ሬሳ ሃሳብን ለተስፋ ማለም መሬሳነት ነው!
አማራጭነት በሌለ እውነት
ተስፋን ተጠራ ማለት ያማል።
„እግዚአብሄር በዬሥራቸው ፀንተው የሚኖሩትን
ሁሉም አውቀው በህጉ ይጠብቃሉ።“
(መቃብያ ቀዳማዊ ምዕራፍ 21 ቊጥር 20)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ (07/07/2018)
(ከኮሽ አይሏ ሲዊዝ።)
- · መነሻ።
https://www.satenaw.com/amharic/archives/60177
„የኢትዮጵያ ፖለቲካ የለውጥ ጉዞ ከትናንት ዛሬ ቢሻልም ነገ ላይ ጥርጣሬ አለን
(ስዩም ተሾመ)“
- · ጠብታ።
ዛሬ ፏ ብላለች ልዕልተይ። ስለሆነም በጥዋቱ ቁርስ ሳልበላ ነው መጣፍ የጀመርኩት። ያስነሳኝም አልጋዬ አጠገብ ባስቀመጥኩት ማስታወሻዬ ላይ ተጋድሜ የጠፍኩትን ሥነ ግጥም ጡሁፍ መለጠፍ አስኝቶኝ። ተዚያ በሆዋላ ሳተናውን እንዴት አደርክ ልል ስገባ እንድ ሁለት ጹሑፎችን አገኘሁኝ። ተነበቡ እናም ዕይታዬ ተጣፈ እንዲህ …
- · እንዲህ
በዛሬው ጡሁፍ አንድ ልባም ነገር ሳነብ „ወያኔ ሃርነት ትግራይ“ ከግንባሩ ከወጣ ብቻ እና ብቻ ነው የመፍትሄ መንገዱ ይላል። እስከ አባላቶቹ እና ደጋፊዎቹ ድረስ ራሱን ችሎ ከኢህአዴግ ግንባር ወጥቶ እንደ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ኢትዮጵያ መሬቷን ያቆዮዋት የቀደምት አርበኞቻችን የነዘረይ ደረስም ስለሆነች እኩል እንደ ማንኛው ዜጋ መወዳድር እንዲችል ከተደረገ ያ አንድ መንገድ ነው። ዜግነትን ነሽም ሰጪም የለም እና። ይሄ የሚደገፍ ነው። ወጥ ፓርቲ የመሆንን ሃሳብ ሠመራ ላይ ባለው ጉባኤ ስለተነሳ ግንባሩ ሊከብደው እንደሚችል ጽፌ ነበር።
እርግጥ ነው በጥናት ላይ የተደገፈ እንደሚሆን ቢገለጽም በሌላ በኩል በመደመሩ ፓለቲካ ያሉ ሌሎች ንጥረ ነገሮችን ቢታከሉበትም በሂደት ፈተናውን ግን ግንባሩ ማለፍ አይችለውም። በሰው አዕምሮ ውስጥ ያለው የበቃን መንፈስን ገርቶ አንድ ነፍስ የሌላ ብሄረሰብ አባል የሆነ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ይመርጣል ብሎ ማሰብ አይመስለኝም። እብሮ መኖር ይቻላል። ደግሞህ ጨርሰኝ ግን አይሆንም። ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል እንዳይሆን ስጋትም አለብኝ። ሊታረቁ የማይችሉ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮች ይኖራሉ። ሁለት ውሃ የያዙ ብርጭቆዎችን እንድ ላይ አድርጎ በአንድ ብርጭቆ ማሟለት ቢሞከር ብርጭቆዎችም ይሰበራሉ ውሃውም ይፈሳል።
- · ሬሳን ሀሳብ ተስፋ ማድረግ አብሮ መሬሳነት ነው።
የዶር አረጋይ በርሄን ፓርቲ ተስፋ የማድረግ ሃሳብም በዚህ ጹሑፍ በጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመ አንብቤያለሁኝ። ስንት ጅሎች ነው ያለነው አሰኝቶኛል። የጅሎች ብዛታችን ልክ የለውም። ቅንነትም አለው ዓይነት። አንደኛ እሳቸውም በሰው እልቂት ወንጀልም ተጠያቂ ናቸው። ሁለተኛ የተለዬ ዓላማ የላቸውም። የሥልጣን ጉዳይ ነው ከአገር ያስወጣቸው ዘሩ አንድ ነው። አረና ይሁን፤ የአቶ ሞላ አስገዶም ሆነ የአቶ ገብሩ አስራት መድፊያው ታላቋ ኢትዮጵያ ሳይሆን ታላቋ ትግራይ ነው። አሁንም ለታላቋ ትግራይ ህልም አብረን ከፍና ዝቅ ከሆነ የቻለ ይሞክረው። እሾኽን ተሸክምህ እሾኹ አልከበደኝም ከሆነ እሾኹን በአዲስ መንፈስ ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ አንቦ ላይ መሞኮር ነው። እዛ ማዘመን። አማራ መሬት ላይ ግን እእ! ለሞቱ ቡፌ አይዘረጋም አማራ።
በሌላ በኩል አውሮፓ የዘለበውን ጃኬት ተሸክሞ መኖሩን ካወለቀ ዓመታት አለፉት። ከህብረቱ ፍረሰት ጋር ቀብር የተላከ ሬሳ ሃሳብ ነው። መሬሳነት ለመሆን ግን ከልካይ የለበትም የወደደ አሽኮ አድርጎ መሄድም መብት ነው። ያን ጊዜ ጸሐፊዎች ልጆች ነበሩ ተማሪዎች። ስለዚህ ዛሬን ለመወሰን ሆነ ለማወደድ አቅም የላቸውም። አብረን የነበረን በተደሞ ግራ ቀኙን ስንከታተልን የነበር ደግሞ በህይወት አለን።
ሁሎችም ከአንድ ወንዝ የበቀሉ ናቸው የተጋሩ ፓርቲዎች። የሚያናቁራቸው ወንበር ነው። ሥም እና ዝና ነው። በህብረ ብሄር ፓርቲ አባወራ የነበሩትም በዬዘመኑ በዬፌርማታው ተንጠባጥበው ነው የቀሩት። ሁሉችም ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ የተለዬ መሥመር የላቸውም። በ90ዎቹ ማእከላዊነት እስከ መጨረሻዎቹ ጊዜ እሳቸውን አውሮፓ ዘውድ አድርጎ ኑሯል። ከፍ እና ዝቅ ሲል ተባጅቷል አውሮፓ። የመሸበት ጸሐፊ ነው ይህን የሚጽፈው። መሠረቱን ሳያጠኑ እንዲህ ዋጋ አልባ ሆነው ወደ ወዳደቀቱ ሬሳ ሃሳብ ምልስትን የሚማጸኑ ጸሐፊዎች ያሳዝኑኛል። ለዛውም እኔ ነኝ ያለ ሊሂቅ የማይመጥነው የብቃት መንፈስ ሙሴ ኢትዮጵያ ላይ እያለ።
ቀድሞ ነገር ለፊርማ እንኳን ከአመራር አካላቸው ውጪ አባል የለውም ድርጅታቸው። ሁሉም የተጋሩ ልጅ በትግራይ ልማት ማህበር የተደራጀ ነው። እነሱንም አውቃቸዋለሁኝ በዝግቶቻቸው ተገኝቼ ዘግቤያለሁኝ። እጅግ ጠንካራ ናቸው ብርቱዎች ናቸው፤ ራሳቸውን ለመስጠትም ለተፈጠሩበት እትብት ቆራጦች ናቸው። ዶር አረጋይም በርሄም አንድ ሰው ከዛ ማህበር በአቅሙ ያመጣው የለም። ሥም ብቻ ነው ያለው። የረባ ጽ/ ቤትም ያለው አይመስለኝም።
አክተሮች ትናንትም ነበሩ ዛሬም አሉ ወደፊትም ይኖራሉ። ቀድሞ ነገር ስለፕሬስ ነፃነት ያላቸውን ትነት ገና ድሮ ድሮ ነው እኔ የጻፍኩባቸው፤ እርምት ለመቀበል የማይፈቅዱ በልባቸው ጥላቻን ቋጥረው የኖሩ ሰው ናቸው። ነፍሱን ይማረው እና በጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ምክንያት ከዚህ ግባ በማይባል ጉዳይ ነበር ሲሟገቱ የነበሩት ለረጅም ጊዜ። የእሱ ነገር ውስጣቸውን ያውካቸው ነበር። ስለምን? ጉዳዩን የሚያብሰለስላቸው እሳቸውን ስለሆነ እሳቸው ይመልሱት።
ለአረባ ወቀሳ አንደ ዓመት ስለተሟገቱ ሥራ ፈትነታቸው ቁልጭ ብሎ ይታዬኝ ስለነበር እኒህ ሰው ጠ/ ሚር ቢሆኑ በምን አቅላቸው ይሆን ብዕር እና ብራናን ሊያስተናግዱት የሚችሉ ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር። አቅል የላቸውም። ታጋሽነትም አልፈጠረላቸውም። ከአለ ሆደ ሰፊነት የትግራይንም ህዝብ ለመምራት ይከብዳል። በተለይ የትውልድ ክፈትት መኖሩን አያውቁትም። ማህበራዊ ንቃተ ህሊናውም አልገባቸውም።
ይልቅ የተገዛው የአቻዎቻቸው ዶክትሬት ቀልባቸውን ስቦ፤ ውድድር ውስጥም አስገብቶ እሳቸው ተምረው ያገኙትን ዶክተሬትነት ይዘው ነው የሚገቡት፤ ዛሬ አቶ አይደሉም ዶክተር ናቸው። ከዚህ በተረፈ አንዲትም ቅንጣት የኢትዮጵያ ህዝብን ውስጥ የሚያደርግ መንፈስ የላቸውም። ተሰፋው አለት ነው። ግን መደመር መደመር እንጂ መቀነስ ሳላልሆነ እዛው ከጥብቋቸው ላይ ተኮፈስው 4% ላይ መዘመን ነው። እና ግነቱ ባይበዛ ጥሩ ነው። ተስፋም የሚደረግባቸውም አይደሉም። ሌላ መከራ ለኢትዮጵያ ህዝብ አይጫንበት። የኖረበት የግዞት ዘመኑ ይበቃዋል። ተስፋ ማድረግ ከተፈለገ በቅዱሱ በአቶ ገብረመድህን አርያ ብቻ እና ብቻ ነው። እንዲሁም በእነ ወዲ ሻንበል እና መስሎቹ …
ግነት በሌላ አቅም ሲሆን ፈገግ ያደርጋል። ተስፋ ለማድረግም ደግሞ የመከነ ነው። „እንኳን ለአገራቸው መሬት አበቃቸው/ ያብቃቸው“ ማለት ግን ይገባል።
አውቃቸዋለሁኝ እኔ ውሳጣቸውን። አማራን እንደሚጸዬፍ። ጹሁፋቸው፤ ቃለ ምልልሳቸው ሁሉ የሚገርም ነው። ግን አከብራቸዋለሁኝ በአካልም ስለማውቃቸው። መድረክ ላይ ቁጭ ብለው ደጋፊ አካላት ሲዋቀር ሃጎስ፤ ተክላይ፤ ዕቁባይ እያሉ እንደ ታዳሚው ጥቆማ ሲያቀርቡ ከውስጤ እስቅባቸው ነበር ለዛውም ያን ጊዜ ወጣት ነበርኩኝ።
ምክንያቱም እኔ በነበረኝ የፖለቲካ ድርጅት ቦታ እና ደረጃ ሰው ጥቆማ ላይ የእኔ ሥራ አለነበረምና። ያልበሰለ ጥሬ ነገር ነበር ሲሠሩ ነበር የማያቸው። ጮርቃ ፖለቲካ ነበር ሲያራምዱ የነበሩት። የተጥመለመለ ጉድ። ዕውቅናው የተንጠለጠለ ብቻ ሳይሆን የተንሳፈፈ ነው። ዶር አረጋይ በርሄ እኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይን የመተቸት አቅም የላቸውም፤ ሞራሉም አይፈቅድም። ለዚህ ነው በመከራ ላይ በውስጥ ዘፈኑ በሚስጠር እድምታው የነበረውም። ከሞት እንኳን፤ ለስቃይ እንኳን ዜጋን የሚነጥሉ ናቸው።
ለነገሩ ደርጅታቸው ያው ትግራይን አንግሦ የማውጣት ነው ህልሙ። አሁን ደስ የሚለው ነገር ሁሉም አለው። እንደ 66ቱ አማራ ዋቢ አልባ አይደለም። በተለይ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሳጅን በረከት ስማዖንን ጋንታ ፍርሰርሱን አውጥተው፤ ጠራርገው እንደ ኦህዴድ ከሳውጡ፤ በሴራ የታሠሩ ቅኖችን አስፈትተው ቁልጭ ያለ ተግባር መፈጸም ከቻሉ፤ በህዝብ አመኔታ ያላቸውን ከሳመረጡ ማን እንደነሱ ጌታ።
የሆነ ሆኖ እነሱ ቢተውቱም ሞርሽ ገባ የሚል ቪዲዮ አይቻለሁኝ። ሞገደኛው ሞረሽ ለሁሉም ይበቃል፤ ይመክታልም። ተመክሮውን መሬት ላይ ሠርቶበታል። ማደራጀት ከጽንሰ ሃሳብ ጀምሮ አመራሩን ሁነቱንም በህጋዊ መድረክ ኑሮበታል። ስልጥኖበታል። የጫካ ተምክሮ አይደለም ያለው። ስለዚህ ሚዛኑ እኩል ለእኩል ነው። ማን ይፈራል ሞት ለመደመር ሥርዬት!እንግዲህ ነፍሱም ከሰነበተች ነው። ገረር ያለ ፖለቲካ ያራምድ ስለነበር እሱ ይሁነው።
- · ሞረሽ።
ሞረሽን አላገዝኩትም ግን አልተጋፋሁትም፤ የሞገትኩት ራዲዮ ፕሮግራም ሲጀምር ሃላፊነት አሰጣጡ ስሌቱ ስላልጣመኝ በጥኑ ሞግቸዋለሁኝ። የግል ቂም መወጣጫ ያ የአማራ ህዝብ መሆን አልነበረበትም፤ ከቅንጅት ፍርሰት ጋር የቆዩ ቅሬታዎች እና ሴራዎችን ከተጋድሎው ጋር ማቆራኘት የሚቀፍ ነገር ነበር። ታላቅ የታሪክም ግድፈትም ነበር።
ውሳኔው ለተጋድሎውም የሚመጥን አልነበረም፤ ከቂም የጸዱ፤ ከቁርሾ ጋር ያልተነካኩ የቅንነት ጋዜጠኞችን በጥንቃቄ የአማራ ልጆችን መምረጥ ነበረበት። ተዚህ ላይ የኖረበትን ተመክሮ ዕሴት አልባ አድርጎታል ሞረሽ።
አንድን ስብዕና በግል ልታከብረው ልትቀርበው ትችላለህ። ማንኛውም ሰብዕና፤ ግን የህዝብ ድምጽ ለመሆን ሰብዕናው ጥረቱ ሚዛን ላይ መቀመጥ ይኖርበታል።
በሌላ በኩል እጅግ ያስተከዘኝ የወሎ ጭፍጨፋን አስመልክቶ "ውግዝ ከአርዮስ" እርግማናዊ መግለጫው ነበር የሞረሽ። ያ ፈጽሞ ምራቁን ከዋጠ ሰው ከሚማራው ድርጀት ሊሆን የማይገባው ነበር። የተጋቡ - የተዋለዱ - ወደፊትም የሚጋቡ፤ በጉርበትና የሚቀጥሉ አባልነትንም ፈቅደው የሚኖሩ ይኖራሉ ከግንቦት 7 ጋር። ለትውልድ እንዲህ ዓይነት መንገድ አይበጅም። ተሳስታችሁዋል ይገባል፤ መሞገት በሃሳብ ይገባል፤ አዝናነንል ማለት ይገባል። ከዚያ ያለፈ ግን ትውልድ አይገናኝ እስከ መጨረሻው ከባድ ነው። የውግዘቱ ዕድምታ ግዙፍ ነው እኔ በግሌ ስመረምረው። የማልደብቀው ነገር ደንግጬለሁኝ።
አማራ መሞት ከለበት ለአማራነቱ ብቻ መሆን እንዳለበት አምናለሁኝ። የግንቦት 7 መፈጠር ደግሞ የጎዳው መከራውን ያበላው አማርን ነው። ባይፈጠር መልካም በሆነ ነበር። ብዙ ሰው ዓርማውን ማዬት አሁን አይፈቅደም።
ዓርማ የማይለጥፈበትን ኢትዮ ሚዲያን የሚጉበኙ ሰዎች ሁሉ አሉ። ያመረቀዘ ነገር ነው። ያንተ ያልሆነ ለወደፊትም ሊሆን የማይችል ግን በዛ ስም ግብር እንድትከፍል አዬር ላይ ፕሮፖጋንዳ መክፈት ለሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠንቀቀህ ለአማራ ብቻ ስቃይ መከራ ሞት፤ መሳደድ ያን ያህል መትጋት ከባድ ነገር ነው። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ የሰው ሊኳንዳ ቤት ነበር የተከፈተለት።
ይህን በሃሳብ መሞገት ይገባል። ነገር ግን እርግማን ሲሆን ከድርጅቱ ከግንቦት 7 የጭካኔ ውሳኔ በምን ይለያል ሞረሽ? ያን ስታወግዝ በውግዘቱ ውስጥ ያንኑ አንተ የምትፈጽመው ከሆንክ እኩል ለኩል ነው።
መነሻው ይገባኛል ግን ከእርግማን መራቅ ነበረበት መግለጫው። ከስሜት መውጣት ነበረበት እንደ ሰውን መሠረት አድርጎ እንደ መነሳቱ ሞረሽ።
በተረፈ አሁን አገር ቤት ገብቷል ሞረሽ አማራን በሚመለከት ሰው አለ ለማለት ይቻላል። ፓርቲም ሆነ የሚልም ያነበብኵኝ ይመስለኛል።
- · የተስፋ ሰነድ።
ያው የብራስልሱም የህይወት እና የትንሳኤ ሰነድ የተቃጠለ ካርቦን ሆኗል። አገግሞ ቢነሳም የሚሆን አይሆንም፤ እርግጥ ነው አሁን አቅምን ከአቅም ጋር ለማዋደድ የተለመደው መንገድ አይቀሬ ነው። ከእንግዲህ ግን ይሄ የአቋራጭ መንገድ አፈር ግጦል። ደቋል። ገጠር ለገጠር ክልትምትም ብሎ ህዝብን ማደረጃት ግድ ይላል … መኮፈስን በቀይ ጀንዴ ለማስኮፈስ አይሆንም።
- ቅን ቢሆነስ? ይቻላቸዋልን?
አሁን ከዚህ ሰላም የማይባበሉት ሁሉ ነው አገር ቤት የገቡት። አንድ ቀን በአንድ አዳራሽ ከጠ/ ሚሩ ጋር መታደም አይቀርም መቼም። ታናሻቸው ይቅር ተባባሉ ሊሏቸው ነው። ምን እና ምን ሊሆኑ ይሆን?
ሁሉም ከውጪ አገር ወደ አገር የገቡት ሁሉም ሴራን ድል አድርገው ሥምን በእጅ ባለ ነገር ላይ ከሀ መጀመር ያለባቸው ይመስለኛል። ሥም ብቻ ተሸክሞ ውድድር ለሞራልም አይሆንም።
አብሶ የአብይ መንፈስ ለሰንፍ፤ ለስልቹ፤ ለችኩል፤ ነገር ለሚያመላልሱ በዛም ተጠግነው ለሚኖሩት ፖለቲከኞች ፍዳ ነው። ጭካኔ አርግዘው ለሚሄዱትም መፈናፈኛ የላቸውም። ክፍለትን ለሰነቁም ድልድዩ ተሰብሯል። ስለዚህ አገር ቤት ከመግባት በፊት እራስን ውስጥን መንፈስን ማጽዳት ይጠይቃል።
መደመር ቢፈቀድም ቢኖርም ማንዘርዘሪያው ለሁሉም እንደሚሠራ ልብ ቢባል መልካም ነው። ምክንያቱም ጠ/ ሚሩ አንድ ናቸው እና። መሪም ናቸው እና ለሁሎችም።
ከዚህ ሄደው ፍርሻ፤ ንደት፤ ሴራ ለሚያሰኛቸው ባይጀምሩት ይሻላቸዋል። በሙያቸው ብቻ አግልግሎት ለመስጠት ቢፊቀዱ የተሻለ ነው። በዛ ላይ የማህበራዊ ንቃተ ህሊናው ከ66ቱ ፍልስፍና የወጣ ነው ያፈነገጠም ነው ... እና ከባህር የወጣ አሳ እንዳይሆኑ የጥሞና ጊዜ ያስፈልጋቸዋል።
- · ክወና።
ተስፋ ለተስፈኞች በሬሳ ሃስብ ላይ ሳይሆን በአዲስ በሰውኛ እና በተፈጥሮኛ በበቀለ ክህሎት ነው። ከአጋም ወጥቶ ከግራር ግን ለኢትዮጵያ እናቶች አልመኝም። የሄሮስ መለስ ዜናዊን መንፈስ አንቅሮ የተፋ መንፈስ የዶር/ አረጋይ በርሄ መንፈስን እንደ አዳኝ መንፈስ መቁጠር ለኮታ ለቁጥር ካልሆነ እነ ተጋሩ ተሳትፈዋል ለማለት ካልሆነ ዕዳው ዘመን አይችለውም ለመሸከም።
ጥንቃቄ እንጂ የጅብ ችኩል መሆን አይስፈልግም። ማስተዋል እንጂ ስሜታዊነት እንዲመራን ፈጽሞ አያስፈልግም። ስክንት ርጋታ ነገሮችን ከውስጥ መመርምር በእጅጉ ያስፈልጋል። አሁን ያገኘነው ዕድል በሆነ ባልሆነ ነገር ተብክሎ ባክኖ እንዲቀር ማድረግ የለብንም። የ66ቱ ሴራ እኮ 90 ደቂቃ በኢንቴቤ ምስጋን ይነሳው። አጋጣሚውን ከገኜ ገለባብጦ ለመቀመጥ ዓይኑን አያሸውም።
ይህ አሁን የተጀመረው እጅግ የረቀቀ ኢትዮጵያን መንፈሱ ያደረገ ሥልጡን መንገድ እንዲቀጥል ሱባኤ ያስፈልጋል። ልዑል እግዚአብሄርም ያውጣን ከማይታዬው የጭቃ እሾህ መከራ መሆኑንም ልብ ልነለው ይገባል። „እናስተውል!“
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚሰጢር ነው!
ቅኖቹ የእኔ የተስፋ ጣዝማዎች ለምትሰጡኝ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁኝ። ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ