ልጥፎች

ከኦክቶበር 24, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ፈሳሽ ፖለቲካ እና አደጋው። ሻማዋም ኑዛዜ ላይ ናት።

ምስል
ጥምዝምዝ አመክንዮ። „የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፣--- የሰው ልጅ ሆይ፤ የወይን ግንድ፣ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይን አረግ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?“ ትንቢተ ህዝቅኤል ምዕራፍ ፲፬ ከቁጥር ፲፪ እስከ ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ጭ ብጥ። መሻገር በአዎንታዊነት ቢሆን ምንኛ መልካም በሆነ። ወንዝ ከላይ ከላይ ሌላ ቦታ ዝናብ ሲጥል በድንገቴ ወንዙ ይሞላ እና ብዙ አደጋ ያስከትላል። ማለትም እዛ አካባቢ ዝናብ ሳይኖር ማለት ነው። የችግሩ ምንጭ ከሌላ በሚነሳ እንደማለት። ሙላቱም ደራሽ ይባላል። ምንልባትም ከሰዎች ተሻጋሪዎች በተጨማሪም የጋማ ከብቶችም ሊኖሩበት ይችላል።  አገር ሰላም ነው ብለው በተለመደው አኳሆን መሻገር ሲጀመሩ ድንገት ዶል ይልና ደራሹ የመጨረሻ ስንብት ይሆናል። የዋና ሙያተኛ የሆነው ግን ምን አልባት ከንፍሮ ጥሬ የሚያወጣው አምላክ ይድን ይሆናል። የኢትዮጵያ የቀውስ መነሻ ውስጣዊ ብቻ ነውን? እእ!የፈሳሽ ፖለቲካ አደጋ ይታዬኛል።  ወደ ቀደመው ጭብጤ ምልሰት ሲሆን አካባቢውን አጥንተው ሰማዩንም አስተውለው ላይ ዘንቧል ብለው የሚያስቡ ጠንቃቆች ግን ከመግባታቸው በፊት ወደ ወንዙ በተረጋጋ ሁኔታ አደብ ስለሚገዙ ብዙም ለአደጋ አይጋለጡም። ደራሽ ሙላቱ ተግ ሲል ሁሉም በነበረው መልክ ሲረጋጋ ሁሉም ወደ ቦታው ሲመለስ ወንዙን አቋርጠው ወደ ቀያቸው ይገሰግሳሉ። ለዚህ ነው አበው „የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ“ የሚሉት። ግን ኦዴፓ ይህን አስተውሎታልን? መሪው አገር መሪው አስተዳዳሪው አውራ ፓርቲ እሱ ስለሆነ። አሁን እማያቸው ጉዳዮች እና መጪውን ጊዜ በእጅጉ ያሰስበኛል በ2017 ህዳር ወር ላይ VOA ከአቶ