ልጥፎች

ከሜይ 28, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጭንቁ ሌቦቹ አቅም አገኙ ነው።

ምስል
              ጭንቁ ሌቦቹ አቅም አገኙ ነው።  ለውጡን የመቀማትም ዕድል ሊኖር መቻሉ መጤን አለበት።                                                                       ከሥርጉተ ሥላሴ 28.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ ) „የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፤ በጥሩ ወርቅ አትገመትም። እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው? ከሕይዋን ዓይን ሁሉ ተሰውራለች። ከሰማይ ወፎች ተሸሽጋለች። ጥፋትንና ሞት ወሬዋን፣---  በጆሮቻችን ሰማን ብለዋል።“ (መጽሐፈ እዮብ ምራፍ ፳፰ ከቁጥር ፲፱ እስከ ፳፪) ·                                        መቅድም። ታዲያ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንን ጎፈሬ እንዲያበጥር ይጥበቃል? የቡላ አጥሚቱን፤ የጎን አጥንት ሾርባውን አዘጋጅተን ስናገጠግጠው በጡጧ ሰነባብተን የለም። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ አቅሙን ያደራጀንለት እኛው እራሳችን ነን። ለውጡ ሊቀለበስ እንደሚችልም ማሰብ ይገባል። ምክንያቱም ትግሉ ከለውጡ ጋር ነውና። በተቃዋሚ ሥም ገንዘብ የከፈለ ሁሉ ምርጥ ዜጋ ነው።  ስለሆነም በአገኘው ተቀባይነት እና ዕወቅና ሽንጡን ገትሮ ቀን ሲገነባ ሌሊት ሲያፈርስ ነው የከረመው። የትኛው ሚዲያ ነው ይህን ለውጥ ደግፎ የተነሳ? የትኛው? አንዲት ነገር እዬመዘዘ ሲታመስ አይደለም የተከረመው። እያንዳንዱ ሂደትን በስላቅ ሲዥጎረጎር አይደለም የተከረመው። ለውጡን የሚቃወሙ ሰዎች እዬተፈለጉ አይደለም ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ ሲደረግ የተከረመው። በምክንያቶች ላይ ሳይሆን በሳቢያዎች እና በዘሃቸው ላይ ብቻ ነበር ውርክቡ። የትኛው ሰው ነው ለውጡን በጤነኛ መንፈስ የሚይ ቃለ ምልልስ የተደረ