ልጥፎች

ከሜይ 18, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

«#UnitedByMusic” ይህ የእምዬ ሲዊዘርላንድ ለዓለም የላከችው የመንፈስ ስጦታ ነው። #Stolz!

ምስል
  • « #UnitedByMusic ” ይህ የእምዬ ሲዊዘርላንድ ለዓለም የላከችው የመንፈስ ስጦታ ነው። #Stolz ! "ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባት ምሰሶም አቆመች።"   79ኛው የዓውሮፓ የሙዚቃ ውድድር ትናንት በባዝል ከተማ በእምዬ ሲዊዘርላንድ #ኦስትሪያ ያሸነፈበት መሰናዶ በስኬት ተጠናቋል። በ2024 እምዬ ሲዊዘርላንድ አሸናፊ ስለነበረች የ2025 አዘጋጅ ቅድስቷ ነበረች። አንድ ሳምንት ቀድሞ መስተንግዶ የነበረ ሲሆን ተሳታፊወች በተመረጡ ከተሞች በነፍስ ወከፍ ግብዣ ነበራቸው። ህሊናቸው #ቤተሰባዊነትን ይዋህድ ዘንድ የነበረው ቅድመ መሰናዶ እጅግ ሳቢ ነበር ለእኔ።   ዘመናችን የዲጅታል ሆነ እና ሰውኛ ጸጋችን እዬተጫነው ስለሆነ የእኔ ማሽን ጄኔሬሽን አስመልክቶ ስጋቴ እጅግ የላቀ ነው። ለዚህም ነው ዓለማችን የፍቅር ተፈጥሮን በትምህርት ደረጃ #ካሪክለም ነድፋ ልትሰጥ ይገባል በማለት የዛሬ 15 ዓመት #ለተመድ እና #ለአውሮፓ ህብረት መሻቴን በክብር የላኩት። እነሱም የተከበሩ ስለሆኑ ለእኔ አንዲት ባተሌ ብላቴና አክብረው መልስ ሰጡኝ።   ይህን ያነሳሁት የነገ ጉዳይ ውስጤ ስለሆነ የኦስትርያ፤ የሲዊዝ የጀርመን እና የኢትዮጵያን የትውልድ ቀረፃ መሰናዶወችን ከውስጤ ሆኜ ነው እምከታተለው። ጭንቅላቴን የሚመራውም ይህ ትጉህ ሰውኛ የተስፋ ብርኃናማ መንፈስ ነው። ሰዋኛ! ሰውኛነት! ተፈጥሮ! ተፈጥሮኛነት! ቢፈቀድላቸው በዓለማችን ያለው የስጋት ዳመና ተወግዶ #ቤተሰባዊነት ይነግሥ ነበር።   የሆነ ሆኖ ዊዝደም ያበቀለው የአውሮፓ የየዓመቱ የሙዚቃ ድግሥ የዬዓመቱን ቴክኖሎጂ፤ የየዓመቱን የሳይንስ፤ የዓመቱን የሞድ፤ የየዓመቱን የሙዚቃ ምርት ዕድገት፤ የያዓመቱን የሚዲያ ክህሎት፤ የየዓመቱን የኮስሞቲክ ሥልጣኔ ብቻ ሳይሆን የየዓመቱን...