ልጥፎች

ከዲሴምበር 18, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በሰሜን ወሎ ህጻናትን ጨምሮ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጎዳታቸው ተገለጸ በሰሜን ወሎ በምግብ እጥረት ምክንያት የተጎዳ ሕፃን BBC

  https://www.bbc.com/amharic በሰሜን ወሎ ህጻናትን ጨምሮ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት መጎዳታቸው ተገለጸ በሰሜን ወሎ በምግብ እጥረት ምክንያት የተጎዳ ሕፃን የፎቶው ባለመብት, BUGNA HEALTH BUREAU 17 ታህሳስ 2024 በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ጨምሮ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ወረዳው አስታወቀ። በክልሉ ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅ እና የምግብ እጥረት መጋለጡን የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ዓለሙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ግጭት አንድ ዓመት ከመንፈቅ ያለፈው ሲሆን ከግጭቱ ባለፈ ወረዳው "ዝናብ አጠር እና በተፈጥሮ የተጎዳ ነው" ያሉት ኃላፊው በተደራራቢ ችግሮች ምክንያት የምግብ እጥረት መከሰቱን አስታውቀዋል። "ማኅበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን በአግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው [አድርጓል]" ሲሉ ተፈጥሯዊውን ተጽዕኖ የገለጹት አቶ ገ/መስቀል፤ "ረድኤት ድርጅቶችም ለማኅበረሰቡ አልደረሱለትም" ብለዋል። በወረዳው ብርኮ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ የካባ የአንድ ዓመት ከሦስት ወር መንታ ወንድና ሴት ልጆቻቸው በምግብ እጥረት "ስቃይ" ውስጥ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ምን አግኝተን እንርዳቸው? እስካሁን ድረስ በተቻለን ይዘናቸው ነበር። ከአዲስ ዓመት ወዲህ ግን ምንም ነገር የለም። ተያይዞ ቁልጭልጭ ሆነ እኮ?" ሲሉ ስላሉበት ሁኔታ አስረድተዋል። "ጡጦ የምልበት ጎን [አቅም] የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት...