እንዴት ይታረቅ?
እንኳን ደህና መጡልኝ። እንዴት ይታረቅ? „በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኽት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።“ መጽሐፈ መክብብ ፱ ቁጥር ፲፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.05.2019 ከመነኩሴዋ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ሁለት ነገር አለ። ይህን ሁለት ነገር ለማስታረቅ እንዴት ይቻል ነው መሰረታዊው ጉዳይ። በአንድ በኩል በሥነ ልቦና፤ በአካል የሚደርስ ጥቃት አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ጥቃት ለመከላከል መፍትሄ የሚሻ አካል ደግሞ ምክክር ሲያደርግ በባህርዳር ሰንብቷል። ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጦር ሃይሎች ጠ/ አዛዥ ሆነው እንዴት ይህን ሃላፊነት ለምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮነን ለቀቁ? በመርህ ደረጃ ይቻላቸዋል ወይ ምክትል ጠ/ሚሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከአገር እያሉ ለመሰብሰብ። መከላከያ 7ኛ ዓመት ባዕሉን ሲያከብሩ የክብር እንግዳው ሌላ ስለነበር ማለት ነው። ስለምን ሽሽት አስፈለጋቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ? አልገብቶም። የችግሩ ሁሉ ምንጭ የአማራን ማህበረሰብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ የተረቀቀው ህገ መንግሥት እና እሱን መሰረት አድርገው የወጡ ዬዬክልል ህገ መንግሥቶች፤ እንዲሁም ከእናት ህገ መንግሥቱ የፈለቁ ሌሎች ብሄራዊ ህጎች፤ ደንቦች፤ እና ፖሊሲዎች ናቸው። መቼም ካንሰር በፓናዶል አይፈወስም። ወይንም ኢንፌክሽን በፓናዶል አይፈወስም። አንድ ችግር መፍትሄ የሚያገኘው የችግሩን መሰረታዊ ጉዳይ ቢያንስ በመርህ ደረጃ መቀበል ሲቻል ነው። የጋዜጣዊ መግለጫዎች፤ የስብሰባ መግለጫዎች፤ የጋራ የፎረም ውይይቶች ሁሉ በሳቢያ ላይ የተሰኩ ከሆኑ ድካሙ የውርንጫ ሆነው ይቀራሉ። ለነገሩ የተለመዱ ናቸው...