ጋዜጠኛ ተምስገን ደሳለኝ እንኳን ወደ አማራ ተጋድሎ መንፈስ መጣህልን!
„ጀግንነት ሰው መሆን ከሚለው ሲነሳ ትውፊት ይሆናል።“
„ኤርምያስ
ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው …
አንተ ግን ሂድ ከአፌም የጸፍኸውን
የእግዚአብሄርን ቃል በፆም ቀን
በእግዚአብሄር ቤት በህዝቡ ጆሮ
በክርታሱ አንበብ ደግሞም
ከከተሞቻቸው በሚወጡ
በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው“
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፮)
ከሥርጉተ© ሥላሴ 23.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
- · መነሻ።
„ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ደግሞ ባላሳፈርሽ ነው።“ ምነው
የአማራ ብዙሃን የመገናኛ ወኪል ቁርጥ አደረጋችሁት ጎመዳችሁት ፍሰቱን። ሙሉ ቢሆን ለዳኝነትም ይረዳም ነበር።
ይህ ግን ቁንጽላዊ
ነው የሚሆነው፤ ቢሆን ግን ሁለት ነገሮችን ማንሳት ግድ ይላል። ሙሉ ስዕል ለማዬት ባልችልም በአገላለጹ ላይ ጋዜጠኛ ተምስገን ደስለኝ
የአማራን ተጋድሎ እና የገዱን መንፈስ ውስጥነት ዕውቅና የመስጠት ዝንባሌው ለእኔ ድንገቴ ነበር።
እንደሚመስለኝ ያላባራው የአማራ
መፈናቀል እና ማዕከላዊ መንግሥት የሰጠው ተባደግ አያያዝ ወደ ራሱ እንዲመለከት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነፍሱ ድንግልዬ መልዕክት
እንደላከችለት አስባለሁኝ።
እኔንም ወደ አማራ ተጋድሎ ጥቅልል ብዬ እንድገባ ያደረገኝ የቪዥን ኢትዮጵያ የጉባኤ አመራር አሳታፊነት፤
እንዲሁም ሚዛናዊነት አድሏዊ አያያዝ ስነበረው ነው። አንዳንድ አጋጣሚዎች አትኩሮትን የሚስቡ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ አቅም በመፍጠር ረገድም
እጬጌዎች ናቸው።
ደራሲና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረገው ቆይታ፡፡
·
መክፈቻ።
ተሜ እንዳይታመም ሁሉ እዬሰጋሁኝ ነው። በተለይም አንጀት በሸተኛ እንዳትሆን። ቁርጥ እኔ ወጣት እያለሁኝ የነበረው ዓይነት ጭስ በውስጥህ ይታዬኛል፤ እኔ ቡድን ሲላክ ወደ እኔ ወደ አለሁበት አውራጃ ደውዬ ለውሎ አብል የላክችሁዋቸው ባለወንበሮችን
ሸኝተናልቸሁዋል ብዬ እደውል ነበር።
ወደ ክ/ ሀገርም ስሄድ ግንባር ግንባራችን ሳትለን ቤታችን እናጽዳም ይሉ ነበር እነዚያ
ሊቀ ለቃውንታት የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁራን። ይህም ብቻ አይደለም አለቆች የሆኑ ሹመኞች ለሥራ ጎንደር ሄደን ግብዣ ሲያደርጉልን ከቡድኑ በመለየየት በይፋ አልበላም፤ አልጠጣም እል ነበር።
ስለምን? ሲባል ገበሬ አልቅሶ የተገኘ፤ የተዘረፍም ስለሆነ የወገኔን ደምም አልበላም አልጠጣም በማለት እነዛ የሚሳሱልኝን መሪዎቾን አስደነግጥ ነበር። አንድ ጊዜ ሟቹ የደርግ አባል ሻ/ ገብርህይወት በቅደም ተከተል ያዘዙልን ምግብ አሻፈረኝ
ብዬ ቤቴ ተመልሻለሁኝ። ሞገደኛ ነበርኩ።
አንድ ጊዜም ጓድ ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ ጎንደር መጥተው የራት ግብዣ ላይ ሳንጠራ በኋዋላ ሰንጠራ ትራፊ ልለቃም አልተፈጠርኩም ብዬ ቀርቼ ማስጠንቀቂያ
ሁሉ ተስጥቶኛል። በእኔ የሥልጣን እርከን ከግብዣው የቀረትሁት እኔ ብቻ ነበር።
ፈንገጥ ያለው ተፈጠሮዬ ቤትም ውስጥ ሳድግ እንዲሁ
ነው … ቤት ወላጆቼ አያዙኝም፤ ይህችን እናትዬ ትሰሪያት ተብዬ ተጠይቄ ነው። በመጠዬቅ እና በመታዘዝ ማህል ልዩነት አለው። በትህትና ለመጣ ግን ሌሌው ለመሆን ፈቃደኛ ነኝ።
ድፈረትን ጭነት አክሎ ለሚመጣ ግን በመጣበት ነው …
ተሜን እልሁን እና ድፈርቱን ሳይ እራሴን በምለሰት እቃኛለሁኝ … እርግጥ ነው
ወደ ፖለቲካው ዓለም ቋሚ ሠራተኛ ስሆን ግን ለእኔ የብረት መዝጊያ የሆኑ ሊቃናት ነበሩኝ ተሜ ግን ተማላ ነው …
ተሜዋ … ያን ጊዜ የእኔን ሰብዕና ቀርጸው ግን በሚገርምህ ሁኔታ አለቆቼ አባታም አዛኝም አሳቢም ስለነበሩ ተቀንጥሳ ትቀራለች ብለው ያስቡ ስለነበረ የገነነ ሙግት ሲኖር፤ ዘወር አድርገው ወደ ኮርስ ይልኩኝ ነበር። አርሲ እንድመደብ የተደረኩበት በዚህ ምክንያት ነበር። የተረጋጋ ሁኔታ ነው ሲሉም እንድመለስ ወደ ጎንደር አደርገውኛል።
ምን ለማለት ነው ለእኔ ቅዱሳን አባቶች ነበሩኝ፤ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ እና አንባሳደር ወንደወሰን ሃይሉ። ሌሎችም በተለያዬ ሁኔታ ስማቸውን እማነሳው፤ እነሱ ደግሞ ጎንደሬዎች
አልነበሩም። አቅሜ የሰጠኝ ጸጋዎቼ ናቸው።
ተሜ ግን ለዚህ አልታደልክም፤ ስለዚህ እባክህን ቀስ አድርገህ ያዘው፤ ባገኝህ ተመክሮዬን አጋራህ በነበረ። ምክንያቱም ቀጥታዊ ሳይሆን ጎናዊ ወይንም ሽንጣዊ ጥቃት እንዳይኖር ሰጋሁኝ በእጅጉ ... እባክህን ለፋንሻም
አዘኔታ
ይኑርህ። ይህም መቼም ለተሜ እማስገነዘብው የሚጨንቀኝም ጉዳይ ነው።
በተረፈ ተሜሻ
ወደ
አማራ ተጋድሎ መንፈስህ መምጣቱ እጅግ በጣም እጅግ አስደስቶኛል።
Welcome! ሻማም አብርቼለሁኝ። ባለቤት ለሌላው ማህበረሰብ ቢያንስ ለሥነ - ልቦናው አለንህ ልንለው ይገባል። ያነሳሃቸው ነጥቦችም እጅግ ከውስጤ የተሰሙኝ ነበሩ።
- የአማራ ተጋድሎ ሥነ - ልቦናዊ ጉዳት።
የአማራ ተጋድሎ ሥነ - ልቦናዊ ጉዳት እጅግ ረቂቅ ነው። ተቋማዊ
አያያዝም ይሻል። አማራ መንፈሱ ተበድሏል። ነፍሱ በጠራራ ጸሐይ ተግርፏል። አሁን የተጋድሎውን መንፈስ አሸናፊ ሆኖ መውጣቱን ለመቀማት
በዬአቅጣጫው ጥድፊያ ላይ ናቸው እንደ የፕ/ መስፍን ወልደማርያም ግርፍ ሰማያዊ ፓርቲ ያሉት፤ እንደ አብን ያሉት።
አብን ቅጽል
ነው። አብን ለአማራ ማህበረሰብ በአማራ ሥም አማራን ለበለጠ የሰውር ጥቃት እና ሽንፈት የሚመራ መንፈስን የያዘ ነው። ቅኖች ሊኖሩበት
ይችላሉ ግን አፈጣጠሩ ጤነኛ አይደለም። ቅኖቹንም አንጥሮ ማውጣት አይቻለም። ዱራኛነት። ይህ መንፈስ በ እርግጥ አማራዊ ጥቃት ካንገበገባው የት ነበር እስከ ሁለተኛው የአስቸኳይ አዋጅ ዕወጃ ድረስ?
ለዚህም ነው የፕ/ መስፍን ግርፍን ሰማያዊ ፓርቲን ውርስ
ቅርስ አስፈጻሚ የሆነው። ይህ የአደባባይ ሚስጢር ነው። እንዲደራጅ የታሰበብት ጊዜም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ
ለዛውም አስቸኳይ ጊዜ ባለበት ተጨማሪ የማሳጫ ጫናን ለመፍጠር ታስቦ ነበር። ጉባኤውም ካልጠፋ ቀለም ሰማያዊን ነው የተጠቀመበት።
ይህ ቅንብር አማራን በራሱ በአማራ ድርጅት የታጋድሎውን ታሪክ ለመዝረፍ ሆን ተብሎ የተቀነባባረ የእነ ፕ/ መስፍን ወልደማርያም ጥልቅ ሴራ ነው።
- · እግዚኦ ስለአንተ የጎንደር ህዝብ።
ለዚህም ነው ጎንደር ላይ ያ ህዝብ ተስብስቦ መሥራች ጉባኤውን
እልል እያለ የተቀበለው፤ ይህ መቼም አሳዛኙ ቲያትር ነበር ለጎንደር ህዝብ። ተጋድሎውን የሚቀማ አዲስ መንፈስ ሲመጣ እልል ኩልል
ብሎ መቀበል ጅልነት ነው …
በሌላ በኩል የገዱ መንፈስ ያስገኘውን አገራዊ ብሄራዊ ድልም አሳልፎ መስጠትም ነው። ይህን መሰል ጅልነት
እኔ በህይወቴ ከጎንደር ህዝብ አይቼ አላውቅም። አብን ሌላ ፓርቲ ጎንደር መሄድ መብቱ ነው። ስበሰባም መጥራት መብቱም ነው። ግን የራሱን ክብር
አሳልፎ ለመስጠት ታዳሚነት ግን እብደት ነበር። ከቤት መቀመጥ ይቻል ነበር። ባዶ አዳራሹን አስታቅፎ።
ከቤተ መንግሥት
አብይ ይውጣላችሁ ከቶ ማን እንዲቀመጥላችሁ ፈልጋችሁ ይሆን እነ ጅሎቹ … ጎንደሬዎቹ? "በሞኝ ክንድ" … እሰከ መቼ ድረስ ነው ጎንደር እንዲህ
ትውልዱን እያስባከነ የሚኖረው … አይበቃም … በአህአፓ፤ በወያኔ ሃርነት ትግራይ፤ በቅንጅት፤ በግንቦት 7 ወዘተ … ወዘተ
ቤተ መንግሥት አንፈልግም አንጋችነትነት ነው እኮ አሁን ተይዞ ያለው ጥንዙል ፈሊጥ ... ጅሎች።
… ጎንደር በዘመኑ ሁሉ ብቻውን ተነጥሎ ሲቀጠቀጥ፤ ለጆቹ በተገኘነበት ቦታ ሁሉ ያገኝ እዬረገጠን፤ እዬቀጠቀጠን ያን
ሁሉ መከራ አይቶ አዶናይ መከራህ ይብቃ ሲልህ አብይን ከነመንፈሱ ሸለመህ የ44ቱ ታቦት፤ ያ ሌት ተቀን በድዋ የሚተጋው ወገንም ድዋ ነው፤ ያከበርከው የእኔ ያልከው። ድልህን ቁጭ ብለህ ማጣጣም ሲገባህ አሁን ደግሞ አዲስ ጎጆ
አውጪ ሆነህ አረፍከው። እግዚኦ ስለአንተ የጎንደር ህዝብ።
አሁን ያለው የአብይ ካቢኔ እኮ የአማራ ተጋድሎ አካል ነው።
ይህን አካል ደግፎ ማስቀጠል እንጂ የዛን አካል ተቀናቃኝ ሆኖ መውጣት ጎንደር ሊያፍርበት የሚገባው ትልቅ የታሪክ ግድፈት ጉዳይ
ነው።
እሺ ጎንደሬውኦች "ኢሳያስ ኢሳያስ ነው" እያላችሁ የምትጽፉትንም ይጨምራል አብይ ይወረድላችሁ ማን እንዲሆንላችሁ ይሆን እምትሹት? ጅሎች። ጅልነቱ የታሪክ ነው።
ይግርሙኛል የአማራ አክቲቢስቶች፤
የአማራ ጋዜጠኞች፤ የአማራ ፖለቲካ ተንታኞች፤ የአማራ ድርጅቶች በአብይ አስተዳደር ላይ ጠናና ምልከታ ሲኖራቸው። ትጋታቸው እኮ
የተፈጠረው የተጠነሰሰው በአማራ ታገድሎ መንፈስ ነበር። ያ መንፈስ ልድል ሲበቃ ደግሞ ተቀናቃኝ ሆነው አርፈው ቁጭ አሉት።
ኦህዴድንም ከኦነግ ጋር ደመሩት? ኦህዴድ እኮ ነው አማራን አፍቅሮ ወንዝ ተሻግሮ ድልድዩን ሰብሮ ጠረናችን የፈቀደው። አፈር ድሜ ግጦም ተሟግቶ የተጋድሎ አርበኞን በሙሉ ያስፈታው የኦህዴድ አቅም ጭምር ነው። የምን ቀልድ ነው? የኦሮሞ ድርጅቶች ሁሉ እኮ ይህን አይደፍሯትም። ህብረ ብሄር የሚባለውም ሴቷን ለቅቀላ ወንዱን ለአንጋችነት ነው በቃ ... ያለንበት እኮ ነው ... ይሄ አንድ ሰው ብቅ ጥልቅ እያደረጉ የሚታዬው? ያ ፌክ ነው። አቅም በተገኜ ቁጥር ወደ መጋዝን ነው የሚላከው ... ነባሩ መንገድ ጠራጊውን ሁሉ ...
የሆነው ሆኖ አሁን ተመስገን የሚያሰኛው ተሜ ወደ ራሱ ተመለሰ።
ይህ ለአማራ ወጣቶች ታላቅ ክንድ ነው፤ ለገዱ መንፈስም የጀርባ አጥንት ነው። ስለምን? ተሜ ከሴራ ከሸር ከምቅኝነት ከአሉታዊ
ምልከታ በፍጹም ሁኔታ የተላቀቀ ነው። መርሃዊ ወጣት ነው። ግልጽነቱ ልክ ደንበር የለውም። ደፋርም ነው።
ከሁሉ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዓርማ ደሙ
ነው። ኢትዮጵያ ጭንቅላቱ ናት። በተሜ ነፍስ ክፍት የነበረው አማራነት ነበር። አሁን ኢትዮጵያዊ ንጥረ ነገሩን ከአማራነት ጋር
አመጣጥኖ ከሄደ ለአማራ የህልውና ተጋድሎ ታሪክ ባይታሚን ዲ ነው።
ምክንያቱም እንደ ሰማያዊ ፓርቲ ያሉ የመንፈስ ዘራፊዎች ትናንትም ዛሬም ወደፊትም አያባሩም ስርቆታቸውን፤ ቅርጻቸውን
እዬቀያዬሩ የአማራ መዋለ መንፈስ ለመምጠጥ። ሳይችሉ ሲቀሩ ተለጣፊዎችን እዬፈጠሩ እነዛ በተከፈሉ ቁጥር አማራ ሲተራመስ እነሱ በማሀል
የራስ ተሰማ ናደውን ሌጋሲ ያስፈጽማሉ።
ቀስተደማነን ቅንጅትን ግንቦት 7 አሁን ግንቦት ሰማያዊን
የፈጠረው የፕ/ መስፍን ወ/ ማርያም መንፈስ ነው። እሳቸው ደግሞ ጎንደርን "ባዶ" ሲሉ ቁጭ ብዬ ነው ያዳመጥኳቸው፤ "አማራ
የለም" ሁሉም የሚያውቀው ሃሞታዊ ፍልስፍናቸው።
እሳቸውን የቀረቡ ወጣቶችን ሁሉ የጠመቁበት መርዝ ነው። መጥምቀ መርዝ ቢባሉ መልካም ነው። እንዲያውም የለም ያሉት ማህበረሰብ
አሁን ወደ ፋሽታዊነት ከፍ አድርገውታል። የሚያሳዝነው አሁንም ለመርዛቸው
እና ለሴራቸው ቤተ መንግሥቱ ክፍት ነው፤ አላዛሯን ኢትዮጵያ ሲሰልሉት ለኖሩት ለፕ/ መስፍን ወልደማርያም ምንግዜም የትኛውም መንግሥት ልብ ኑሮት አያውቅም።
ኢትዮጵያ የሽንፈት ቀጠና እንድትሆን የውጮች ሞክረው አልሳካላቸው
ያለው በአማራ ደም ውስጥ ያለው የኢትዮጵያዊነት ገናና መንፈስ ጽናቱ ብቻ ነው። ዛሬም አዲሱ ትውልድም እዬታዬ ነው። ለዶር አብይ አህመድ
በፃፍኩት አቤቱታ እስኪ ዕድሉን ይሰጠው እና ብሄራዊ ሰንደቁን ይዞ እንዲወጣ አማራ ከእናት አገሩ መንፈሱ ከተነጠለ ያዩታል አልኩኝ
የሆነውም ይሄው ነው።
ለዚህ ነው ፕ/ መስፍን ወልደማርያም አማራን አምርረው የሚጠሉት።
ኢትዮጵያ በግማሽ ልቦና ስትስተናገድ ፍስሃቸው ነው። የአማራን ትውልድ
ሥነ - ልቦናውን ቀብረው ኢትዮጵያዊነት በዝንጥሉ የማንኛውም አይነት ጥቃት ሰለባ እንዲሆን ይሻሉ።
እሳቸውን አምላኪዎች በሙሉ በዚህ
መንፈስ የተቃኙ የተጠመቁም ናቸው። እና አቤቱ ጎንድር „ባዶ“ ያሉትን ምፃተኛ
መስቃ ተናጋሪ ሙሁር ይቀበባል ወይንስ ከአብይ መንፈስ ጋር ይቀጥላል? ይህ የማያወላዳ ቀጥ ያለ መልስ ይሻል። የትኛውንም የፌኩን
ጉዞ መተው ወይንስ ለዚህ ማደግደግ? ኢትዮጵያን ሆነ አማራን ያቃለለ፤ የዘለለ፤ ጨፍልቆ እና ረግጦ ለመሄድ ያሰበው ጊዜ እዬጣለው ነው
የሚሄደው።
ለአማራ ከአብይ መንፈስ ውጪ መድህን የለውም። እርግጥ ነው
ቤተ መንግሥት ውስጥ በስል የገባ ጤነኛ ያልሆነው መንፈስ እስከ ዲያስፖራው እንዳለ አስተውላለሁ። ነገር ግን የአብይን መንፈስ ማን
በመቅድምነት፤ በንጽህና እና በቅድስና ሲደግፈው፤ ሲረዳው እንደቆዬ ማስተዋሉን ለሚዛኑ መስጠት ግድ ይለዋል። ኦህዴድም አኩል ለደጋፊ አማራ መንፈሶች ዕውቅና መስጠት ግድ ይለዋል።
አሁን ይህን ሃሳብ መሬት ላይ ሊያስታርቅ የሚቸለው የተሜ
የብዕር ሞገድ ይሆናል። ተሜ አማራነቱን ከተቀበለ ከሺህ ካድሬ፤ ከሺህ ጋዜጠኛ፤ ከወዘተረፍ የፓርቲ ድርጅት ይበልጣል። እኔ እንዲያወም የአማራ ብዙሃን ሚዲያ
በቋሚነት ቢቀጥረው ምኞቴ ነው። ሃብቱን ቢጠቀምበት ይመረጣል።
የሽግግር መንግሥት ህልመኞች ጠለፋዊ ምትሃት።
የሸግግር መንግሥት የሚሉ አሉ። ይህ የጠለፋ ጉዳይ ነው።
ይህን የመሰለ የሰማይ እና የምድር ብቃት እራሱን መምራት ለተሳነው መንፈስ አስረክቦ ኢትዮጵያ ከሚጠፉት አገሮች ተርታ ማሰለፍ ወይንስ
የብቃት ልቅና ያለውን መንፈስ ደግፎ፤ የጎደለውን ሞልቶ፤ ቀዳደውን ሸፍኖ አብሮት ከጎኑ መቆም የቱ ነው ቀላሉ መንገድ?
ራሱ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች መሪ አልነበራቸውም። በሃሳብ የሚበልጥ
መሪ አልነበራቸውም። ሁሎችም በተመሳሳይ ደረጃ ነው የነበሩት። አንዱ ሌላውን ለመዋጥ ነበር ፉክክሩ የነበረው። አሁን ግን አለ።
የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች አቅማቸውን ያውቁታልና ዝብሪቱን አቁመው መመራት እንደሚገባቸው መቀበል ግድ ይላቸዋል። ያልቻሉት ደግሞ የልቦናችን ማግኘት ባይችሉም "ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነውና"
ድል ለአብይ መንፈስ ብለው በክብር፤
በሽልማት ታሪክ ሠርተው ትግሉን መሰናበት ነው። ትግሉን ሲሰናበቱ ደግሞ ለቅንነታቸው፤ ለሰጡን የመንፈስ ብርታት፤ ታላቅ የሽልማት እና የምስጋና ቀን ነፃነት
በመፈለግ ሲተጋ የነበረው ሁሉ ምንም ደንበር ሳይኖረው አክብሮ አሸኛኘት ሊያደርግላቸው ይገባል። ጀግኖቻችን ናቸዋ።
የጠፋውን ሁሉ ይቅር
ማለት ለራስ ክብር ነው። ስለዚህ ይህን ቅን መንገድ ቢከቱሉ ማን እንደነሱ ጌታ … ካለ ፈጣሪ ምርቃት የሚሆን ነገር የለም። አገር
የገቡትም ቢሆኑ የጡረታ ጊዜያቸውን በሰላም ቢያሳልፉ ተመራርቀው ቢለዩ መልካም ነው። ስንት ዓመት ሊኖርበት? አሁን ዘመኑ የወጣቱ
ነው፤ ፓለቲካውም ሥልጡን ነው፤ ስለዚህ ለስልጡኖቹ ወጣቶች ማስረከብ ጊዜ ፈቅዷል።
አሁን እኔ አቶ ሃይለማርያም ደሰ አለኝን እባከዎትን ሥልጣነዎትን ያስረክቡ፤ ይውረዱ ሞአ ኢብራሂም
ፋውንዴሽን ሽልማትን ይወሰዱ እያልኩኝ እጨቀጭቃቸው ነበር፤ ሞአ
ባይሸልማቸውም አሁን ግን ዲታ ናቸው። ሸልማት ሁላችንም በሥነ - ልቦና አበርክተንላቸዋል። ረቂቅ መንፈሳዊ ሃብት አላቸው።
አመስግነናቸዋል። ወቀሳ ነቀሳ የለም
ዛሬ። ቤተሰቦቻቸውን ይባርክ ብለናል። ከልብ እና ከቅንነት። ይሄው ሳይሰደዱ ቤተሰባቸው ኑሮው ሳይበትን በክብር አገራቸው መሬት
መኖር ያቻሉት በወሰዱት ዕንቁ እርምጃ ነው።
አቶ ደመቀ መኮነን ከተከሳሽነት የወጡትም በፈቃዳቸው እጩ
ተዋዳዳሪነታቸውን መልቀቀቃቸው ብቻ ሳይሆን፤ ከሥር ሆነው ሲመሩት ለነበረ ሚር/ ተመሪ ብቻ ሳይሆን አብረው ሞቱን ለመፍቀድ በመወሰናቸው፤
ተግባር ላይ ስላገኘናቸው፤ አሁን በሆነ ባልሆነው አይነሱም።
እርግጥ ውክልናቸው ለአማራ ህዝብ ስለሆነ አማራ ተጎዳ ሲባል ደማቸው
የማይቆጣበት ብልሃት ለእኔ ግልጽ ባይሆንልኝም፤ ግን አሁን ያለው ድባብ መልካም አዝማማሚያ ነው። እህቶቼ የሳቸው ፋኖች ናቸው።
ስለዚህ ያቺን 4ኪሎ አስቦ የነበረው ሁሉ ራሱን እኔ ማን
ነኝ? ህዝብ የወደደውን፤ ህዝብ ያፈቀረውን፤ ህዝብ አንቱ ያለውን እማልቀበል ብሎ ራስን ማሰናደት የጀግኖች ቁንጮ ያደርጋል። አዲስ
ልብስ ሲገዛ ደስ ይላል። አዲስ መንፈስ ሲመጣም ደስታ ይሰጣል።
ስለዚህ ለታዳሚም ጫና ባያበዙ ጥሩ ነው። ጊዜ ራሱ በቃህ ያላቸው
ማንኛውም ሊሂቅን … መጪውን ዘመን በመፎካከርም ቢሆን ሁሉን አጀንዳ ፈጻሚ ማዕከላዊ መንግሥት ከኖረ ጥቅሙን የሚፃረር ተጠቃሚ አይኖርም።
ፈቅዶ እና ወዶ አዲሱን መድህን መንገድ ይመርጣል። ከሁሉ የሚያስደስተው ከሶሻሊዝም የሴራ ፖለቲካ ጋር ተፋታን … ይህ የድሎች ሁሉ
የገድሎች ሁሉ ማህደረ ዝማሬ እጬጌም ነው።
- · ተሜ እንዴት ወደ አማራ ተጋድሎ ዝንባሌው ተመሰጠ።
በመጀመሪያ ነገር „የፈራ ይመለስ“ ከኦሮሞ ንቅናቄም የቀደመ
ነው። 500 የመይሳው ወጣቶች በራሳቸው ወጪ ቲሸርት አዛጋጅተው „የፈራ ይመለስ“ ሲሉ የተሜን ሞቶ መርህ አድርገውታል።
ከዚህ
ነው የተነሳው የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ፤ መጀመሪያ ፕራክቲስ አድርጎታል … ስለዚህ ተሜ ከዚህ መንፈስ ጋር ያን ያህል ሩቅ
መሄድ አያስፈልገውም ነበር።
በራሱ ችግኛዊ መንፈስ ውስጥ ያለን አብዮት ማበረታት ሲገባው ከሰማይ ሌላ ተስፋ አንጋጣጭ ሆነ … ልክ አንድ
ቅን አርበኛ አለ ለእሱ የሚሰጠውን አክብሮት እየሸበለለ ለሌላ ሲያስረክብ እንደማዳምጠው ማለት ነው … መቼም የጎንደር ቅንነት
መከራ ነው …
አሁን ተሜ ምልሰቱ ምክንያታዊነቱን የአማራ መፈናቀል ዋቢ
ደንጋጣ ጠበቃ አለማግኘት እና፤ ዛሬ ያለው የህዝብ ድጋፍን የማድመጥ አቅም ኖረው ተሜ። የነፃነት አርበኞችንም ከእስር ሲለቀቁ እኔ ስል የነበረው
ይህንኑ ነው። ከዚህ ሲወጣ ነው ብዙ ነገር የሚበላሸው። በመደበኛ አብይን እስከ መንፈሱ ዘልዝሎ የሰቀለው መንፈስ „የእኛ ወገን
አብይ እያለ“ እነ ተሜ ሌላ መንገድ መፈለግ አይገባቸውም ነበር። ተሜ እኮ የራሱ ችግኝ ነው ማዳበሪያ የሆነው ለአማራ ገናና እጹብ ድንቅ የተጋድሎ ኢዲስ ምዕራፍ በፋሲል አደባባይ በመይሳው የዘለቀ የበላይ መንፈስ!
- · ደስ የሚል ዜና።
ሌላው ደስ የሚለው ዜና አርበኛ
ዘመነ ካሴ ወደ አገሩ እንደሚገባ ዜና ከዘሀባሻ አዳምጥኩኝ። አርበኛው ሁሉንም ፈታትሾ አይቶ ስለመረመረ የእትጌ ኤርትራን ያህል ንጹህ እና ቅን አጋዢ አዎንታዊነት ለአብይ
መንፈስ ይሆናል የሚል ምኞት አለኝ።
አሁን አብን ውስጥ ቅኖች ይኖራሉ፤ ግን መረቡን አልተረዱትም። ስለዚህ ነው እኔ መንፈሴ በሰቀቀን
የሚያቸው። ውጥኑ መቼ? ስለምን የሰማያዊ ፓርቲ አሰርውሃ አስፈለገው? ስለምንስ ያን ቀለም መረጠው? ለእኔ ግልጽ ነው። ነገ ከሁለት እንደሚተረተር እና
የአንድነት ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥመው፤ ስለዚህ አቅም ለማባከን ፈቃደኛ አይደለሁም ለአብን። ቤተሰቦቼም አያባክኑም። አርበኛ ዘመነ ካሴም እንዲህ ዓይነቱ ላይ ግድፈት ላለመስራት ይጠነቀቃል ብዬ አስባለሁ። አቀባበሉስ ተባደጋዊ ይሆን?
- · የገዱን መንፈስ በአቅሙ ልክ ቁመናውን የማደረጃት አስፈላጊነት።
አቅም መበካን ያለበት። የገዱ
መንፈስ ዕውነተኛውም የአማራ ሥነ - ልቦና ይዞ መውጣት እንዲችል መጣር ነው ሥራችን በመደበኛ ሊሆን የሚገባው። የአማራዊ መንፈስ ጥርት ያለ ንጥራዊ ለክልሉ በአጅጉ
ያስፈልገዋል።
አማራ መሬት ላይ ሆነው ፌድራል መንግሥትን ሃላፊነት እንወስዳለን ካሉ የገዱ መንፈስ እና ባልደረቦቹ ይፈንዳሉ። አቅሙ አይፈቅድላቸውም። ያሉት አማራ
መሬት ላይ ነው፤ ሊታገሉ የሚገባቸውም ለተፈጠሩበት ዓላማ ነው። የፓርቲውን ሥያሜ፤ ዓርማውን፤ የመንግሥታቸውን ሥያሜ እና መለያውን
በጣምራነት መለወጥ ግድ ይላቸዋል። አማራ የ እኔ ነው ብሎ አያውቅም። ሊለውም አይገባም። ሳጅን በረከት፤ ሳጅን አዲሱ፤ ሳጅን አለምነህ የእሱ አልነበሩም እና።
አማራ መሬት ላይ ተሁኖ ህብረ ብሄር ፓርቲነት ሎጅኩን መሸከም አይችሉም። በጉልበትም ቢሆን ቦታውን
የያዙት ግን መረጠን የሚሉት አማራው እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳልሆነ ያውቁታል። ምኔ ብሎ? ምስጋና ለመስጠት፤ ለመጋበዝ ያለውን
ተባደግ እኮ እያዩት ነው።
አማራን የሚያቅርብ መንፈስ ገና አላዛሯ ኢትዮጵያ አምጣ መውለድ አላባት። አማራዊ መንፈስ አሁንም የጥቃት
ኢላማ ነው። አብዛኛው የሌላ ብሄረሰብ ሊሂቃን መሸጋገሪያ ሊያድርግ የሚሻው ደግሞ ይህን መንፈስ ነው።
ስለዚህ ጥርት ያለ መንገድ
እና ጥርት ያለ ጎዳና ይዞ መገኘት አለበት የገዱ መንፈስ። በስተቀር የ1983/ 1984 ዳግም ውክል አልባነት አይቀሬ ነው። ለዚህ ደግሞ አማራ
ፈቃደኛ አይደለም።
አሁን ተሜሻ ወደዚህ ድርጅት በቅርበት ከመጣ ይህን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የማያያዣ ሊንክ መፍጠር ይቻላል።
የተሜ የፖለቲካ ግንዛቤ ግልብ አይደለም። ፍሬ ነገሩን ከሥረ መሠረቱ ያውቀዋል። አጥንቶታል። ጠንካራ የሆነ አቅም አማራ መሬት ላይ ለማምጣት
ተሜ አንድ የመፍትሄ አካል ነው።
- ተወራራሽንት ትውፊትን በማስጠበቅ!
የአማራ ተጋድሎ ተወራራሽነት
እና ተከታታይነት የተጋድሎው ድል ውስጥ እንጂ በውጭ በሚፈስ ውሃ ላይ መማከል አይኖርበትም። የአማራ ተጋድሎ ከቄሮ ተጋድሎ ጋር
በመሆን ነው ለዚህ ድል የተበቃው። ቄሮም እነ ለማን ድጋፍ ከነሳ ታሪኩን ያጣታል። የቄሮን ድል ማስቀጠል የሚቻለው አብይ እና ለማን የገዱን መንፈስ አክብሮ ዕውቅና ሰጥቶ ማስቀጠል ሲቻል ነው። አሁን አንድ ዝግጅት አለ ሜኔ ላይ አዘጋጆች የሚገርሙ ናቸው።
ዝግጅታቸው ድሉ በቄሮ ላይ እንደሆነ ነው የሚናገሩት ...ተዛነፍ ግንዛቤ ነው። ብቻማ ተሞከረ፤ አማራን በመንፈስ ተገሎም ተሞከረ ሁሉም አልሆነም። አማራ ትምህክቱ ከቅንነቱ እና ከ አምላኩ ነው። ዘመኑ የመሰከረውም ይህንኑ ነው ...
እኛ ብንሆን ገዱን ጠርተን ለማን ልንለዬው? አይታሰብም፤ እንዲያውም እናበዛዋለን እኛ ... ቅንነቱን ... ብቻ ጊዜ የማያስተምራቸው ናቸው ...ለቄሮ ቅንቅስቃሴ መሰረቱ "የፈራ ይመለስ ነው።" ከዛም ክንዱ "የኦሮሞ ደም ደሜ ነው" ነበር፤ ከዛ የቀጠለውም የገዱ መንፈስ የለማን መንፈስ መቀበል ነው፤ ከዛ የቀጠለው አቶ ደመቀ መኮነን ውድድሩን በፈቃዱ መልቀቁ ነው ...
አሁን የምንደግፈው እኛ አማራዎች እንጂ እነሱማ ፍርሻና እመሳን ሲያውጁ ነው ውለው የሚያድሩት፤ በተሸፈነ ልብ ነው አገርም የገቡት ... አሁን በዚህ ሰዓት ጠበንጃ ያነሱትም እነሱ ናቸው ...
- ተመስጦ በጥሞና!
የዚህ ድል መንፈስ የለማ እና የገዱ መንፈስ ነው። የገዱን መንፈስ ዘንጥለህ ድልህ ታሪኬ ነው
ማለት አትችልም አማራ። ኦሮሞም እንዲሁ።
የአማራ
ታገድሎ ድል እና ገድል ወደ ተግባር የተሸጋገረው በአብን ሳይሆን በገዱ መንፈስ ውስጥ ነው።
ስለዚህ አማራ ያለውን አቅም ሁሉ
ገዱ መንፈስ ጋር ማዋደድ ይኖርበታል። ሌላው የገዱ መንፈስ ደግሞ ብአዴን የ100 ሚሊዮን ህዝብ ግዴታ የመወጣት አቅም እኔ አመነጫለሁ
ብሎ ያልተገባወን የሥልጣንም፤ የሃላፊነት ጫን ተደል መከራም መሸከም አይገባውም።
ፓርላማው፤ ፌድራላዊ መንግሥታዊ ተቋማት ምን ይሠሩ? ቅይጥ የሆነ ጉዞ ለድል አያበቃም። ክልሎች የራሳቸው የሥልጣን እርከን እና የሃላፊነት የወሰን ደንበር አላቸው፤ ፌድራላዊ መንግሥትም
እንዲሁ። ሥለዚህ ይህን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። አዲስ አባባ ላይ ህብረ ብሄራዊ አወቃቀር፤ አደረጃጃት እና አማራር ግድ ይላል።
አማራ ክልል ግን 27 ዓመት የተቀለደው ይበቃል።
ሁሉ የክልሉን
ህዝብ ፍላጎት ነው አስቀድሞ እዬተጋ ያለው። ትግራይ ለአዲስ የወጣቶች ፈጣራ ይተጋል አማራ ደግሞ አሳታፊነት ምንትሶ ቅብጥርሶነት
ናሙናነት ወዘተ እያለ እርካሽ ተወዳጅነት ለማትረፍ ይዳክራል፤ ይሄ መሳቂያነት ነው።
አማራ
ክልል ላይ ግን ብአዴኖች ወደ ውስጣችሁ ተመልሳችሁ የራሳችሁን ሥራ ለመስራት መትጋት ነው ድርሻችሁ። ለፌድራል እማ ላካችሁ እኮ
ሰው፤ እነሱ ይትጉበት፤ ለፌድራልማ ድምጻችሁ ሙሉ ለሙሉ ሰጣችሁ እራሳችሁን
ቀቅላችሁ … ከዚህ በላይ መስዋዕትነት የለም፤ ይህን በማድረጋችሁ ደግሞ ሁላችንም ነው ደስ ያለን።
ኢትዮጵያን የኮታ ሳይሆን የህሊና
ብቃት ከብሄራዊ አቅም ሙሉነት ጋር እንዲመራት ስለምንሻ። ብአዴን
ቧልቱ እና ቀልዱን ቆም አድርጎ ይህን የታቱ ዥግራን ማላገጥ አቁሞ፤ ይህ በቆዬ ዲሪቶ የማረተ የበረከት ጋንታ ንድፈ ሃሳብን ድርሰት
አቁሞ በፍጥነት የተቃጠለውን የሦስት ወር የለውጥ ወራት ሃላፊነት በዳብል ጥረት አሳድጎ ተጨባጭ አዲስ ታምር መፍጠር ይጠበቅበታል።
አሁን
አገር እንዴት እንደሚመራ እያያችሁ ነው፤ በ100 ቀን ምን እንደተሠራ … እነ ተሜን በአግባቡ መጠቀም፤ አቅርቦ በመደበኛ መዋቅር
ውስጥ አስገብቶ መራመድ ያስፈልጋል።
አዎንታዊ ሰዎችን ማሰባሰብ ያስፈልጋል። መብታቸውን ብቻ እንጂ ግዴታቸውን ለማያውቁት አቅም ማባከን
አያስፈልግም። የአማራ እሳት የላሱ ቅን ጀግኖችን የት አላችሁ ብሎ
ማቅረብ እና መንፈሱን ከመንፈሱ ማገናኘት ያስፈልጋል። ሥር ነቀል የአስተሳስብም የተገባርም ለውጥ አማራ መሬት ላይ ሊካሄድ ይገባል።
ሌላው
ፈቃደኛ ከሆኑ ሌላ ክልልም የሚኖሩ የአማራ ዕምቅ አቅሞችን ወደ ድርጀቱ ማምጣት ግድ ይላል። ባይታዋር ናቸው። ለዚህም የተጠናከረ ገምጋሚ ቡድን
አዘጋጅቶ አቅምን በጥናት ላይ በተመረኮዘ ሁኔታ መሰብሰብ ግድ ነው። ለዚህ ደግሞ ፕ/ አበባው አያሌውን የመሰለ ሊቀ ሊቃውንት አላችሁ
…
ብአዴኖች ከለማ ከከኦህዴድ ተማሩ … አማራ እንኳንስ ሌላ ክልል፤ የፖለቲካ አቅሙ ተጠቃሚ ጠቃሚ ሊሆን ቀርቶ፤ አማራ መሬት ላይም ከፖለቲካ ተስትፎ ተገሎ የኖረበት ዘመን ለመጨረሻ ጊዜ መልክ
መያዝ አለበት። መሃል አገርም አዲስ አባባ የሚኖሩትም ድሎቱን ትተው ወደ ህዝባቸው ተመልሰው ሙሉ አገልግሎት ለማበርከት ቅናዊ እርምጃ
መውሰድ ይገባቸዋል።
አማራ እኮ ወደ ፌድራል የሚወከል የረባ አለ የሚባል ሰው እኮ የለውም። ምክንያቱም አቅሙን ያልሰበሰበ ብኩን
ድርጅት በሥሙ በደንቀራነት 27 ዓመት ሙሉ ስለተሸከመ - አማራ።
አማራን አማራ ነው መምራት ያለበት። እርግጥ ነው በክልሉ የሚኖሩ
ማህበረሰቦችም የቁጥራቸውን ያህል ውክልናቸውን ሊረጋገጥ ይገባል። ከዚህ በተረፈ ግን በግማሽ እና በሲሶ ማንነት ቀልድ እና ቁምነገሩ
ማብቃት አለበት … ወጣቶችም የሚሉት ይሄንኑ ነው።
ሌላ ቦታ ተገለህ በባዕትህ ደግሞ የበይ ተመልካች ተሁኑ አይሆንም። እኛም አንተኛም።
ወጣቶቻችን ብቁዎች ወደ ፊት እንዲመጡ እንሻለን። ናፍቆናል የወጣት አማራ ብቁ አመራር …
የአብይ መንፈስን ቀጣይነት ዋስትናው ይሄው መንገድ ብቻ ነው። ጅሉ ጎንደርም
ልብ ይስጥህ መንፈስህን ሙሉውን ለአብይ መንፈስ መስጠት ይኖርብሃል። "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣላች፡ እንዳይሆን።
ጥያቄህን
ጊዜም ህግም ይፈታዋል። የኤርትራም ተፈቷል እንኳንስ የአማራ። ስክነት እና ስልት ይፈታውል። የተሰጠህን ስታመሰግን ሌላም ይሰጠሃል። ይጨመርሃልም። የተሰጠህን እያጣወርክ ከሆነ ግን የተሰጠህንም ትንጠቃለህ
… አንበሳህ ከእነ ሙሉ አካሉ መረከብህ ታላቅ ስጦታ ነው ….
ጎንደር
ሆይ የማታውቀው አገር አይንፍቅህ!
ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ