ጋዜጠኛ ተምስገን ደሳለኝ እንኳን ወደ አማራ ተጋድሎ መንፈስ መጣህልን!
„ጀግንነት ሰው መሆን ከሚለው ሲነሳ ትውፊት ይሆናል።“ „ኤርምያስ ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው … አንተ ግን ሂድ ከአፌም የጸፍኸውን የእግዚአብሄርን ቃል በፆም ቀን በእግዚአብሄር ቤት በህዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንበብ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው“ (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፮) ከሥርጉተ© ሥላሴ 23.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) · መነሻ። „ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ደግሞ ባላሳፈርሽ ነው።“ ምነው የአማራ ብዙሃን የመገናኛ ወኪል ቁርጥ አደረጋችሁት ጎመዳችሁት ፍሰቱን። ሙሉ ቢሆን ለዳኝነትም ይረዳም ነበር። ይህ ግን ቁንጽላዊ ነው የሚሆነው፤ ቢሆን ግን ሁለት ነገሮችን ማንሳት ግድ ይላል። ሙሉ ስዕል ለማዬት ባልችልም በአገላለጹ ላይ ጋዜጠኛ ተምስገን ደስለኝ የአማራን ተጋድሎ እና የገዱን መንፈስ ውስጥነት ዕውቅና የመስጠት ዝንባሌው ለእኔ ድንገቴ ነበር። እንደሚመስለኝ ያላባራው የአማራ መፈናቀል እና ማዕከላዊ መንግሥት የሰጠው ተባደግ አያያዝ ወደ ራሱ እንዲመለከት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነፍሱ ድንግልዬ መልዕክት እንደላከችለት አስባለሁኝ። እኔንም ወደ አማራ ተጋድሎ ጥቅልል ብዬ እንድገባ ያደረገኝ የቪዥን ኢትዮጵያ የጉባኤ አመራር አሳታፊነት፤ እንዲሁም ሚዛናዊነት አድሏዊ አያያዝ ስነበረው ነው። አንዳንድ አጋጣሚዎች አትኩሮትን የሚስቡ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ አቅም በመፍጠር ረገድም እጬጌዎች ናቸው። https://www.youtube.com/watch?v=_CNYkBGZseM&t=2s ደራሲና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአማራ...