የግድፈቶቻችን ነቁጦች ምንድን ናቸው? ይጠኑ በራስ ህሊና። ይዳኙ በራስ ሚዛን ሳናሻግረው።
የግድፈቶቻችን ነቁጦች ምንድን ናቸው? ይጠኑ በራስ ህሊና። ይዳኙ በራስ ሚዛን ሳናሻግረው። "ሽበትስ የሰው ዕውቀቱ ነው፦ የእርጅናም ዘውዷ ያለነውር መኖር ነው።" (መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፱) #ስለምን ስኬት ራቀን? #ስኬት የሚባለው የሁላችን ውስጥ ስለምን ሊሆን አልቻለም? #እርካታስ ለመቼ ተቀጠረ? የርካታው ሃርድ እና ሶፍት ዌርንስ እንዴት ይበጅ? ለመሆኑ ታስቦበት ያውቃልን? #ከኢትዮጵያ ተፈጥሮ ጠረን ጋር ርቀታችን በምን ያህል ይሆን? #ዕውን ኢትዮጵያዊነታችን እንወደዋለን? ምክንያቱም ስለድህነቷ የሚጠዬቁት የሚፎካከሯት መሆኑን ስለማስተውልም። #ግንዬ እስቲ ብቅ በልልኝ በሞቴ። #በውስጡ ለመኖር ቆርጠናል ወይንስ ለመናጆ? #ለምን ቋንቋችን ባቢሎን ግንብ ናፈቀው? #ስለምንስ ያለን ነገር መበወዝ አስፈለገን? ጊዜውስ አለን? በጀቱስ? በቅለት ይሆን??? እ። #ልለብሰናል ወይንስ እርቃናችን እንሆን? በአቶ ሂደት። #ማን ተመሰገነ? #ማንስ ተወቀሰ? #መመስገናችን ምን አስተማረን? #መወቀሳችንስ ምን አጎደለብን? #ጉዟችን ወፍ ያወጣው ወይንስ ያደናቀፈው? #ተደናቀፏል ካልን ለምን? ተሳክቷል ካልን እንዴት ለማን? #ለመሆኑ ኢትዮጵያን በቀናባት፤ ኢትዮጵያን በሚፎካከራት፤ ኢትዮጵያን በሚበረብራት መንፈስ ውስጥ ዕውን ኢትዮጵያ አለችን? #ማነው ባላንጣ? #ማንስ ይሆን ባለአደራ? #ኢትዮጵያ የማን ናት? መልስ ያለው ታድሏል። የሌለው ግን ያፈላልግ። ለለትጉርስ፤ ለለት እራፊ፤ ለለት መጠለያ የሌለው ማህበረሰብ ወገንተኛ ነን እና። #ግን ማነው አጥፊ? #ግን ማነው ካሺ? #ግን ማን ይሆን አልሚ? እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉትሻ አገልጋይ። 2024/05/16 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።