመልክቶኛል። ሥልጣኔው የህሊና እና በመንፈስ ስለሆነ ሰላማዊ ሽግግሩ ፍጹም ድንቅ ነው። በዚህ የፖለቲካ ፋክክር ያደረጉት ሊቃናቱ ሳይሆኑ ይልቁንም የፖለቲካ ድርጅታቸው ዓላማ እና ተግባር፤ #ፖሊሲ እና አፈፃጸም መሆኑ #በሰብዕና #ግንባታ #ሲታክት ለሚውለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ሐዋርያዊ አስተምህሮ ነው። የጹሁፌም ጭብጥ ይኽው ነው። ለዚህም ነው ሥም ላይ ያላተኮርኩት። CDU የአውሮፓ ህብረትን በድርጊት ጠንካራ ያደረጉትን የቀድሞዋን የጀርመን ካንስለር ልዕልት ዶር አንጊላ ሜርኬልን መስመር ለመከተል የአማተረ ስለመሆኑ ዘገባወች እዬጠቆሙ ነው።
 
ለአሸናፊው የተከበሩ ፍሬደሪሽ ሜርስም መልካም የስኬት ዘመን እንዲሆንላቸው እመኛለሁኝ። ለልዕልቴ፤ ለውዷ እና ለክብርቴ ለዶር አንጊላ ሜርክልም ትልቅ የሰናይ ቀን ይመስለኛል ትናንት ምሽት። ተሰናባቹ ካንስለር የተከበሩ አቶ ኦልፍ ሹልዝም በመሪነታቸው ዘመን ለዓለም ለአበረከቱት የሰባዕዊነት ትጋት አመሰግናቸዋለሁኝ። ጥምረቱ ከቀጠለም የመሪነት ደረጃው ዝቅ ሊል ቢችልም ቀጣይ ሚና ሊኖራቸው እንደሚችል አስባለሁኝ። 
 
በጭንቀት ለሰነባበተው የአውሮፓ ፖለቲካም ቢሆን አንፃራዊ እፎይታ ይመስለኛል ይህ የጀርመን መራጭ ህዝብ ስኬት።
 
እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት?
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/02/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?