የሚለምኑትን ሰዎች ልመናቸውን ይሰማቸዋል፤
„የሚለምኑትን ሰዎች ልመናቸውን ይሰማቸዋል፤
በንፅህና የልቡና ፈቃዱን የሚያደርግን ሰው ልመናውን
ይቀበለዋል።
እሱም ጸሎታቸውን ይሰማቸዋል፣
በለመኑትም ሁሉ ፈቃዳቸውን ያደርግላቸዋል።
(መቃብያን ቀዳማዊ 21 27)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 07.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
መሸታ የሸመነ መሸተኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛኛ
ካልገለበጠ የማያስተኛ።
ማገዶ ተከፍሎ ለመናኛ
የሥም አያሌው መጋኛ።
በመሾር ሽሮ ግርፋቱ
የመግል መቅኖ ለመብላቱ።
የጪስ ተወይራ ተገድግዶ
ፍሙን ማን ደፈርት
ተሸልቶ።
አያልቅም ፊደል መከረኛ
የዙር
ተመለስ ዛሬኛ።
የቄራ ጥቅጥቅ ሸር ጠጥቶ በመዋል
ያፍ ሰብል ምርቱ ሲዋልል።
መዋል አልዋለም ከነክቱ
የትነበር የኩራት አልባሳቱ?
ዕውነት ዬሌለው ተገንኖ
የቅጽል ልሳኑ ገምኖ።
እቴ የእኔቱ ባለ
ዕንባ
የልኳንዳ መብለት ተለላላ።
በእግር መዳፉ ሊናደፍ
ታጥቆ ተነስቷል ለመግፈፍ።
ትበይው ይሆን ያራጁን
የሴራ መለከት ጉበቱን?
እቴ ሆይ! ስላንች እኔም
እምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምመምምምምምምምምምምምምምምም።
- · ተጣፈ 07.07.2018፤ 09.00 ሲዊዝ።
- · ሥጦታ ለአክሮባቲስቶች።
- · እርእሱ "ዛሬኛ" ነው።
- ክብረቶቼ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ