እርድ በሰማያዊ ተቀይ ጋር … በበረደው የጨዋታ ትዕይንት፤

ታጠፊያ አልጋ ይዞ ሜዳ የገባው የሲወዲን
 ቡድን ለሽ እንዳለ እንግሊዞች 
ለቀጣዩ ጨዋታ አለፉ። 

„ለሁሉም ዘመን አለው፣ ከሰማይ በታችም ለሆነው
ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።“
(መክብብ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፩ )
ከሥርጉተ ሥላሴ 07.07.2018
(ከደጓ ሲዊዝ።)

  • ·       ከእረፍ በፊት ስለነበረው ጨዋታ።

ዛሬ ፈታ ያለ ቀን ነው። ገብያውም ደርቷል። ርገጡኝ ላለ ለፈቀደ ምን አለ። የትናቱ አልጠቀመኝም ዛሬንም አለሁላችሁ ኑልኝ የተባባራችሁት እግሮች ሆይ ብላ ድንቡልቡሊት ይሄው ትደሰቃለች።



እንግሊዞች ተ30 ደቂቃው ላይ ገድ ሰጣቸው እና አንድ ለምንም በሆነ ውጤት የመጀመሪያውን ጨዋታ በግል አጨዋወት ዘይቤ የበላይነት በተጫነ የማጥቃት አቅም ጢባ ጢቦ አጨውተውቸዋል ሲዊዲኖችን በተወሰነ ደረጃ ለጥቂት ደቂቃ ቢሆንም። 

በቡድን ጨዋታ ቢቀምሩት ኖሮ ያገኟቸውን ወርቅ ዕድል ቢጠቀሙበት ሁለት መረብ እንኳን ደህና መጣሽ በሚል ማከያ ሦስቷን ጨበጥ አድርገው እረፍታቸውን ያጣጥሙ ነበር።

እኔ ለእንግሊዝ ቡድን የገጠማቸው ቡድን ስውዲን ስለሆነ ከዚህ የበለጠ ነጥብ ማምጣት ይጠበቅባቸው ነበር። በማሃል ሰፊ ክፍተት ነበረው የእንግሊዝ ቡድን። አንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ቲም ወርክ ያስፍለጋቸዋል። በእኔ ግምት የገጠማቸውን ዕድል በመጠቀም እረገድ ያደረጉት ጥረት ዝቅተኛ ነው።

እኩል የመሮጥ እኩል መፍጠን ይጠብቃባቸዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካም እንዲሁ ነው ኦህዴድ ኳሷን ይዞ ወደፊት ይገሰግሳል፤ አባል ድርጅቶች ግን ባሉበት ይድሃሉ፤ ተፎካካሪዎች ደግሞ  የዘጋቢነቱን ደርሻ ይዘውታል።

ያዬሁት ድክመት የፍላጎት የኮኦርድኔሽ ስስነትን ነው። የእንግሊዝ 10 ቁጥሩ የሚጥረውን ያህል ሌሎቹ አልነበሩ ማለት ያስቻላል። የጨዋታ ጥራት የሚጠበቀውን ያህል ነው ለማለት አልችልም። ግጥሚያው ከብራዚል ጋር ቢሆን እንግሊዞች ዛሬ ይሰናበቱ ነበር።

በሙሉ አቅማቸው ሊጫወቱ አልቻሉም። የመጀመሪያው ድል ለተጨማሪ ድል በር ከፋች ሆኖ የሥነ - ልቦና አቅማችን ገንብቶ አቅም ሊፈጥርላቸው አልቻለም። እንደገናም 10 ቁጥሩ ተደጋጋሚ የማጥቃት እንቅስቃሴ እድርጎ ግን ረዳት አጣ። ለወደፊትም ኦህዴድ አቅም ካነሰው በደራጎን ማህበር መዋጡ ያሰጋኛል። 

አጥቂ ብቻውን ሳይሆን ተከላካዮችም እኩል የማጥቃት ሂደትን መርህ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ጎል ጠባቂዎች ደግሞ ንቁ እና ብርቱ ጠንቃቃ መሆን አለባቸው ካፌ ለካፌ ቤት ከሚባዝኑ።

የእብሪሄሙች ቤተሰቦች ከሲዊዝ ጋር ካደረጉት ጨዋታ ዛሬም የተሻለ ተጫውተዋል ማለት አልችልም። ከሲወዲን ጋር ከመጨዋት ኩታ መቋጨት በስንት ጣዕሙ።  
  • ·       ከእረፍት በኋዋላ

ከእረፍት መልስ ሲዊዲን እንደገባ እንዲት ዕድል ሞከረ በለስ አልቀናውም። 50ዎቹ ገባን ሲሉ እንግሊዝ አንድ በ20 ቁጥር ተጫዋቻቸው አማክኝነት ድል እንደነገሩ ተደገመ እና ሁለት ለዜሮ ተሆነ። ከሲዊድን ጋር የሚደረግ ጨዋታ እጅግ አስልቺ እና ጨምታርም ነው።



እንግሊዞችም ቢሆኖ የተጠበቀውን ጥበብ ማሳዬት ያልቻሉበት ምክንያት የተፎካካሪያቸው ልዝነት ይመስለኛል። አብረው በረዱ። በአቅማቸው ልክ አልተጨዋቱም እንግሊዞች። ጨዋታውም ማራኪ አልነበረም እንዲያውም እጅግ አሰልቺ ነበረ። የሆነ ሆኖ ሁለት ለባዶ በሆነ ውጤት አልፈዋል።


የኔዎቹ እለቱ እንዲህ ነበር… ለዋንጫ ለመወስድ እንግሊዞች እሱ ይሁናቸው እንጂ በዛሬ አያያዛቸው ጥንካሬያቸው እንብዛም ሆነ ነው ያገኘሁት። ብዙ ክፍተት ነው ያለባቸው። 

ቅኖቹ ክብረቶቼ ለነበረን ጊዜ ኑሩልኝን ልሸልም።
ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።