እቴጌ ጣይቱ ቶማስ።

እቴጌ ጣይቱ ቶማስ።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 
(07.07.2018።)
(ከደጊቱ ሲዊዝሻ።)
„ለሁሉ ጊዜ አለው ከሰማይ በታችም 
 ለሆነው ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።“
(መክብብ ምዕራፍ 3 1)
  • መነሻ።

https://www.youtube.com/watch?v=f7N2xbsODz8
https://www.youtube.com/watch?v=NdTDI2xfS3U

ኢትዮጵያዊነትን ፍለጋ- ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለአመታት የተደረገዉ ጉዞ

የተወለደችው በታላቋ ብርቴን ነው። ከዛ ወደ ጃምይካ ከዛም ኑሮ በአሜረካ። አያቷ ጎጃሜ ናቸው። ለተወሰነ ዓመት ባህርዳር ቆይታለች። አሁን ግን አዲስ አበባ ነው የምትኖረው። አዲሱ የ ዓለምን ሚዲያ እያስደመመ የሚገኘው የሞድ ኢንደስተሪ ባለሙያ ናት። የሠለጠነቸውም አውሮፓ ውስጥ እንደሆነ ከቃለ ምልልሷ ለማወቅ ችያለሁኝ።




  • ዕንባ ፍል ነው? ግን ስለምን ፍል ሆነ?

ዕንባዋን ማቆም አልተቻላትም። ሐሤቷ ወደር የለውም። ኢትዮጵያዊ ዜግነት በማግኘቷ።

የኔዎቹ ዛሬ ስለ ድንቅነሽ ድንቂት ትንሽ ላወጋችሁ ፈለግሁኝ። „ኢትዮጵያ እምነቴ ናት“ ትላለች። ኢትዮጵያዊቷ እቴጌ ጣይቱ ቶማስ ለእኔ የኢትዮጵያ ጥበብ ናት። ሥነ - ህይወት ናት። ሥነ - ሥህን ናት። ሥህነ -መሆን ናት። ሥህነ - ነፍስ ናት።

የእኔ ጣይቱ የልቤ መስረቲቱ
የመሆን የኔይታይቱ።

የእኛዊነት አርበኛይቱ
እቴጌ ጣይቱ ቶማስ ውቢቱ።

ድፍን ጠይም ፎለቄዩቱ
የኢትጵዮጵያዊነት ሰንደቂቱ
እጬጌይቱ!

የትናንቷ አንሻ የድንቅ ነሽ ድንቂቱ
የመሆን ብሥራት ጣይቱ
የድል ዜና ህብሪቱ
የኛይቱ ጣይቱ።

የትውፊት እቴጌ ቀለሚቱ
የብጡል ፍቅር ሰብሊቱ።

አንቺ ጣይቱ የመውደድ አብነቲቱ!!

እንኳን ደስ አለሽ ጥበቢቱ
የኢትዮጵያዊነት ግርማዊቱ።


እኔ የፊልም ፕሮዲስር እንደነ መቅዲ እንደነ ፍጹሜ ብሆን በእቴጌ ጣይቱ ቶማስ ላይ አንድ ነፍስ ያለው ዶክመንተሪ ፊልም እሰራ ነበር። ተዋናይም ናት። ዲዛይነርም ናት። ሥልጣን ቢኖረኝ ይህቺን ድንቅ ስለ ኢትዮጵያዊነት እንድታስተምር ማናቸውንም መድረክ አመቻችላት ነበር። እራሷ ተቋም ናት። ራሷ የኢትዮጵያዊነት ኮሌጅም ናት። እራሷ የኢት ጵያዊነት ዩንቨርስቲም ናት። ዕንቁ!ይህን ያህል መንገላታት እልበራትም በDNN ማረጋገጥ ይቻል ነበር። ደከመች፤ ጣረች፤ ለፋች አሁን ዜግነቷን አረጋገጠች። ጀግኒት!
  • ·       ንቂት።

ይህቺ ድንቅ ራሷን ፈልጋ ያገኘች፤ ስንት አገር አቆራርጣ አፈሯን ለመርገጥ የወሰነች። በአፈሯ ውስጥ እሷነቷን በህጋዊ መሠረት ለመገንባት የታተረች፤ ብቸኛዋ የኢትዮጵያዊነት ልዩ ፈርጥ፤ ፍጹም ልዩ የኮከቦች ኮከብ፤ የልዩዎች ልዩ እጬጌያዊት ልዕልት ናት።


የሊቀ ትጉሃን ሊቅም ናት። ምክሯ፤ የምትሰጠው ትምህርት ራሳችን እንድንመረመር ይሞግተናል። ጊዜ መልካም ነው።

ስለ እትዮጵያዊነት ዕንባውን በማዬት ብቻ፤ እሷን ገፆዋን በመልከት ብቻ ውስጧን ፈልጎ በማግኘት ብቻ መማር ይቻላል። የኢትዮጵያዊነት ልዩ ፍጹም ልዩ ገድል ናት። ሚስጢር ናት።

ይህቺ የፍቅር እመቤት እናት አገሯን ኢትዮጵያን ከምንም እና ከማንም በላይ ትወዳለች። ታከብራለች። ስለ እሷ ተቆርቋሪነቷ በፍጹም ለመግለጽ አቅም የለኝም። እናታችን እናብቅላት እናጽድቃት እናስብላት ትለናለች።

ይህቺ የዘመን እንቁ "ደሜን ቢወጣ ኢትዮጵያዊ ነው" ትለናለች። የተደላደለ ኑሮዋን፤ ሥራዋን እርግፍ አድርጋ ትታ ባህርዳር ለመኖር የወሰነችው እቴጌ ጣይቱ ቶማስ 5 ዓመት ሙሉ ያለመታከት፤ ያለ ድካም፤ ያለ መሰልቸት ሁሉንም መከራ ታግሳ፤ የነገን ቀጠሮ አሸንፋ አሁን የኢትዮጵያዊነትን ማረጋገጫ አገኘች።
  • ·       ብሄራዊ ደረጃ ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ፓስ ያላት ድንቅ።

„የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤
      እግዚአብሄር
ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱

የሚገርመው አንድም ሰው ኢትዮጵያ ያለ በብራዊ ደረጃ ኢትዮጵያዊ የሚል ፓስ የለውም። እሷ ግን አላት።

አያችሁት የመንፈሷ ረቂቅነት። አያችሁት የፍቅርን ንጹህ ዳኝትን። አያችሁ የውስጥን መሻት ፈጣሪ እንዴት እንደሚመለከት። አሁን ከዛ ተወልዶ ያደገ በብሄራዊ ደረጃ ከዞጉ ውጪ ኢትዮጵያዊ የሚል መለያ ያለው ማን ነው? ይሄ ድንቅ ታምር የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያ የተባለችው በ27 ዓመት የኢትዮጵያ መከራ ውስጥ ልዕልት ጣይቱ ቶማስ ብቻ ናት።

ልጆቿም ብቻ አይደሉም መላ ቤተሰቦቿ ባለቤቷ፤ ወላጅ እናቷ፤ እህት እና ወንድሞቿ፤ የእህት እና የወንድሞቿ ልጆች ሁሉ ኢትዮጵያዊነታቸው ተረገጋገጦላቸው። እልልልልል ይላሉ ባንድነት።

ስደት አልፈልግም እናት አገሬ እያለችልኝ ትላለች። የጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን „ኢትዮጵያ አገሬን“ እጅግ እንደምትወደውም ትግልጣለች። ሁለት ልጆች አሏት። ሁለቱም ልጆቿ ቤተሰቡ በሙሉ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር ያበዱ ናቸው።
  • የእኛዊነት አርበኝት።

ያላትን ያወቀች። ያላትን ያከበረች። ያላትን ያደነቀች። ያላትን የወደደች። ያላትን የተመሰጠችበት። ያላትን የተቃኘችበት የእኛዊነት አርበኝት። ምን አለ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዘኛ ክፍል አንባቢ ቢያደርጋት። የእንግሊዘኛ ፕረዘንቴሽን ሲኖርም ምን አለ ቢያሳትፏት።

ዘመኑም አማሯል እኔ መላ ቤተሰቧ በጠ/ ሚር ቢሮ ብትጋበዝልኝ። በቤተ መንግሥት ማንኛውም ሥርዓት ላይ እንደ ዓርማ ሆነ፤ ተምሳሌት ሆና ብትታይልኝ ምኞቴ ነው። በ እሷ ሥምም የሆነ ነገር ቢከፍትላት። አይገባትም ወይ?!

የኔዎቹ ቅኖቹ እባካችሁን ደስ እንዲላት ይህን ጹሑፍ ፌስ ቡካችሁ ላይ ለጥፉልኝ። 
  
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ቅኖቹ ኑሩልኝ። እናንተን አያሳጣኝ።


መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።