እቴጌ ጣይቱ ቶማስ።
እቴጌ ጣይቱ ቶማስ። ከሥርጉተ © ሥላሴ (07.07.2018።) (ከደጊቱ ሲዊዝሻ።) „ለሁሉ ጊዜ አለው ከሰማይ በታችም ለሆነው ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።“ (መክብብ ምዕራፍ 3 1) መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=f7N2xbsODz8 https://www.youtube.com/watch?v=NdTDI2xfS3U ኢትዮጵያዊነትን ፍለጋ - ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለአመታት የተደረገዉ ጉዞ የተወለደችው በታላቋ ብርቴን ነው። ከዛ ወደ ጃምይካ ከዛም ኑሮ በአሜረካ። አያቷ ጎጃሜ ናቸው። ለተወሰነ ዓመት ባህርዳር ቆይታለች። አሁን ግን አዲስ አበባ ነው የምትኖረው። አዲሱ የ ዓለምን ሚዲያ እያስደመመ የሚገኘው የሞድ ኢንደስተሪ ባለሙያ ናት። የሠለጠነቸውም አውሮፓ ውስጥ እንደሆነ ከቃለ ምልልሷ ለማወቅ ችያለሁኝ። ዕንባ ፍል ነው? ግን ስለምን ፍል ሆነ? ዕንባዋን ማቆም አልተቻላትም። ሐሤቷ ወደር የለውም። ኢትዮጵያዊ ዜግነት በማግኘቷ። የኔዎቹ ዛሬ ስለ ድንቅነሽ ድንቂት ትንሽ ላወጋችሁ ፈለግሁኝ። „ኢትዮጵያ እምነቴ ናት“ ትላለች። ኢትዮጵያዊቷ እቴጌ ጣይቱ ቶማስ ለእኔ የኢትዮጵያ ጥበብ ናት። ሥነ - ህይወት ናት። ሥነ - ሥህን ናት። ሥህነ -መሆን ናት። ሥህነ - ነፍስ ናት። የእኔ ጣይቱ የልቤ መስረቲቱ የመሆን የኔይታይቱ። የእኛዊነት አርበኛይቱ እቴጌ ጣይቱ ቶማስ ውቢቱ። ድፍን ጠይም ፎለቄዩቱ የኢትጵዮጵያዊነት ሰንደቂቱ እጬጌይቱ! የትናንቷ አንሻ የድንቅ ነሽ ድንቂቱ የመሆን ብሥራት ጣይቱ የድል ዜና ህብሪቱ የኛይቱ ጣይቱ። የትውፊት እቴጌ ቀለሚቱ የብጡል ፍቅር ሰብሊቱ። ...